Google search engine

ሀይንከን ክላረንስ ሴዶርፍንና የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ወደ ኢትዮጵያ አመጣ

ሀይንከን ክላረንስ ሴዶርፍንና የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ወደ ኢትዮጵያ አመጣ

ሃይንክን ዛሬ ሚያዚያ 2 ቀን 2014 ዓ.ም ዝነኛውን የእግር ኳስ ኮኮብ ክላረንስ እና የአውሮፓ ሻምፒዮና ሊግ ዋንጫን ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ለኳስ አፍቃሪያን አቀረበ፡፡

ሃይንከን ኢትዮጵያ ይህንን መርሃ-ግብር ያዘጋጀው የኢትዮጵያ እግር ኳስ አፍቃሪያን የአውሮፓ ሻምፒዮና ሊግ ዋንጫን እና የጨወታውን ኮከብ በቅርበት የማየት እና የማግኘት እድል እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው፡፡

ይህ በሃይንኬን የቀረበው የአውሮፓ ሻምፒዮና ሊግ የዘንድሮ መርሐ ግብር ዲሞክራቲክ ኮንጎ ፣ ሞዛምቢክ እና ናይጄሪያን የሚጎበኝ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ ኢትዮጵያ ደርሷል ።

የአውሮፓ ሻምፒዮና ሊግን አስመልክቶ በሃይንከን የሚቀርበው ዝግጅት የዘንድሮው ዓመት ስያሜ ውዳሴ ለሁሉም የኳስ አፍቃሪ ፤ ውዳሴ ለኳስ ተከባቢያን የሚል ነው፡፡ ይህም ማለት በእግር ኳስ መዝናናት የዘልማድ አመለካከቶችን በማስቀረትና ሁሉም አፍቃሪያን መካተትና አብሮነት እንዲሰማቸው በማድረግ ለድንቅ ጨዋታዎች ያላቸውን ፍቅር ያለግ ደስ እንዲያጋሩ ማስቻል በሚለው ላይ የተመሰረተ ነው።

በዚህ በዘንድሮው ዓለም አቀፍ ዝግጅት በሃይንከንም የሚቀርበው የአውሮፓውያን አመቱ የሻሚፒዮና ሊጉ ዋንጫ ጉዞ ሚያዝያ 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ የሚደርሰው ከሞዛንቢክ ተነስቶ ነው ። በዚህ በአዲስ አበባ በሚያደርገው የአንድ ቀን ቆይታ የእግር ኳስ አፍቃሪያን በአገራቸውና በከተማቸው ከዋንጫው ጋር ፎቶ የመነሳት እና ከሲዶርፍ ጋር የመገናኘት ተፈጥሮላቸዋል ። ዋንጫው ከአዲስ አበባ ቆይታው በኋላ በቀጥታ ወደ ናይጄሪያ ከዚያም ወደ ኮንጎ ሪፖብሊክ የሚጓዝ ይሆናል ።

ክላረንስ ሲዶርፍ በእርሱ ትውልድ በዝነኝነት ከሚታወቁት ምርጥ ተጫዋቶች መካከል አንዱ ሲሆን በሻምፒዮንስ ሊግ ከተለያዩ ክለቦች ጋር አራት ግዜ ዋንጫውን ያነሳ ብቸኛው ተጫዋች ነው። ክላረንስ ሲዶርፍ ከአውሮፓ ቻምፒይንስ ሊግ ታሪካዊ ቁርኝት ያለው ሲሆን በውድድሩ ላይም ድንቅ ብቃትና ተሰጥኦው ከማሳየት አንፃር የጎላ ሚና ያለው ነው ።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P