Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አይደለም ተጫውተህ ደጋፊ ሆነህ ራሱ ያለው ስሜት ቀላል አይደለም” “ኢትዮጵያ ቡና አመቱ መጀመሪያ ላይ ቡድኑን ስላልሰራ ነው ዘንድሮ ውጤት ያጣው”  አላዛር ሽመልስ /ኢትዮጵያ ቡና/

 

የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና በብሄራዊ ቡድናችን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ምክንያት ከተቋረጠ በኋላ  ውድድሩ ዳግም የተመለሰ ሲሆን በእዚሁም መሰረት የአሰልጣኝ ካሳዬ አራጌው ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚውን አዳማ ከተማን 2-1 ሊረታ ችሏል።  የእነዚህ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የአዳማው አሜ መሀመድ በጊዜ ባስቆጠረው ግብ አዳማዎች 1-0 ለመምራት ቢችሉም በዕለቱ ግጥሚያ ምርጥ ብቃቱን ያሳየው  የአቡበከር ናስር ሁለት ግቦች ኢትዮጵያ ቡናዎችን አሸናፊ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን ድል ባደረገበት ጨዋታ ለአቡበከር ናስር ሁለት ግቦች አላዛር ሽመልስ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል የተዋጣለት ብቃቱን ያስመለከተን ሲሆን  ይህን ተጨዋች የሊግ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/  በድሉ ዙሪያ እና ሌሎችንም ጥያቄዎች አቅርቦለት ተከታዩን ምላሽ ሰጥቶናል። መልካም ንባብ።

ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ከተቋረጠ በኋላ ዳግሞ ሲጀመር ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን አሸንፎ ባለ ድል ሆኗል፤ የድሉ ስሜት ምን ይመስላል? ስለ ጨዋታውስ ምን የምትለው ነገር አለ?

“ጨዋታውን በማሸነፋችን በጣም ደስ ይላል፤ ከሲዳማ ቡና ጋር በነጥብ በመጋራትም ወደ ሶስተኝነቱም መጥተናል። ከእነሱ ጋር ያለን ልዩነት የግብ ብቻም ነው። አሁንም ሁለተኛ የመሆን ዕድልም አለን፤ ቡናን ለእዛ ደረጃ ለማብቃትም እንታገላለን።  ወደ ግጥሚያው ሳመራ በመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታው እንደተጀመረ ቅድሚያ ጎል ስለተቆጠረብን ትንሽ ተዘናግተን ነበር።  ወዲያው ግን ከደቂቃ ወደ ደቂቃ ስናመራ ብዙ መሻሻሎችን አድርገን በኳስ ቁጥጥሩ የተሻልን ሆንን። እነሱ ደግሞ ወደ መዳከሙ አመሩ። በእዚህ ጊዜ ውስጥም እኛ ያገኘናቸውን የግብ አጋጣሚዎች መጠቀም ብንችል ኖሮ  ከእረፍት በፊትም ውጤቱን መምራት እንችል ነበር።  ወደ ሁለተኛው አጋማሽ ስናመራ ደግሞ ከመጀመሪያው አጋማሽ በጣም የተሻልን ነበርን። ብዙ ወደ ጎል ጋር እንደርስ ነበር። በኳስ ቁጥጥሩም የተሻልን ነበርን።  በአቡበከር ናስር አስደናቂ ግቦች ግጥሚያውን ስለ ረታን የመጣው የድል ውጤት የሚገባንም ነው”።

በአዳማ ከተማዎች የመሪነቱ ግብ በጊዜ ሲቆጠርባቸው የነበራቸው ስሜት

“ትንሽ የመዘናጋት ስሜት ነው የተፈጠረብን፤ ይህ ሁኔታ ሊደጋገምብንም ችሏል። ይህ ሁኔታ ደግሞ የቡድንን ስሜትም ይረብሻል።  ያም ሆኖ ግን በእዚህ ጨዋታ ላይ ራሳችንን ወደ ኋላ በመመልከት እና  ከመመራትም ተነስተን እናሸንፋለንም ወደሚል መንፈስ ስላመራን ጨዋታውን በድል ለመወጣት ችለናል”።

ስለ ተጋጣሚያቸው አዳማ ከተማ

“አዳማ  ከፈቀድክላቸው ኳስ የሚጫወት ቡድን ነው። ኳስን ይዘው የመጫወት  ሀሳቡም አላቸው። ጥሩም ቡድን ነው። ዛሬ ግን እኛ በመንጠቁ በኩል እና ኳስን ተጭነን ስንጫወት የተሻልን ስለነበርን  አሸንፈናቸዋል”።

ለኢትዮጵያ ቡና ሁለቱን  ግቦች ስላስቆጠረው አቡበከር ናስር

“አቡኪ በክለብም ሆነ ለብሄራዊ ቡድን እያሳየ ባለው ብቃት፣ የጎል ማስቆጠር ችሎታው የታክቲክ አረዳዱ እንደዚሁም ደግሞ ስብዕናው ለኢትዮጵያ አብዛኛው  ታዳጊዎች  አርአያ /ተምሳሌት/ የሆነ ተጨዋችም ነው። ከእሱ ጋር በመጫወቴም ዕድለኛ ነኝ፤  ከእሱ ውጪ ኳሱን ከእነ ታፈሰ ሰለሞን  ጋርም ሆነ ስትጫወት አንተም እድገቱ ይኖርሃል። የእነሱን ምክር ስትሰማም ደስ ይላልና  እኔ ብዙ ነገሮችን እየተማርኩኝ ነው”።

አዳማ ከተማን ባሸነፋችሁበት ጨዋታ ጥሩ ስለ መንቀሳቀሱና አቡበከር ላስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ምክንያት ስለመሆኑ

“የመጀመሪያውን ግብ ስናስቆጥር  ለአቡበከር ያቀበልኩት በተሻለ የቦታ አቋቋም ላይ ስለነበርና ያለውን ጎል የማስቆጠር ችሎታውን  ስለማውቅ  ነው፤ እንዳቀበልኩትም ግቧን በቀላሉ አስቆጥሯታል፤ የሁለተኛውን ግብ በተመለከተ ደግሞ ብዙዎች ግቧን እኔ ማስቆጠር እንደምችል ግምታቸውን ሲያስቀምጡ ስምቻለሁ፤ ያም ሆኖ ግን ኳሷ ወደ እኔ ጋር ስትመጣ የመዘግየት ሁኔታ ስለነበራት ነው  እኔ መትቼ ከምሞክራት እና  ለማስቆጠር ከምጥር  ይልቅ በጥሩ የቦታ አቋቋም ላይ የሚገኘው አቡበከር ናስር እንዲያስቆጥር በመፈለግ ኳሷን ላቀብለው የቻልኩ፤ በእግር ኳስ ደግሞ ብዙ ጊዜ እኔን የሚያስደስተኝ ራሴ ጎል ከማስቆጥር ይልቅ ለጓደኞቼ ሳቀብል ነውና  ይሄ ነው የእኔ መለያዬም”።

በኢትዮጵያ  ቡና ውስጥ አሁን ያለህን አበረታች የኳስ ጅማሬ የት ድረስ ለመውሰድ እንደተዘጋጀ

“እነ አቡበከር ናስር እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱበትን መንገድ በመከተል እና እነሱንም ቀርቦ በመጠየቅ ከዛ ውጪም አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ለተጨዋቾች ግልፅ ሰው ስለሆነ እና  ለምትጠይቀው ነገር ሁሉ  መልካም የሆነ ምላሽን በመስጠት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ወደፊት ጥሩ ነገር ይኖረኛል ብዬ አስባለውኝ”።

ለኢትዮጵያ ቡና መጫወት ስላለው ስሜት

“የኢትዮጵያ ቡና ማለት ለእኔ በልጅነቴ ጀምሮ ሰፈሬ ኳስ ሜዳ  አበበ ቢቂላ አካባቢ ስለነበር ቡድኑን ለመደገፍ ወደዛ አመራ ነበር። ካለቀ በኋላም ተጨዋቾቹን ሰርቪስ ውስጥ እስኪገቡ  ለማየት በሩ ላይ እንቆምም ነበር። ያኔ  ደጋፊ ሆኜ ያየሁትን ነገር ዛሬ ላይ በተጨዋችነት ስመለከተው ለቡድኑ መጫወት በጣም ነው ደስ የሚለው፤  ክለቡ ታሪካዊም ነው። የትም ሄደህ ስትጫወት ደጋፊው ከአንተ ጋር ሆኖ  ያበረታታካል፤ ስምህን እየጠራም  ይዘምርልሃል።  ለእዚህ የቡድኑ ማሊያ ብዙ ሰው ተዋድቆለታል። በእነሱ ፊት ስትጫወትም ደስታው የተለየ ስሜትንም ይሰጣልና ቡናን ለእዚህም  ነው እንድትወደው የሚያደርግህ”።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብፅን ካሸነፈ በኋላ የቡድኑን መለያ ለብሶ ስለመጫወት በውስጥህ ምን አይነት ስሜት አቃጨለብህ

“ኢትዮጵያ ስትባል ብዙ ባህል እና ብሄር  ያላት ሀገር ናት፤  መተሳሰብና አንድነትም አላት።  ከማንም ልታወዳድራት የማትችልም ሀገር ናት።  ይሄን ስታይ በተለይ ግብፅን ካሸነፉ በኋላ መለያዋን አድርጎ ስለመጫወት ብዙ ነው የምትመኘው። ከግብፅ ጋር በነበረው ጨዋታ እኛ እነሱን ስናሸንፋቸው ኳሱን ከጓደኞቼ ጋር  ተሰብስበን እያየን ነበርና በፍፁም አላመንም። እነ አቡበከር ኳሱን ከእነሱ ላይ ሲነጥቁ  ስትመለከት እና  በከፍተኛ ፍላጎት ሲጫወቱ ስታይ የያዙትን የኳስ ብልጫ ጨምሮ  በጣም ነበር ደስ ያለኝ። የመጨረሻዋ ፊሽካ ሲነፋም ውጤቱን ካለማመን በጣም ጨንቆን እና ደስ ብሎንም ነበር የጨፈርነው። ይሄ ውጤትም አይደለም የቡድኑ ተጨዋች ሆነህ ደጋፊ ሆነህ ራሱ  ልክ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ዋልያዎቹን ከ31 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ሲያሳልፋቸው  እንደነበረው አይነት የደስታ ስሜትም ነው ሊሰማኝ የቻለው፤ ምክንያቱም ግብፆች ለእኛ ያላቸው ንቀት አለ። ከዛ በመነሳት እነሱን ተጭነን /ዶሚኔት አድርገን/ ቡድኑን ቡድን አስመስለሁት ሲወጡ በጣም ነው ያስደሰተኝና እኔም እነ አቡበከር ያደረጉትን አይነት ነገር ማድረግ እፈልጋለሁ። በብሄራዊ ቡድን የእግር ኳስ ደረጃ እንኳን እየተጫወትክ አይደለም ደጋፊ እንኳን ሆነህ እንዲህ ያለ ድልን ስትቀዳጅ ስሜቱ ቀላል አይደለም። እነ አቡበከር ያደረጉትን ማድረግ እፈልጋለሁ ፤ ከእነ አቡበከር በመቀጠል ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርግ ተጨዋች መሆንም እፈልጋለሁ። አሁን ላይ እኛ በእግር ኳሱ ታላላቅ ከሚባሉት ሀገራት አናንስም። ከሰራንና ከተተጋገዝን የትም መድረስም እንችላለን። የእኛ ተጨዋቾች ያሳዩንም ይሄን ነው። ሌሎቹ በስም ነው እንጂ የተሻለ ነገር እኛ ጋር አለ፤ እግር ኳሱ ላይ በህብረት ከሰራን ከግብፅ አይደለም ነገ ከአውሮፓ ካሉት ሀገራት  ጋር መፎካከር የምንችልበት እድሉ ይኖረናል”።

ቤትኪንጉ የአራት ሳምንት የጨዋታ መርሀ ግብር ይቀረዋል፤  ምን ውጤትን ማስመዝገብ ነው እቅዳችሁ?

“እኛ ከዋንጫው ፉክክር መውጣታችን ይታወሳል። ከእዚህ በኋላ ውጤቱ  እንደ ትልቅ ክለብነቱ  ለቡና ባይመጥንም  ሁለተኛ  ወጥተን  ለኮንፌዴሬሽን ካፕ ለማለፍ እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ እንታገላለን”።

ኢትዮጵያ  ቡና  ሁለተኛ ሆኖ ለመጨረስ  ከፊቱ ያሉት ቡድኖች  ነጥብ ሊጥሉለት እና ራሱም ግጥሚያዎችን ማሸነፍ ይኖርበታል፤  ይሄ  ባይሳካስ?

“እንደያዝነው የተጨዋቾች ስብስብ ሶስተኛ ሆነን መጨረስም ለእኛ ውጤቱ በቂ ነው።  ቡና ቤት ግን ይህ ሁኔታ ፈፅሞ አይታይም፤ በየቱም የተጨዋቾች ስብስብ /ስኳዱ/ ውስጥ ግባ ውጤት ማምጣት ግድ ነው። ያም ሆኖ ግን የዓመቱ መጀመሪያ ላይ ቡድኑ በደንብ ተደርጎ ስላልተሰራ ይሄም ማለት የተጨዋቾች ስብስቡ ልምድ ባላቸው ተጨዋቾች ስላልተገነባ እና በሜዳ ላይም  ብዙ  የምንሳሳታቸው ነገሮች ስለነበሩም ውጤትን ሊያሳጣን ችሏል”።

ወደ ማጠቃለያው እናምራ

“በመጀመሪያ እዚህ ደረጃ ላይ ላደረሰኝ አምላኬ ከፍተኛ  ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በመቀጠል በጣም ኳስ ወዳዱ የሆነው ወላጅ አባቴ  እኔን እንደ አባትም እንደ እናትም በረሃ ለበረሃ በመንከራተት  ብዙ ለፍቶልኛል፤ ብዙም ደክሞልኛል እና እሱም ይመስገንልኝ። ሌላው የማመሰግነው በጨዋታም በስብዕናውም ጥሩ እንድንሆን ያደረገንን  አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌን እና አሁን ከቡድናችን ጋር የሌለውን ዘላለም ፀጋዬን እንደዚሁም  የቡና ደጋፊንና  ልምዳቸውን በመጠቀም እኛን በብዙ ነገሮች እየረዱን ያሉትን አማኑኤል ዩሃንስን፣ ስዩም ተስፋዬን፣ አቡበከር ናስርን፣ ታፈሰ ሰለሞንን፣ አስራት ቶንጆን ለማመስገን  እወዳለሁ”።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P