Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ለቡድኔ ውጤታማነት በእልህ የምጫወት እንጂ ነውጠኛ የምባል አይነት ተጨዋች አይደለውም፤ ከዚህ በፊት አጥፍተሃል ካላችሁኝም ይቅርታ”



በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/


በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታ አዳማ ከተማ ወልቂጤ ከተማን በከነዓን ማርክነህ እና ተቀይሮ በገባው በረከት ደስታ ሁለት ግቦች 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፤ ለአዳማ ከተማ በሊጉ የውድድር ተሳትፎዎች ጥሩ እንቅስቃሴ በማሳየት የሚታወቀው ወጣቱ ተጨዋች በረከት ደስታ ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ ጋር በክለባቸው የውድድር ተሳትፎ ዙሪያና ስለራሱ የሜዳ ላይ ብቃት ቆይታን አድርጎ ነበርና ምላሹ በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፡፡
ወልቂጤ ከተማን ድል ስለደረጉበት ጨዋታ እና ተቀይሮ በመግባት ጎል ስለማስቆጠሩ
“ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያደረግነውን ጨዋታ በተጠባባቂ ወንበር ላይ ሆኜ መጀመሪያ እንደተመለከትኩት በእንቅስቃሴው በኩል ጥሩ ነበርን ወደፊት ልናጠቃም ስንሄድ መልካም ነበርን ያም ሆኖ ግን በእዛ መልኩ እየተጫወትን ሳለ የምናገኛቸውን የግብ እድሎች አለመጠቀማችን የሚያስቆጭ ነበር፤ ከዛ ውጪ ሌላ ያየሁት ነገር ቢኖር እኔ ተቀይሬ ከገባው በኋላ የእነሱ ተከላካዮች ወደፊት ገፍተው ይወጡ ስለነበርና ለእኛ ያለን አማራጭ ደግሞ በረጅሙ ተጫውተንና በፍጥነትም አምልጠን ተጨማሪ ግብ ማስቆጠር ይኖርብን ነበርና በእዛ መልኩ በመንቀሳቀስ ለክለቤ ሁለተኛውን የድል ግብ አስቆጥሬ ለአሸናፊነት ልንበቃ ችለናል፤ በማሸነፋችንም በጣም ደስ ብሎኛል”፡፡
ለአዳማ ከተማ ተቀይረህ ስትገባ ጥሩ ለመንቀሳቀስ ችለሃል፤ ጥሩ ጎል ከማስቆጠርህ ባሻገር ለጎል የሚሆን ኳስም ለማቀበል ሞክረሃል፤ የጨዋታው ልዩነት ፈጣሪ አንተ ነበርክ ማለት ይቻላል?
“ኸረ! በፍፁም፤ ልዩነት ፈጣሪው እኔ ሳልሆን መጀመሪያ ሜዳ ላይ የነበሩትና ለቡድናችን የተሰለፉት ተጨዋቾች ናቸው፤ እኔ ደግሞ የግቡን መጠን ሰፋ ያደረግኩት ተጨዋች ነኝ፤ ከዛ ውጪም ደግሞ በዕለቱ ፍልሚያ ወደሜዳ ገብቼም ከቡድኔ ተጨዋቾች ጋር ጥሩ በመንቀሳቀስ ለቡድኔም ውጤታማነት የሚቻለኝን ሁሉ ጥረትም ያደረግኩ ተጨዋች ነበኝ”፡፡
ለአዳማ ከተማ ሁለተኛ የሆነችዋን የድል ግብ ያስቆጠርክበትን መንገድ እንዴት ትገልፃታለህ?
“በመጀመሪያ ከዛ በፊት ማለት የምፈልገው ነገር ቢኖር ለአዳማ ከተማ ጎል ካስቆጠርኩ ስምንት ሳምንት ስላለፈኝ ግቧን እንዳስቆጠርኩ በጣም መደሰቴን ነው፤ ግቧን ያገባውበት መንገድ ደግሞ ከላይም ገልጬዋለው የእነሱ ተከላካዮች ወደፊት ገፍተው ለመጫወት ይሞክሩ ስለነበር ልክ ከጓደኛዬ ኳሱን እንደተቀበልኩ ያለኝን ፍጥነትና የኳስ ብቃቴን ተጠቅሜ ነው ጎሏን ላስቆጥር የቻልኩት፤ ከዚ በኋላም እንግዲህ ወደ ጎል ማስቆጠሩ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረትንም አደርጋለው”፡፡
በአዳማ ከተማ ክለብ ውስጥ በአሁን ሰዓት ስላለህ ወቅታዊ አቋምና ከወልቂጤ ጋር በነበረው ጨዋታ ተጠባባቂ ስለመሆኑ
“በአዳማ ከተማ ክለብ ውስጥ ስጫወት ያለኝ ወቅታዊ አቋም በጣም ጥሩ ነው፤ ለቡድኔም በበርካታ ጨዋታዎች ላይ በመሰለፍም ነው እስካሁን ስጓዝም የነበርኩት፤ በሐሙሱ ከወልቂጤ ከተማ ጋር በነበረን ጨዋታ ደግሞ የተጠባባቂ ተጨዋች የነበርኩት በብዙ ጨዋታዎች ላይ ስለተሰለፍኩና ጉልበት እንዳላባክንም በሚል እንዳርፍም በመፈለጉ ነበር፤ በኋላ ላይ ግን ካለኝ ወቅታዊ አቋም ተነስቶ አሰልጣኙ ቀይሮ አስገባኝና ለቡድኔ ጥሩ ነገርን ልሰራ ችያለው”፡፡
ወልቂጤ ከተማን በጨዋታው ላይ እንደተመለከትካቸው
“በጣም ጠንካራ እና ጥሩ ስብስብ ያላቸው ናቸው፤ በተለይ ደግሞ ፊት መስመራቸውም በጣም ያስፈራል፤ ፈጣን ልጆችም አላቸው፤ ልምድ ያላቸውም አይመስሉም፤ ጥሩ ነገርን ተመልክቼባቸዋለው”፡፡
አዳማ ከተማ ዋንጫ የሚናፍቅ ቡድን ነው፤ አሁን ላይ እያስመዘገበ ያለው ውጤት ቡድኑን ይመጥነዋል
‘‘እንዳለን የተጨዋቾች ስብስብ ውጤቱ እኛን ፈፅሞ አይመጥነንም፤ ውጤት ያሳጣንም ክለባችን ጋር በነበረው ከደመወዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ ያለው ችግር ነው፤ አሁን ላይ ግን እነዛን ችግሮቻችንን ተቋቁመን ጥሩ ውጤት ለማምጣት እየሞከርን ነው”፡፡
የፕሪምየር ሊጉን ፉክክር በተመለከተ እና አዳማ ከተማስ ምን ውጤት እንደሚያመጣ ምን ትላለህ?
“ፉክክሩ አብዛኛው ቡድኖች በተቀራረበ ነጥብ ላይ ስለሚገኙ እና አንድ ጨዋታን ስታሸንፍም ብዙ ደረጃን የምታሻሽልበት ስለሆነ ጥሩ ነው፤ ክለባችን የሚያመጣውን ውጤት በተመለከተ ደግሞ አሁን ላይ በስነ-ልቦና ደረጃ በጥሩ ሁኔታ ላይ ስለምንገኝና በሊጉ መቋረጥም እረፍቱ ለመረጋጋት የሚጠቅመንም ስለሆነ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘን እናጠናቅቃለን”፡፡
በአዳማ ከተማ ውስጥ ስላለው ወቅታዊ አቋም
“በአሁን ሰዓት ለክለቤ ሳልቀየር ጭምር ጥሩ እየተጫወትኩበት ያለ ሁኔታ በመኖሩ በጥሩ አቋም ላይ ነው የምገኘው፤ ያም ቢሆን ግን ይሄ ብቻ በቂ አይደለምና ለብሔራዊ ቡድን የሚያስመርጠኝንም ብቃት ይዤ ለመምጣትም ተዘጋጅቻለው”፡፡
በረከት በሜዳ ላይ ጥሩ ችሎታና አቅም አለው፤ በባህሪው ግን በጣም አስቸጋሪና ነውጠኛም ነህ ይሉሃል..በዚህ ዙሪያ ምን ትላለህ?
“እኔንጃ፤ ብዙ ሰው እንደዛ ይለኛል፤ በተለይ ደግሞ አዲስ አበባ ላይ መጥተን ስንጫወት የቅዱስ ጊዮርጊስም ሆኑ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች በዛ መልኩም ያስቡኛል፤ እኔ ግን እንደዛ አይነት ተጨዋች አይደለውም፤ ሜዳ ስገባ ሁሌም አንድ ተጨዋች ለቡድኑ አሸናፊነት ሲል እንደሚከፍለው መስዋዕትነት ነው እኔም ያንን ከፍዬ የምጫወተው፤ ያንን ሳደርግ ከተመልካቹ ተቋውሞ የሚደርስብኝም የእህለኝነት ስሜትን ይዤ በሜዳ ላይ ስለምጫወትም ነው፤ ያኔ እንደነውጠኛ ተጨዋችም የምቆጠረው ከእነሱ ቡድን ጋር ስንጫወትና ከተጨዋቾቹም ጋር ተጋፍጬ በምጫወትበት ጊዜ ላለመሸነፍ በማደርገው ጥረት በሌላ መልኩ ስለሚያዩኝም ነው፤ ይሄ ሁኔታ ለመጀመሪያ ጊዜ የገጠመኝ ደግሞ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ስንጫወትና አንድ ለዜሮ ከመራናቸው በኋላ እነሱ ባለቀ ሰዓት የአቻነቱን ግብ ሲያስቆጥሩና ከዛም የእኛ ቡድን ኮርና ባገኘበት ጊዜ ሰዓቱም እያለቀ ነበርና እነሱ እንዲረጋጉ ስል ቀስ ብዬ ኮርናውን ለመምታት በምሄድበት ሰዓት ለምን ቶሎ አይመታም በሚል ደጋፊው ሲቃወመኝና ድንጋይም ወርውረው በመቱኝ ሰዓት አልመታም በሚል ሌላ ተጨዋቻችን እንዲመታ ባደረግኩበት ጊዜ ከተፈጠረው አጋጣሚ ጊዜ አንስቶ ነው፤ እኔ ያደረግኩት ነገር ለቡድኔ ውጤት እስከሆነ ድረስ ልክ ነበርኩ፤ ይሄን የማንም ቡድን ተጨዋች የሚያደርገውም ነበር፤ በዛ ጨዋታ እኔ ሌላ ዓላማ ፈፅሞ አልነበረኝም፤ ደጋፊን ከደጋፊም እንዲጣላም ጥረት አላደረግኩም፤ ግን ከዛ ጊዜ አንስቶ ነው እኔ ወደሜዳ ገብቼ በእልህ በተጫወትኩባቸው እና ቡድኔን ለድል ለማብቃትም ጥረትን በማደርግባቸው የቅዱስ ጊዮርጊስና የቡና ጨዋታዎች ሁሉ ተቃውሞ የሚቀርብብኝ፤ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማሃል ወይ ለተባልኩት ሜዳ ስገባ ሁሌም በእልህ ነው የምጫወተው፤ አንድአንዴ ከተጨዋች ጋር ኳስ ንክኪ ያለው ጨዋታ ነውና መጋጨት ይኖራል፤ ያኔም ተመልካቹ ሊቃወመኝ ይችላልና የጥፋተኝነት ስሜት የሚሰማኝ ጊዜ አለ፤ ያኔም ተጨዋቹን ይቅርታ እላለው፤ የእግር ኳስ ተመልካቹን አስቀይሜ ከሆነም ይቅርታን እጠይቃለው”፡፡
በእግር ኳስ ህይወትህ ደስተኛ ነህ
“በጣም ደስተኛ ነኝ”፡፡
የተከፋህበትስ
“በ2010 ላይ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት እንችል ነበር፤ አምስት ጨዋታ እየቀረንም ሊጉን እየመራን ነበር፤ ያም ሆኖ ግን በቢሮ ደረጃ በተፈጠሩት ችግሮች ያንን ዋንጫ ማጣታችን እኛን ተጨዋቾች በጣም ያስቆጨናል”፡፡
በመጨረሻ…
“በእግር ኳስ ህይወቴ ለእዚህ ደረጃ እንድደርስ በቅድሚያ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን እኔን ወደዋና ቡድን ከማሳደግ ባሻገር ብዙ የመጫወት እድሉንም ሰጥቶኛልና በጣም አመሰግነዋለው፤ ከእሱ በፊት ደግሞ ፈጣሪዬን፤ ሌሎቹ የማመሰግናቸው ደግሞ ዳዊት ታደለን፣ ነኮቻን፣ አስቻለውን፣ ደጉን እንደዚሁም ደግሞ ሌሎች ያሰለጠኑኝም አሰልጣኖችና ቤተሰቦቼም ብዙ ነገር ያደረጉልኝ ስለሆኑ እነሱም ይመሰገናሉ”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P