“ለቡንዬ እሮጣለሁ” 3ኛው የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰብ ሩጫ ተካሄደ
በ2007 ዓ.ም የተጀመረው የኢትዮጵያ ቡና የቤተሰብ ሩጫ ዘንድሮ ለ3ኛ ግዜ ሲካሄድ እንደቀደሙት ግዚያት መነሻ እና መድረሻውን ለቡ በማድረግ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ።
ከ25 ሺህ በላይ የቡና ደጋፊዎች በተሳተፉበት
ሩጫ 8ኪ/ሜ የሸፈነ ሲሆን ውድድሩን የክለቡ ኘሬዝዳንት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ እና በእለቱ ተጋባዥ የነበሩ አንግዶቸች ውድድሩን አስጀምረዋል። በውድድሩ ላይ ከቲሸርት ሽያጭ ከ6.5 ሚሊየን ብር በላይ እንደተገኘ ተገልጿል።
የተገኘው ገቢ ክለቡ ስታድየም ለማስገንባት ላሰበው አላማ እንደሚውል ታውቋል።