Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ዋንጫ ባላነሳ ኖሮ ይቆጨኝ ነበር” “የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎች የዘንድሮ ዋንጫ ሲያንሳቸው እንጂ የሚበዛባቸው አዬደለም” ሄኖክ አዱኛ /ቅ/ጊዮርጊስ/

 

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሁለተኛ ዋንጫውን ያነሳው ሄኖክ አዱኛ  ከቄ/ጊዮርጊስ ጋር ዘንድሮ። ሻምፒዮና እንደምንሆን  ሙሉ ለሙሉ። ያወቅኩት ከአርባምንጭ ከተማ ጋር  የነበረንን ወሳኝ እና ፈታኝ ጨዋታ እንዳሸነፍን ነበር ሲል  ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ  አዘጋጅ  ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል።

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ከጅማ አባጅፋር እና ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር በማንሳት ሁለተኛ ድሉን ሊያጣጥም የቻለው ሄኖክ  ከአራት ዓመት በፊት ከተቀላቀለው እና ብዙ የዋንጫ ድሎችን ከተቀዳጀው  የቅ/ጊዮርጊስ ቡድን ጋር   የሻምፒዮንነት  ክብሩን ባይቀዳጅ ኖሮ በጣም ይቆጭ እንደነበርም ይናገራል።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ቅ/ጊዮርጊስ  የዘንድሮ የውድድር ዘመኑ  ሻምፒዮና ሲሆን  በዓመቱ ተሳትፎ ጥሩ  እንቅስቃሴን ካሳዩ ተጨዋቾች መካከል ስሙ የሚጠቀሰውን ሄኖክ አዱኛን ሊግ ስፖርት በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ  አናግራው  የሰጣት ምላሽ በሚከተለው መልኩ ቀርቧል።

የቢትኪንግ ዋንጫን  አንስታችኋል፤ ዓመቱ እንዴት አለፈ?

“በጥሩ ሁኔታ ነበር የውድድር ጊዜውን  ያሳለፍነው፤ ፈጣሪ እረድቶንም የውድድር ዘመኑን በሻምፒዮናነት ልናጠናቅቅ ችለናል”።

ከቅ/ጊዮርጊስ ጋር ሻምፒዮና መሆን ያለው ስሜት ምን ይመስላል?

“በጣም ነው እንጂ ደስ የሚለው ምክንያቱም ዓመቱን ሙሉ ለፍተን ነበር። ዋንጫውም ይገባን ነበር። ለእዛም ነው ደስታችን ከፍ ሊል የቻለው”።

የውድድር ዘመኑን ዋንጫ ያነሳችሁት በመጨረሻው ቀን በተደረገው  ግጥሚያ ነበር፤  ለስኬቱ ስጋት  አልገባችሁም?

“ባህርዳር ላይ የነበሩት  ግጥሚያዎቻችን  ለእኛ ትንሽ አልተመቸንም ነበር፤  ነጥብ እየጣልንም  እየተንሸራተትን ሄደናል። በኋላ ላይ እኛ ጋርና የአሰልጣኞች ስብስቡ ጋር  ያለው የውድድር  መንፈስ ሻምፒዮና  ከመሆን ጋር የተያያዘና ስኬታማ እንደምንሆንም እርግጠኞች ስለነበርን  ያን ልናሳካ ችለናል”።

በውድድር ዘመኑ ስለነበራቸው ጥንካሬና ክፍተት  ጎናቸው

“በክፍተት ጎን ደረጃ ብዙም የታየን ነገር አልነበረም።  ጥንካሬያችን ደግሞ አንድነታችንና መግባባታችን ነው፤ ከእዛ ውጪም አሰልጣኞቻችን ከእኛ ተጨዋቾች ጋር  በቅርበት ሆነው ይነጋገሩ ስለነበር እነዚህ ጎኖች ለጥሩ ውጤት ሊያበቁን ችለዋል”።

ቅ/ጊዮርጊስ  ለአራት ዓመታት  የሊጉን  ዋንጫን አላነሳም፤  የቡድኑ ተጨዋች ከመሆንህ ጋር ተያይዞ ይህን ስኬት አለመጎናፀፍህ

“የዋንጫ አለማንሳታችን ዋናው ምክንያት የአሰልጣኞች በየጊዜው  መቀያየር ነው። የዘንድሮ የውድድር ዘመን ሻምፒዮና የሆነው ደግሞ በሚያቀን አሰልጣኞች  ሊጉን ስላጠናቀቅን ያ ለስኬቱ ሊያበቃን ችሏል”።

ለቅ/ጊዮርጊስ ፈታኙ  እና አስደሳች  ስለነበረው የዘንድሮ ጨዋታ

“አርባምንጭን የረታንበት ግጥሚያ  ነበር ከባዱ ፍልሚያችን፤   ያን ጨዋታ እንዳሸነፍንም የውድድር ዘመኑ ሻምፒዮና እንደምንሆን እርግጠኛ ለመሆን ቻልኩኝ”።

ስለ ዘንድሮ  አስከፊ ግጥሚያቸው

“ከፋሲል ከነማ ጋር  ተጫውተን የተሸነፍንበት ነው፤ ያን ዕለት በጣም ተናድጄ ነበር”።

ቅ/ጊዮርጊስ  ከአራት ዓመታት በኋላ ነው ሻምፒዮና ሊሆን የቻለው በቀጣዮ የውድድር ዘመንስ ይህን ስኬት የሚጎናፀፍ ይመስልሃል?

“አዎን፤ ቡድኑ በወጣት እና  ልምድ ባካበቱ ተጨዋቾች የተመሰረተ ነው።  ይህን ስመለከትና  ሌሎች ክለቡን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ልጆችም ስለመጡ  ተከታታይ  ድሉን የሚያገኝ ይመስለኛል”።

በቅ/ጊዮርጊስ  ያለህን የውል ዘመን አጠናቀሃል፤  ከክለቡ ጋር  ስለመቀጠሉ እና  ስለመለያየቱ

“ከባድ ጥያቄ ነው። እነሱ ሊያናግሩኝ ጠርተውኝ እኔ  በአጋጠመኝ አንድ ጉዳይ ላወራቸው አልቻልኩም። ሰሞኑን ግን የምንነጋገርበት አንድ ጉዳይ ስላለ የሚፈጠረውን ነገር አላውቅም”።

የውድድር ዘመኑ ሻምፒዮና  ስትሆኑ የወርቅ ሜዳሊያውን  ለማን እንደሰጠ

“ለማንም አልሰጠውም። ይሄ ሽልማት  የለፋውበት እና የደከምኩበት ስለሆነም በክብር ከእኔም ጋር  ነው ያለው”።

የቅ/ጊዮርጊስን መለያስ ለአድናቂህ  እና ጥያቄ ላቀረበልህ ደጋፊስ ሰጠህ ታውቃለህ?

“ሰጥቼ አላውቅም። የጠየቀኝም የለም። ሲጀመር ማሊያው የተሰጠን ዘንድሮ ነው።  የምንጫወትበት ማሊያም ሶስት  ነው። ይሄ መለያም ለአራት ዓመታት የለፋሁበት ስለሆነም እኔው ጋር ነው ያለው”።

በጅማ  አባጅፋር ቆይታ  ዋንጫ ማንሳትህ ይታወቃል፤  ላለፉት አራት ዓመታት ከቅ/ጊዮርጊስ  ጋር ይህን ስኬት ሳታጣጥም ስትቀር ስለተፈጠረብህ ስሜት

“ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ሳመራ አስቤ  የመጣሁት ዋንጫን ፈልጌ ነበር።  ያም ሆኖ ግን  ከዘንድሮ ውጪ ያለፉትን አራት ዓመታቶች  ይህን ድል ሳላገኝ ስቀር ስሜትን የሚጎዱ ነገሮች ነበሩ። ደግሞም በቅ/ጊዮርጊስ ቤት አይደለም ለአራት ዓመታት  ለአንድ ዓመታት ዋንጫን ስታጣ መጥፎ ጊዜን ነውም ያሳለፍከው ስለሚባል የእዛ ዕጣ ገፈት ቀማሽ ልሆንም ችያለሁ። ያም ሆኖ ግን ከአራት ዓመታት በኋል ይህን ድል ከቡድኑ ጋር ስለተጎናፀፍኩና  ሁለተኛ የሊጉን ዋንጫም ስላገኘው በጣም ነው ደስ ያለኝ”።

ከቅ/ጊዮርጊስ  ጋር  ሻምፒዮና ስትሆኑ የመጀመሪያውን የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክት  ያስተላለፈልህ

“ከባለቤቴ ፂዮን ቴዎድሮስ  ተደውሎልኝ ነበር እንኳን ደስ ያለህ የተባልኩት ይህም ጥሪ ከእሷ ስለመጣ በጣምም ነው ደስ ያለኝ”።

በቅ/ጊዮርጊስ ስለነበረው ያለፉት አራት ዓመታት ቆይታ

“በጣም ደስተኛ  ነበርኩ።  እንደ ግል  ጥሩ ጊዜያቶችንሞ አሳልፌያለሁ። ያም ሆኖ ግን  ክለቡ ሽንፈትን ስላለመደ እና  በምንሸነፍበት እና  ባልተለመደ ሁኔታ  የሻምፒዮናነቱን ክብር ባጣንባቸው ጊዜያቶቾ ደግሞ በጣም ልከፋ ችያለሁ”።

በቤትኪንጉ ሻምፒዮና ሆናችሁ ክለባችሁ ሸልሟችኋል፤ በሽልማቱ ደስተኞች ናችሁ?

“በግሌ እኔ ደስተኛ ነኝ፤ ጥሩም ሽልማት የተሰጠን ይመስለኛል”።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ለየት ባለ ሁኔታ የተመለከተው እና ፕሮሚሲንግ የሆነው  የዘንድሮ ቡድን

“አብዛኛው ተወዳዳሪ ቡድን ይመሳሰላል። ወጥ የሆነ ጨዋታን ያሳየ ቡድንንም አልተመለከትኩም”።

በእዚህ ዓመት የቱ  ተጨዋች  ለአንተ ጥሩ ነበር?

“ጎልቶ ወጥተዋል ብዬ የማስባቸው ጋቶች ፓኖም እና አማኑኤል ወልደሚካኤልን ነው፤ ጥሩ  የውድድር ጊዜያቶችንም ሊያሳልፉ ችለዋል”።

በመጨረሻው ቀን ጨዋታ  ዋንጫ ስለማንሳታቸው

“የውድድር ዘመኑ ሻምፒዮና እንደምንሆን ከነበረን ጥሩ መንፈስ  አኳያ  እና አርባምንጭ ከተማን ካሸነፍንበት ጨዋታም አንስቶ በጣም እርግጠኞች ነበርን።   ያን ድል ደግሞ በተለይ በመጨረሻው ቀን ጨዋታ ላይ ስላገኘን  የውጤት ጣዕሙ ለየት ይልም ነበር”።

ሻምፒዮና በሆኑበት ቀን ተፋላሚያቸው ስለነበረው የአዲስ አበባ ከተማ ቡድን

“በኳስ ቁጥጥር ላይ የተመሰረተ ጨዋታን ነበር ሲያደርጉ  የነበሩት፤  በመጀመሪያዎቹ አስር ደቂቃዎች ላይም ፈትነውናል። ያን  እንቅስቃሴያቸውን በመቋቋም እና ወደ ራሳችንም  የጨዋታ ዘይቤ በማምራትና ግጥሚያውን የማሸነፍ ቁርጠኝነቱም ስለነበር በመጨረሻ የድሉ ውጤት ወደ እኛ  ሊያመራ ችሏልና ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶናል”።

በፍፃሜው ቀን ጨዋታ  እንደ እናንተ የዋንጫ ባለቤትነት  ዕድሉ የነበረው ፋሲል ከነማ በተመሳሳይ ሰዓት ላይ በነበረው ግጥሚያ  አስቀድሞ  ጎል ሲያስቆጥር  እንደ አንድ የቅ/ጊዮርጊስ ቡድን ተጨዋች ሁኔታውን ሰምተካልና በእዚህ ዙሪያ የምትለው  ነገር ካለ

“ያን ቀን ላይ በነበረው ጨዋታ  እኔ በግጥሚያው ላይ ተሳታፊ ባልሆንም የፋሲሎች  አስቀድሞ  ግብ ማግባት ይሰማ ነበር።  የእኛ ልጆች ግን ጠቅላላ ትኩረታቸው  የነበረው ጨዋታው ላይ ስለነበር ብዙ ጎሎችን በማስቆጠር ባለድል ልንሆን ችለናል”።

ቅ/ጊዮርጊስ ወደ ኢንተርናሽናል ጨዋታ ያመራልና በእዛ የውድድር ተሳትፎው ስለሚያመጣው ውጤት

“ከእዚህ በፊት የነበረው ውጤት ይታወቃል።  የአሁኑ የቡድኑ እልም ደግሞ  ክለቡ ጥሩ ጥሩ ተጩዋቾችን ያስፈረመበት ሁኔታ ስላለና ከእኛም ጋር  የበለጠ የምንጠናከርበት  መንገድም ስለሚኖር የምድብ ድልድሉን በመጀመሪያ መቀላቀል እና  ከእዛም ደግሞ  የተሻለ የሚባል ውጤትን ማምጣት መቻልም  ነውና ይሄን ለማሳካት የምንችለውን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን”።

በእዚህ የውድድር ዘመን ስለነበረው ወቅታዊ አቋም  እና ደርሶበት ስለነበረው ጉዳት

“ጉዳቱ የደረሰብኝ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር በነበረው ጨዋታ ነው። የብሽሽት ህመምም ነበር ያጋጠመኝ።  እኔ በጉዳቱ ፈርቼ የነበረ ቢሆንም  ብዙ የከፋ  አልነበረምና  በአሁን ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ ሆኜ  ከተመረጥኩበት የብሄራዊ ቡድን ጋር ልምምዴን እየሰራሁ ነው።  ከእዛ ውጪ የዓመቱን የውድድር ዘመን ቆይታዬን በተመለከተ ጥሩ ጊዜን አሳልፌያለሁ። በእዛም ደስተኛ  ነበርኩ”።

በቅ/ጊዮርጊስ ቡድን ውስጥ የቱ ተጨዋች ለየት ያለ  ባህሪ አለው?

“ሁሉም ተመሳሳይ ነው፤ እንደ ጓደኝነትም ነው የምንተያየው። ወጣ ያለ ባህሪ ያለውን ተጩዋች አልተመለከትኩም”።

የዋልያዎቹ ተመራጭ ተጨዋች ስለመሆንህ

“ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው ይሄ ጥሪ  የደረሰኝ፤  ሶስት ዓመትም ሊሆነኝ  ችሏል። ፈጣሪ ረድቶኝ ለቡድኑ በመመረጤ  በጣም ደስ ሊለኝም ችሏል”።

በቀጣይ የኳስ ህይወትህ የት ጫፍ ላይ እንጠብቅህ

“በእግር ኳሱ ጥሩ ደረጃ ላይ መድረስ ዋናው እልሜ ነው። ለእዛም በተደራራቢ ልምምዶች ጠንክሬ እሰራለሁ፤ ፈጣሪ  እንዲረዳኝ ስለምለነውም   ሁሉንም ነገር በቀጣይነት የምንመለከተው ነው”።

ስለ ቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎች

“እንደሚታወቀው በየሜዳው በመገኘት ይደግፉን ነበር፤ ከዛ ውጪም  በዲ ኤስ ቲቪም ደረጃ ግጥሚያዎችን እየተመለከቱም የሚያበረታቱን  ነበሩና  የድጋፍ ዘይቤያቸው ለየት ይልም ነበር”።

በእግር ኳስ ተጨዋችነትህ ባለቤትህ ስላላት ሚና

“እሷ ሁሌም ከጎኔ ነበረች፤  ስለ ኳስም በደንብ ታውቃለችና ለእኔ የኳስ ተጨዋችነት እዚህ ደረጃ ላይ መድረስም የነበራት ድርሻ በጣም ከፍ ያለም ነበርና ላደረገችልኝ ነገር ሁሉ ከልቤ አመሰግናታለሁ”።

በአፍሪካ ዋንጫው የማጣሪያ ጨዋታ የዋልያዎቹ ተጨዋች ነበርክና ግብፅን ስናሸንፍ ስለነበረህ ስሜት

“ባለድል መሆናችን በጣም ደስ ይላል። ይህ ሊሆን የቻለውም  በእኛ እና በእነሱ መካከል ካለው የኳስ ልዩነት  አኳያ ይሄ ውጤት ይመጣል ብሎ ያሰበ ስላልነበር እና እኛ ደግሞ ውጤት ማምጣት እንደምንችል ያሳየንበት ስለሆነ በጣም ደስ የሚል ስሜት ሊሰማን ችሏል”።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P