Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ወደ ዋንጫው ፉክክር ለማምራት ለዛሬው ብቻ ሳይሆን ለእያንዳንዱ ጨዋታ እኩል ትኩረት መስጠት እንዳለብን ተረድተናል ሳላአምላክ ተገኝ/ባህር ዳር ከተማ/ “ሁሉም ቡድን ለእኛ ጠንክሮ ቢመጣም የዛሬውን ጨምሮ እያንዳንዱን ጨዋታ ለማሸነፍ ተዘጋጅተናል”
ያብስራ ተስፋዬ /ቅጊዮርጊስ/

ሁሉም ቡድን ለእኛ ጠንክሮ ቢመጣም የዛሬውን ጨምሮ እያንዳንዱን ጨዋታ ለማሸነፍ ተዘጋጅተናል”
ያብስራ ተስፋዬ /ቅጊዮርጊስ/

ወደ ዋንጫው ፉክክር ለማምራት ለዛሬው ብቻ ሳይሆን ለእያንዳንዱ ጨዋታ እኩል ትኩረት መስጠት እንዳለብን ተረድተናል ሳላአምላክ ተገኝ/ባህር ዳር ከተማ/

በመሸሻ_ወልዴ

በጅማ ዩንቨርስቲ ሜዳ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከባህር ዳር ከተማ ጋር የሚያደርጉት የዛሬው ከሰዓት የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በጉጉት ተጠብቋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ በሚያደርጉት የዛሬው ጨዋታ ዙሪያ እና ከቡድኖቻቸው ጋር በተያያዘ ከሁለቱ ቡድን ተጨዋቾች መካከል ያብስራ ተስፋዬን እና ሳላአምላክ ተገኝን የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጠር ባለ መልኩ አናግሯቸው የሚከተለውን ምላሽ ሰጥተውታል።

ስለ ቡድናቸው ወቅታዊ አቋም የቅዱስ ጊዮርጊሱ ያብስራ ተስፋዬ ሲናገር “በአሁን ሰዓት በጥሩ አቋም ላይ እንገኛለን። ከስህተታችንም ተምረናል። ቡድናችን ዘንድሮ የግድ ዋንጫ ስለሚያስፈልገውም እያንዳንዱን ጨዋታዎቻችንንም እንደ ዋንጫ በመቁጠርም ልንጫወት ዝግጁ ነን”። የባህር ዳር ከተማው ሳላአምላክ ደግሞ በእዚህ ዙሪያ ሀሳቡን ሲሰጥ “በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ከጨዋታ ወደ ጨዋታ በጣም እየተሻሻልን ይገኛል። አሁን ላይም በጥሩ አቋማችን ላይ እንገኛለን። በቀጣይነትም ከእዚህ የበለጠ ምርጥ አቋም ይኖረናል”።

ስል ጠንካራ እና ደካማ ጎናቸው ለተጠየቀው ደግሞ ያብስራ ሲመልስ “ጠንካራው ጎናችን አንድነት እና ህብረታችን ነው። በድክመት ወይንም ደግሞ በክፍተት ደረጃ ደግሞ አለብን የምለው ችግር ብዙም የለም። ከዛ ተነስተንም በሊጉ ጉዞ ያለንን አንድነት የበለጠ አጠናክረን በማስጓዝ ክለቡ በቅርብ ዓመታት ያጣውን ዋንጫ ዳግም ወደ ቤቱ እንዲመልስ እናደርጋለን”።

ሳላአምላክም በእዚህ ዙሪያ ላይ ይሄንን ብሏል “የእኛ ጠንካራ ጎን በህብረት ማጥቃታችን እና መከላከላችን ነው። ክፍተት ጎናችን ደግሞ የምናገኛቸውን የግብ አጋጣሚዎች አለመጠቀም ነበርና ይሄ ችግር ባለፈው ጨዋታ ላይ ተሻሽሏል”።

ስለ ዛሬ ጨዋታም ለተነሳለት ያብስራ ምላሹን ሲሰጥ “ከባህር ዳር ጋር የምናደርገው ጨዋታ ጠንካራ እንደሆነ እናውቃለን። ሁሉም ቡድኖችሞ ከኛ ጋር ሲጫወቱ የፍፃሜ ያህል አድርገው ስለሚቆጥሩት ይህንን እና እያንዳንዱን የሊጉን ጨዋታ ለማሸነፍ ዝግጁ ሆነናል”። ሳላአምላክም አስተያየቱን ሲሰጥ “ከቅ/ጊዮርጊስ የሚኖረን የዛሬው ጨዋታ በቅርብ ጊዜያቶች ቡድናችን አንድ አንድ ነጥቦችን ጥሎ ከመምጣቱ እና ከተጋጣሚያችንም ጥንካሬ አንፃር ከባድ እንደሚሆንብን እናውቃለን። ያም ስለሆነ ወደ ዋንጫው ፉክክር ውስጥ ለመግባት ለእዚህም ጨዋታ ሆነ ለእያንዳንዱም ግጥሚያዎች ዝግጁ መሆን እንዳለብን ስላወቅን ቅዱስ ጊዮርጊስን ከፈጣሪ እርዳታ ጋር የምንረታው ይመስለኛል”።

ለየቡድኖቻቸው እየሰጡ ስላለው ግልጋሎት ደግሞ ጥያቄ የቀረበለት
ያብስራ ሲናገር “የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብን አስቀድሞ ደርሶብኝ ከነበረው ጉዳት አኳያ በእዚህ ፈጣን ጊዜ ውስጥ ቶሎ ድኜ እደርስለታለው ብዬ አልጠበቅኩም ነበር። ያም ሆኖ ግን ተሰልፌ በምገባባቸው ጨዋታዎች ላይ በፈጣሪ እርዳታ በፍጥነት ድኜ ክለቤን ሊጠቅም በሚችል መልኩ እየተንቀሳቀስኩ መሆኔ አስደስቶኛል። በቀጣይነትም ጥሩ ብቃቴን በማሳየት ቡድኔን እስከ ዋንጫ ባለቤትነት በሚያስደርሰው ደረጃም ልጠቅመው ዝግጁ ነኝ”። ሲል ሳላአምላክ ደግሞ “ለባህር ዳር ከተማ በሚሰጠኝ የመጫወቻ ቦታ ሁሉ ክለቡን በሚገባ ልጠቅመው ተዘጋጅቻለሁ። ጎሎችንም ከወዲሁ ማስቆጠር ጀምሬያለሁ። ከዚህ በኋላም የምችለውን እና ከእኔ የሚጠበቀውን ጥቅምም ልሰጠው እንደምችልም በጣም እርግጠኛ ነኝ”።

በመጨረሻም ሁለቱን ተጨዋቾች ሀሳባቸውን እንዲቋጩ ጠይቀናቸው ሲመልሱ ያብስራ እንዲህ አለ “በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ነጥብ የጣልንባቸው ጨዋታዎች ቢኖሩም አሁን ላይ ተመልሰን ስለነዛ ጨዋታዎች ማሰብ አንፈልግም። ቡድናችን ወደ ጥንካሬው ስለተመለሰ በእዛ ላይ ነው አተኩረን የምንሰራው። ከፈጣሪ እርዳታም ጋር የሊጉን ዋንጫ የምናነሳበት እና ምርጥ ድጋፋቸውን የሚሰጡንን ደጋፊዎቻችንን የምናስደስትበት ትክክለኛው ወቅትም ዘንድሮ ይመስለኛል”። ሲል ሳላአምላክ ደግሞ “የሊጉ ውድድር ዘንድሮ በዲኤስ ቲቪ መተላለፉ ሁሉንም ተጨዋች እያበረታታውና እያነቃው ይገኛል። ይሄንንም እኛ ተጨዋቾች ልንጠቀምበት ይገባል። በተረፈ የባህር ዳር ከተማ ደጋፊዎች ለሚሰጡን ድጋፍ ከልብ ላመሰግናቸው እፈልጋለው”።

https://t.me/Leaguesport

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P