Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ለቅዱስ ጊዮርጊስ ለመሰለፍ ያለው ፉክክር ፈታኝ ነው”
ጌታነህ ከበደ (ቅ.ጊዮርጊስ)

#በመሸሻ_ወልዴ

ቅ/ጊዮርጊስ በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና የሶስተኛው ሳምንት ጨዋታው ላይ ሐዋሳ ከተማን 4-1 በማሸነፍ  ደረጃውን ከማሻሻል በተጨማሪ ወደ አሸናፊነት መንፈሱ መመለሱንም በሰሞኑ ጨዋታው ጭምር ሊያረጋግጥ ችሏል፡፡

ቅ/ጊዮርጊስ ከሐዋሳ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ ከተጋጣሚው በተሻለ መልኩ በመቅረብ ባለድል የሆነ ሲሆን ለክለቡ የተገኙትን ግቦችም ሁለቱን አዲሱ የቡድኑ ካፒቴን ጌታነህ ከበደ ቀሪዎቹን ደግሞ የሐዋሳ ከተማው ተጨዋች ዳዊት ታደሰ በራሱ ላይና ሮቢን ንጋላንዴ ሊያስቆጥሩ ችለዋል፤ ለሐዋሳ ደግሞ በባዶ ከመሸነፍ የዳኑበትን ግብ ብሩክ በየነ በፍፁም ቅጣት ምት ሊያስቆጥር በቅቷል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዋሳ ከተማን አሸንፎ ጨዋታውን ካጠናቀቀ በኋላ በጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴ ካሳዩት ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነውን ጌታነህ ከበደን ስለ ዕለቱ ግጥሚያ፣ የድል ግቦችን ስለ ማስቆጠሩ፣ ስለ ካፒቴንነቱ፣ ከሐዋሳ ከተማ ጋር በነበረው ጨዋታ ምርጥ ብቃቱን ስላሳየው አቤል ያለው፤ ስለ ቀጣይ ጨዋታቸው፣ በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ በፋሲል ከነማ ስለደረሰባቸው ሽንፈት፣ ዘንድሮ ስለሚያስመዘግቡት ውጤት እና ሌሎችንም ጥያቄዎች በየተራ የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አንስቶለት ተጨዋቹ ምላሾቹን ሰጥቶባቸዋል፤ ተከታተሉት፡፡
ቅ/ጊዮርጊስ ሐዋሳ ከተማን ድል ስላደረገበት ጨዋታ
“የሁለታችን ጨዋታ ጥሩ እና በእኛ የበላይነት የተጠናቀቀ ግጥሚያ ነበር፤ ያገኘነው  የድል ውጤትም ቡድናችንን ወደ ቀጣይ ጊዜው አሸናፊነታችን ይበልጥ የሚያሸጋግረውም ነውና ይሄ ድልን ማሳካታችን በጣሙን ሊያስደስተን ችሏል”፡፡

ስለ ቤትኪንግ የውድድር ጅማሬያቸው

“የቤትኪንግ የውድድር ተሳትፎአችንን በተመለከተ በሊጉ የመጀመሪያው ጨዋታችን ላይ ትንሽ ለመቸገር ችለን ነበር፤ ይሄ ሊሆን የቻለውም ሊጉ ገና ጅማሬ ላይ ስለሆነ ነበር፤ በአሁን ሰዓት ላይግን ከጨዋታ ወደ ጨዋታ እየተሻሻልንና በፋሲል ከነማም ከደረሰብን ሽንፈት ቶሎም ለማገገም ስለቻልን ወደ ውጤታማነቱ ልናመራ ችለናል፤ እያሳየን ያለነው መሻሻልም ሊደነቅ የሚገባው ነው”፡፡

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ በፋሲል ከነማ ስለደረሰባቸው ሽንፈት

“በፋሲል ከነማ የደረሰብን ሽንፈት ቢያስቆጭም በአንድ በኩል ሲታይ ደግሞ ያለብንን ችግርም ፍንትው አድርጎ ያሳየን ስለሆነም ጥሩ ጎን አለው፤ በዛ ጨዋታ ሽንፈት የተማርነው ነገር ነበር፤ ለዛም ነው በተከታታዮቹ ሁለት ጨዋታዎች ላይ ግጥሚያዎቻችንን በሰፊ ግቦችም ልናስቆጥርም የቻልነው”፡፡

ስለ ጠንካራ እና ደካማ ጎናቸው

“የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮናው ውድድር ገና ጅማሬ እና የሶስተኛው ሳምንት ላይ ስለሆነ አሁን ላይ ስለ ጠንካራና ደካማ ጎን ወይንም ደግሞ ስላለብን ክፍተት ለማውራት ጊዜው ገና ነው፤ በተለይ ደግሞ የሊጉ ጨዋታዎች ብዙም ባልተለመደም መልኩ ጠዋት ላይም እየተካሄደ እና ጠዋታ ላይ መጫወትም ደግሞ ከሚኖረው የአየር ንብረት አኳያም ግጥሚያዎችን አስቸጋሪ የሚያደርግበትም ሁኔታዎች ስላሉ ሊጉ እየተጧጧፈ ሲሄድ ስለ ቡድናችን ብዙ ነገሮችን ማለትም ይቻላል”፡፡

ለቅ/ጊዮርጊስ የድል ጎሎችን ማስቆጠር ስለመጀመሩ

“በአጥቂው ስፍራ ላይ ካለኝ ስምና ዝና አንፃር እንደዚሁም ደግሞ ለቡድኔ ከምጫወትበት የ9 ቁጥር ሚና አኳያ ሁሌም ቢሆን ከእኔ ጎሎች እንደሚጠበቅ አውቃለውና ከሐዋሳ ከተማ ጋር በተደረገው ጨዋታ ቡድናችን 4-1 ሲያሸንፍ ሁለት የድል ጎሎችን በማስቆጠር መልካም የሆነ ጅማሬን ማድረጌን ወደጄዋለሁ፤ ግቦቹን ማስቆጠሬም ለቡድኔ የሚፈጥርለት ብዙ ጎን አለው፤ በእዚህ ዓመትም ከእዚሁ በመነሳት በርካታ ግቦችን እንደማስቆጥርም በራሴ እተማመናለው”፡፡

ቅ/ጊዮርጊስን በካፒቴንነት ስለመምራቱ እና ካፒቴን ሆኖም ጎል ስለማስቆጠሩ

“በቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ታሪክ ብዙ ስመ ጥር ተጨዋቾች ያላገኙትን የካፒቴንነትን ማዕረግ እድል እኔ አግኝቼው ቡድኑን በጥሩ መልኩ ልመራው ስለቻልኩና ካፒቴን ሆኜም በተጫወትኩበት ጨዋታ ላይ ሁለት የድል ግቦችን ለእዚህ ታሪካዊ ቡድን ላስቆጥር ስለቻልኩ የተሰማኝን ደስታ በቃላት ብቻ የምገልፀው አይደለም”፡፡

ለቅ/ጊዮርጊስ ውጤታማነት ኳሶችን በማቀበል ምርጥ ብቃቱን ስላሳየው አቤል ያለው

“ሐዋሳ ከተማን ድል ባደረግንበት ጨዋታ አቤል ያለው የነበረው ሚናና አስተዋፅኦ በጣም ጥሩ እና ከሁሉም ተጨዋቾችም ከፍ ያለ ነበር፤ ለጎሎቹ መገኘት ሁሉ የእሱ ድርሻም በጉልህ የሚጠቀስም ነበርና ይሄን ስመለከት ከአቤል ጋር በደደቢት ክለብ አብረንም ተጫውተን ቆይተን ነበርና ከጊዜ ወደ ጊዜ ራሱን በጣም እያሻሻለ መሄድኑም በየጨዋታዎቹ ላይ ሊያሳይ ችሏል፤ ካለው ብቃት አኳያም ከሀገር ወጥቶ ለመጫወት ስለሚችል በእዚሁ ሊቀጥልም ነው የሚገባው”፡፡

ከሐዋሳ ከተማ ጋር በነበራቸው ጨዋታ ስለ ተጋጣሚያቸው ቡድን አቋም

“የሐዋሳ ከተማን አቋም በተመለከተ ከተጨዋቾቹ የልምድ ማነስ ካልሆነ በስተቀር ጥሩ ቡድን ነው ያለቸው፤ በዛ ላይ አሰልጣኙም ገና ወጣት ነው፤ ጊዜ የሚፈልግ ቡድንም ነው፤ በእንቅስቃሴ ደረጃ ሌላ መጥፎ የሚባል ነገርን አልተመለከትኩባቸውም”፡፡

ከአጥቂነቱ ባሻገር በጥልቀት ወደ ኋላ ተስቦም ስለመጫወቱ

“ከቅ/ጊዮርጊስ ተጨዋችነቴ ባሻገር ለብሔራዊ ቡድንም ስጫወት በእዚህ መልኩ የምጫወትበት እንቅስቃሴው አለኝ፤ ይሄን የማደርገው አንድ አንዴ ኳስ ቶሎ ሳይመጣ ሲቀር ከኋላ ኳሱን መስርተነው በመጫወት ወደተጋጣሚ ቡድን የሜዳ ክልል በፍጥነት እንድንገባ ከመፈለግም ነው”፡፡

ቅ/ጊዮርጊስን በአዲስ መልክ ስለተቀላቀሉት ተጨዋቾች እና ስለ ቡድኑ የተጨዋቾች ስብስብ

“ዘንድሮ ወደ እኛ ቡድን የመጡት አዲስ ግደይ፣ ከነዓን ማርክነህ እና አማኑኤል ገ/ሚካሄል ቀደም ሲል በነበሩበት ክለብ በየጨዋታው እንቅስቃሴ ለቡድናቸው ውጤት ማማር ትልቅ አስተዋፅኦን ያደረጉና ከፍተኛ ስምም ያላቸው ተጨዋቾች ናቸውና ወደ እኛ ቡድን መምጣታቸው ቀደም ሲል የነበሩብንን አንድ አንድ ክፍተቶቻችንን እንድንሸፍንበት እና ለቡድኑ ለመሰለፍም ለሚኖረው ፉክክርም መልካም ነገርንም ያስገኝልናልና ወደ ሜዳ ለመግባት ዘንድሮ ፉክክሩን አይጣል ነው የሚያደርገው፤ ከእዛ ውጪም የእነዚህ ተጨዋቾች ዘንድሮ ቡድኑን ተቀላቅለው አሁን ላይ ቡድኑን በሚገባ እየተዋሀዱም መሆኑም ለእኛ ጥሩ ነገርም ነው፤ እንደ አጠቃላይ ደግሞ ክለባችን ስላለው የተጨዋቾች ስብስብ ካነሳው ደግሞ በቂና ሙሉ የሆነ ቡድን ቅ/ጊዮርጊስ አለው፤ በጉዳት ላይ የነበሩት እነ አስቻለው ታመነ እና ሳላህዲን ባርጌቾም አገግመው ልምምዳቸውን እየሰሩ ነው፤ ሌላው ከክለቡ በጉዳት ከዓመት በላይ ርቆ የነበረው ናትናሄል ዘለቀም ድኖ ወደ ክለቡ የተመለሰበት እና ቡድኑንም የተቀላቀለበት ሁኔታ ስላለ በስብስብ ደረጃ አስፈሪውን ቡድን ነው ዘንድሮ ይዘን የቀረብነው”፡፡

ቅ/ጊዮርጊስ ምርጥ የተጨዋቾች ስብስብ ቢኖረውም ምርጥ አሰልጣኝ ግን የለውም የሚሉ አሉ

“እንደ እኔ እምነት ይሄን አልቀበለውም፤ አሁን ያለው አሰልጣኝም ጥሩ ነው፤ በዛ ላይ ገና ወጣትም ነው፤ ጥሩ ስራን እያሰራንም ይገኛል”፡፡

ቅ/ጊዮርጊስ በቀጣይነት ስለሚያደርገው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታው

“ተጋጣሚያችን ሰበታ ከተማ ነው፤ በእዚህ ሳምንት አርፎም ነው እኛን የሚፋለምን፤ ከእነሱ ጋር ስለሚኖረን ጨዋታ አሁን ላይ ብዙ የምለው ነገር የለም፤ ያም ሆኖ ግን ይሄን ጨዋታ እንደ አንድ ከሌላ ቡድን ጋር እንደምናደርገው ጨዋታ በመመልከት እና አሁን የያዝነውንም የጨዋታ ሪትምም በማስቀጠል ከግጥሚያው የሚጠበቀውን ሶስት ነጥብ ይዘን ለመውጣት ከፍተኛ ጥረትን እናደርጋለን”፡፡

ለቅ/ጊዮርጊስ በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና የትኛው ቡድን ስጋት ይሆንበታል? ማንስ ያቆመዋል?

“ለእኛ ማንም ቡድን ስጋት አይሆንብንም፤ ይሄን ደግሞ ከሊጉ ስድስት እና ሰባት ጨዋታዎች በኋላም የክለቦችን አቋም በደንብ እያወቅን የምንሄድበት ወቅት ስላለ ያኔ ሁሉን ነገር እናውቀዋለን፤ ከዛ ውጪም አሁን ላይ ሊጉን ማሸነፍ ስለጀመርንና ቡድናችን ደግሞ አንዴ ማሸነፍ ከጀመረና ወደ አሸናፊነቱም ከመጣ ማንም አያቆመውምና ያንንም ነው እየተጠባበቅን ያለነው”፡፡

ቅ/ጊዮርጊስ በርካታ የድል ግቦችን በማስቆጠር እያሸነፈ ስለመምጣቱ

“ይሄ የሚያሳየው ከሁሉም በላይ ጠንካራና ውጤታማ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋቾች ቡድኑ እንዳሉት ነው፤ ከዛም ውጩ በሁሉም ቦታ ላይም ጠንካራ ተጨዋቾች ስላሉን በማጥቃቱም በመከላከሉም ላይ የተሻለ ነገርን ሰርተን መምጣታችንን ያሳያል”፡፡

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ማን በበላይነት ያጠናቅቃል?

“ቅ/ጊዮርጊስ ካሉት ነባርና ጥሩ ተጨዋቾች ውጪ ከተለያዩ ቡድኖች ሌሎች ጠቃሚ ተጨዋቾችን ሊያመጣ የፈለገው ባለፉት ዓመታት በክለቡ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ያጣውን ዋንጫ ዳግም   ማግኘት ስለሚፈልግ ነውና የዘንድሮውን ዋንጫ በእርግጠኝነት የምናነሳው እኛ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ነን፤ ይሄን ለማሳካትም ነው የአሁን ሰዓት ላይ ራሳችንን ከኮቪድ ወረርሽኝ ለመጠበቅ ጭምር መቀመጫችንን በቢሾፍቱ አካዳሚ በማድረግና  ከሆቴልም ባለመምጣት የእዚህ ዓመት ስኬታማነታችንን እየተጠባበቅን የምንገኘው”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P