Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ሀድያ ሆሳዕና በወርሃዊ ደመወዝ አለመክፈል ችግር እንጂ  ለሻምፒዮንነት መጫወት ይችል ነበር” ፍቅረየሱስ ተ/ብርሃን  /ሀድያ ሆሳዕና/

 

ሀድያ ሆሳዕና በሀብታሙ ገዛኸኝ፣ በፍቅረየሱስ ተ/ብርሃንና የሐዋሳ ከተማው ተከላካይ ካሎንጂ ሞንዲያ  በራሱ ላይ ባስቆጠራቸው ሶስት ግቦች ሐዋሳ ከተማን 3-1 ያሸነፈ ሲሆን ተባረክ ለሐዋሳ ከተማ ብቸኛዋን ግብ ማግባት ችሏል።

ለሀድያ ሆሳዕና ከተቆጠሩት ግቦች ውስጥ አንዱን ያገባውና ለቡድኑም ጥሩ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ፍቅረየሱስ /ችምስ/ በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ ከሊግ ስፖርቱ  ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ጋር ቆይታን አድርጓል።

ሊግ፦ በሶስት ከተሞች ላይ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ተካሄደ፤ የእነዚህ ከተማ የውድድር  ቆይታችሁ ምን ይመስላል?

ፍቅረየሱስ፦ ከሶስቱ ከተማ ቆይታችን በሐዋሳ እያለን ቡድናችን ብዙ ውህደት ይቀረው ነበር። ይህም ሊሆን የቻለው ሁላችንም ከተለያየ ቦታ ስለመጣን አልተዋድንም ነበር። ፈርሶም የተሰራም ቡድን ነበርና  በቆይታችን ከስድስቱ ጨዋታ ሶስት ብቻ በማሸነፋችን ጥሩ አልነበርንም።  ወደ ድሬዳዋ ስናመራም ከሐዋሳ የሚሻል ውጤትን ባለማስመዝገባችን  ጥሩ ስኬት ሳይቀናን ቀርቷል።  አሁን ወደ አዳማ ስንመጣ ደግሞ ቡድናችን በአቋሙ ተስተካክሏል። ምንም ጨዋታን አልተሸነፈም። አሪፍም ሆነናል። ጥሩ የሚባለውን በቡድንም እየተመለከትን ነው።

ሊግ፦ ሀድያ ሆሳዕና ምርጥ ቡድንና ስብስብ ነው ያለው?

ፍቅረየሱስ፦ ስብስቡም ኮቹ ሙሉጌታ ምህረትም ጥሩ ናቸው። ግን የክለቡ አማራር ቦታ ላይ ያሉት ሰዎች ኳሱን የማወቅ ዝንባሌው ስለሌላቸው እና  ብዙ ነገሮችንም በሆይ ሆይ ክለቡን የሚያስኬዱት በመሆናቸው ቡድኑን በሚፈልገው መልኩ እንዳይጓዝ አድርገውታል።   እኛ ወደ ሀድያ ስንመጣ  ቡድኑ እንዲህ አልመሰለንም ነበር። በስታፉ አመራሮች በኩልም ደስ የሚል ነገርን  አታይም። ኳሳዊ ሰዎች ስላልሆኑ አሁንም ደግሜ እነግረዋለሁ ይሄ ጥሩና ምርጥ ስብስብ ያለው ቡድንን ወደ ውጤታማነት እንዳያመራ አድርገውታል።

ሊግ፦ ሀድያ ሆሳዕና ለተጨዋቾቹ ደመወዝ የመክፈል  ችግር ስላለበት እንጂ  ከእዚህ የበለጠ ውጤት እናመጣ ነበር እያልከኝ ነው?

ፍቅረየሱስ፦ በቃ እንደዛ እንዳይሆን አንደኛ ያደረገው ነገር እሱ ነው። በየጊዜው እንጠይቃለን መልስ የሚሰጠን አካል የለም። እኛ ለራሳችን ስንል ሜዳ እየገባን ኳሱን እንጫወታለን እንጂ በእነሱ በኩል ምንም አርኪ ነገሮች የላቸውም።

ሊግ፦ ለአሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ስትሉስ ለቡድኑ ተጫውታችኋል?

ፍቅረየሱስ፦ አዎን፤ እሱ ጥሩ አሰልጣኝ  ነው። ችግሩን ተንተርሶ ግድ የላችሁም ብሎ  ስለነገረንና ለእሱ ጥሩም ነገር ስላለን የተጫወትንበት ጊዜ ነበር።

ሊግ፦ ቤትኪንጉ ሲጠናቀቅ ምን ውጤትን ታመጣላችሁ?

ፍቅረየሱስ፦ አሁን ላይ  ለቡድኑ ሰዎች የተቀመጠላቸው ነገር  ክለቡ ከሊጉ እንዳይወርድ ማድረግ  ነው። ለምን ሰዎቹ ስራቸውን ስለሚያውቁት ነው። ከመጀመሪያው ጥሩ ነገርን ሰርተው ቢሆን ኖሮ ግን ለዋንጫ የሚጫወት አቅም ያለው ቡድን ነበረን።

ሊግ፦ በእናንተም በኩል ግን ቡድኑን እንዳይወርድ ለማድረግ ነው የምትጫወቱት?

ፍቅረየሱስ፦ ሻምፒዮናው  ላይ ለመድረስ በጣም ሩቅ ነው። ደረጃው ውስጥ ለመግባት ካልሆነ በስተቀር። ስለዚህም እስከ ስድስተኛ ሆነን ከጨረስን በቂ እና ከበቂ በላይ  ነው።

ሊግ፦ ዘንድሮ ጠንካራ ጎናችሁ ምን ነበር፤ ደካማና ክፍተት ጎናችሁስ?

ፍቅረየሱስ፦ ደካማ ጎኖች አሉን። ግን የማይሻሻልበት ምክንያት የለም። ጎል አግብተን ቶሎ ይገባብናል። በፍጥነት ጎል ጋር ደርሰን እነዛን አለመጠቀማችን ዋጋ ያስከፈለንም ነገር አለና እነዚህ የሚጠቀሱ ናቸው። ሁለተኛ ነገር  ደግሞ ሰውን ልትወቅሰውም አትችልም።  በሰጠከው ልክ ነው ልትይዘውና ልትወቅሰው የምትችለው።  ከመሀል  ደስተኛ ያልሆነ ሰው ሊኖርም ይችላል። እየደበረውም ኳሱን የሚጫወት ሰው ስላለም ካለው ነባራዊ ሁኔታ እንደውም እኛ  በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው የምንገኘው። ጠንካራው ጎናችን  ገብቶብን ራሱ ጎል እናገባለን።  ብዙ ጊዜ ሳናገባ አንወጣም። በተለይ አዳማ ከመጣን በኋላ በየጨዋታው አግብተናል።

ሊግ፦ ያስቆጫችሁ ጨዋታ?

ፍቅረየሱስ፦ በድሬዳዋ ከወልቂጤ ጋር ያደረግነውን ነው። ሁለት ጊዜ እየመራን ሶስት ነጥብ ማግኘት ሲገባን  አቻ ልንለያይ ችለናል።

ሊግ፦ በተለየ መልኩ ያስደሰተ ጨዋታ?

ፍቅረየሱስ፦ ይሄ ነው የምለው ጨዋታ የለም። ግን ከፋሲል ጋር ስንጫወት ጥሩ አቋም ስለነበረንና እነሱ ጎል አግብተውብንም አቻ የወጣንበት ጨዋታ ካሉት የሚሻል ነው።

ሊግ፦ በወቅታዊ አቋምህ በፊት በምናውቅህ ብቃት ላይ ነው የምትገኘው?

ፍቅረየሱስ፦ አዎን።

ሊግ፦ ጎሎችን እያስቆጠርክ ስለመሆንህ?

ፍቅረየሱስ፦ ይሄ ከአጨዋወት ሲስተም የመጣ ነው። በምፈልገው ቦታ ላይ ስጫወት ደስተኛ  ሆኜ ስለምጫወት በእዛ ነው ገና ሊጉ ሳይጠናቀቅ  የመሀል ተጨዋች ሆኜ 5 ግብ ላስቆጥር የቻልኩት።

ሊግ፦ የኮከብ ግብ አግቢዎች  መሪው የቅ/ጊዮርጊሱ  ኢስማሄል ጎሮ አጎሮ 10 ጎል አለው እደርስበታለው እያልክ ነው?

ፍቅረየሱስ፦ እኔ የመሀል እንጂ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች አይደለሁም። ግን እንደ መሀል ተጨዋችነቴ ከእዚህም በላይ ጎል ባስቆጥር ለቡድናችን ውጤት ጥሩ ነው። እኔ የምሰራውም ሁሌ ቡድኔ እንዲያሸንፍም ነው።

ሊግ፦ ወደማጠቃለሉ እናምራ?

ፍቅረየሱስ፦ እናንተንም የሚሰሟችሁ ከሆነ የሆሳዕና ሰዎች የእኛን የስፖርተኞች ጉዳይ ቢያስተውሉት ለቡድኑ ጊዜ ሰጥተው እንደ ሌሎቹ ከንቲባዎች ሜዳ መጥተው ጨዋታችንን ቢያዩት። ሌሎቹ ጋር ቢያንስ የክለቦቻቸው ስራ አስኪያጆች እንኳን ይገኛሉ። እኛ ጋር ይሄ የለም። ሁሌም በደመወዝ ጉዳይ ጭቅጭቅ ነው። ደመወዛችንን ማቋረጥ ልክ አይደለም። ብዙ የሚደብር ነገርም ነው ያለውና  እኛም እንደ እነሱ የራሳችን ህይወት ስላለን የወር ደመወዛችንን ቢከፍሉን ጥሩ ነው።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P