Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ለክለቤ መከላከያና ለአጥቂያችን ምንይሉህ ወንድሙ ችሎታ ያለኝ አድናቆትና ፍቅር መቼም ቢሆን ተዝቆ አያልቅም” ቴዎድሮስ ታፈሰ (መከላከያ)



በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ይወዳደር ለነበረው ዓምና ደግሞ ወደ ከፍተኛ ሊጉ ለወረደው የመከላከያ እግር ኳስ ቡድን በአማካይ ስፍራ ላይ የሚጫወተው ድንቁ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ቴውድሮስ ታፈሰ ኮቪድ 19 ወደ አገራችን ከገባበት ጊዜ አንስቶ ወቅቱን በምን መልኩ እያሳለፈ እንደሆነ ከዛ ውጪም ከእሱ የኳስ ጨዋታ ዘመኑ ውስጥ ስለሚገናኙ አንድ አንድ ነገሮች እና ሌሎችንም አጠር አጠር ያሉ ተጨማሪ ጥያቄዎችን የሊግ ስፖርት ጋዜጠኛው መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ አንስቶለት ምላሾችን በሚከተለው መልኩ ሰጥቷል፤ ተከታተሉት፡፡
ሊግ፡- በኮቪድ 19 የእግር ኳስን መጫወት አቁመሃል፤ ኳሱ በመቆሙ እና በቤት ውስጥ በመዋልህ ያለህ ስሜት ምን ይመስላል?
ቴውድሮስ፡- ኸረ በጣም ይከብዳል፤ ስለ ስሜቱ ለማውራትም ሆነ ለመናገርም ቃላቶችም ያንሱሃል፤ እግር ኳስ ማለት ለኳስ ተጨዋቹ ህይወት ማለት ነው፤ በእዛም ነው ተጨዋቹ ራሱንም ሆነ ቤተሰቡንም ጭምር እያስተዳደረ የሚገኘው፤ ስለዚህም በአጠቃላይ ኳሱ ሲቆም ህይወትም እንደ ቆመም ተደርጎ ነው የሚታሰበው፤ እንቅስቃሴን የማታደርግ ከሆነ ደግሞ በአንተ ላይ የስነ-ልቦናም ጫና ስለሚፈጠርብህና በኢኮኖሚካሊም ስለምትጎዳ እንደዚሁም ደግሞ ስፖርተኛውም ከዛ ውጪ ሌላ አማራጭ ስለሌለውም ያለ ኳስ በቤት ውስጥ መዋልን በጣም ከባድ ሆኖ ነው ያገኘሁት፡፡
ሊግ፡- ከእግር ኳሱ ለወራቶች ርቀሃል፤ ከኮቪድ 19 በመነሳት የት ነው ጊዜህን የምታሳልፈው?
ቴውድሮስ፡- በሐዋሳ ከተማ ያለው ሁኔታ እንደ አዲስ አበባ ስላልሆነ፤ ያ አልሆነም ማለት ደግሞ ወረርሽኙም ወደእዚህ አይመጣም ማለት ስላልሆነ የአሁን ሰዓት ላይ ጊዜዬን እያሳለፍኩ ያለሁት በእዚችው የትውልድ ከተማዬ ላይ ሆኜ ስፖርትን በመስራት፤ ከጓደኞቼም ጋር አልፎ አልፎ ርቀታችንን በመጠበቅ እና ከቤተሰቦቼም ጋር ሆኜ በመጨዋወት ነው፤ ይህን ወቅት ስናሳልፍም አስፈላጊውንም ጥንቃቄም እያደረግን ነው፡፡
ሊግ፡- በቤት ውስጥ ብቻ ነው የምታሳልፈው ወይንስ ወጣ ወጣስ ትላለህ?
ቴውድሮስ፡- አንድ ሰሞን ወጣ ወጣ እልና የስፖርት እንቅስቃሴዎችን እሰራ ነበር፤ ልምምድን ስሰራም አስፈላጊውን ጥንቃቄም እያደረግኩ ነበር፤ አሁን ላይ ግን ከወረርሽኙ አደገኛነት አንፃር ስፖርቱን እንዳንሰራ እየተገደብን ነውና ያን አቁሜ በቤቴ ውስጥ ብቻ ልምምዴን እየሰራው ነው፡፡
ሊግ፡- በደቡብ ክልል ጥሬ ስጋ በጣም ተወዳጅ ምግብ ነው፤ ሐዋሳ ከተማም አንዷ የደቡብ ከተማ ነችና አሁን ላይ አትብሉ የተባለው ጥሬ ስጋ እየተበላ እንደሆነ ይነገራል፤ ከዚህ ጋር አያይዘህ የምትለው ነገር ካለ?
ቴውድሮስ፡- በእኛ ክልል ጥሬ ስጋን እየበሉ ስላለበት ሁኔታ እስካሁን ዞር ዞር ብዬ አላየውም፤ ያም ሆኖ ግን ህብረተሰቡ ያን ከማድረግ ወደ ኋላ ፈፅሞ አይልም፤ ቢያንስ እንኳን እንደበፊቱ ባይሆንም ቀንሶ መብላቱ አይቀርም በተለይ ደግሞ በዓላቶች ሲመጡ፤ ስለዚህም ይህን የሚያደርጉ ካሉ ለእዚህ ክፉ ጊዜ ሲሉ ለጊዜው ከመብላት ቢታቀቡ ጥሩ ይመስለኛል፡፡
ሊግ፡- በኮቪድ 19 በርካታ ክለቦች ለተጨዋቾቻቸው ደመወዝ እየከፈሉ አይደሉም፤ የእናንተው መከላከያስ?
ቴውድሮስ፡- ስለ ክለባችን መከላከያ ብዙ ነገር ማለት ይቻላል፤ መከላከያ በዚህ በኩል እንደሌሎች ክለባትና ተቋማትም ነው ብዬ አላስብም፤ በቡድኑ ውስጥ እኔ እስካለሁበት ጊዜ ድረስም ቡድናችን ከደመወዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ ሲታማም ሰምቼም አላውቅም፤ ምንአልባት አንድአንድ ጊዜ ለቀናት ሊዘገይብን ይችላል እንጂ እንደሌሎቹ ቡድኖች ወር እና አስራአምስት ቀናቶችን አያቆየንምና ከክለባችን ጋር ተያይዞ ያለው የደመወዝ አከፋፈል ሁኔታ በጣም ጥሩ ነው፤ ክለባችንንም በእዚህ በኩል ላመሰግነውም እፈልጋለው፡፡
ሊግ፡- አሁን ላይ የስፖርት እንቅስቃሴዎችን ትሰራለህ፤ ከዛ ውጪስ ያስለመድከው ነገር አለ?
ቴውድሮስ፡- አሁን ላይ ከቤት መውጣት በጣም ከባድ ነገር ስለሆነና እዛም ስለማሳልፍ ከስፖርት እንቅስቃሴዎች ውጪ ሌላ ያስለመድኩት ነገር ተከታታይ ፊልምንም ማየት ነው፤ በተለይ ደግሞ መኒ ኤይስት ፊልም በጣም ተመችቶኝ እየተከታተልኩት ነው፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ዘመኔ ምርጡ ጨዋታዬ የምትለው የትኛውን ነው?
ቴውድሮስ፡- ምርጡ ጨዋታዬ ወደ ከፍተኛ ሊጉ በወረድንበት ዓመት ላይ ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረግነውንና እነሱን ያሸነፍንበት ነው፤ ያ ጨዋታ ለእኛ በወራጅ ቀጠና ላይ የነበርንበት እና ለእነሱ ደግሞ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ወደሚቃረቡበት ስፍራ የሚወስዳቸው ስለነበር የእኛ ቡድን ባሳየው ምርጥ ብቃት ያን ጨዋታ የማልረሳውም ነው፤ ምናለ ሁሌም እንደዛ ተጫወተን ቢሆን ኖሮ በሚልም ከፍተኛ ምኞትም ያሳደርኩበት ጨዋታም ነበር፤ ግን ምን ያደርጋል፤ በዛ ጨዋታ ላይ ጥሩ ነገርን ሰንቀን እና ተደስተን ወጥተን በሌላ ጨዋታ ላይ በሊጉ የሚያቆየንን ውጤት ለማስመዝገብ ስላልቻልን ያ ሁሌም ቢሆን ይቆጨኛል፡፡
ሊግ፡- ምርጧ ጎልህስ?
ቴውድሮስ፡- በእዛው ከሲዳማ ቡና ጋር ስንጫወት ያስቆጠርኳትን ነው፤ ድንቅ የቅጣት ምትንም ነበር ያገባሁት፡፡
ሊግ፡- በዓለም አቀፍ ደረጃ የአንተ የምንግዜም ምርጡ ተጨዋች?
ቴውድሮስ፡- ሴስክ ፋብሪጋዝ ነዋ!
ሊግ፡- ይሄን ጥያቄ ወደ እኛ ሀገር ስናመጣውስ?
ቴውድሮስ፡- ሙሉጌታ ምህረት፤ እሱን ምርጫዬ ያደረግኩት የክልሌ ልጅ ስለሆነ ሳይሆን ከልጅነቴ አንስቶ አባቴ ወደ ስታድየም ይዞኝ ሲመጣ በችሎታው የማረከኝ እና ፀባዩም የሚወደድ ተጨዋች ስለሆነም ነው፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ሜዳው ላይ አብረኸቸው ከተጫወትካቸው ተጨዋቾች መካከል ለአንተ የጨዋታ ሚና በቀዳሚነት ስፍራ ላይ በማስቀመጥ በጣም የምታደንቀው እና ምርጡም ጥምረቴ የምትለው ተጨዋች?
ቴውድሮስ፡- በእዚህ በኩል የምጠራው ተጨዋች ቢኖር ምንይህሉ ወንድሙን ነው፤ ከእሱ ጋር ከተስፋ ቡድኑ ጀምሮ አብረን ተጫውተናል፤ ጥሩ አቅም አለው፤ ጎል ያስቆጥርልሃል፤ መልካም ፀባይም አለው፤ ከዛ ውጪ ሁሉንም ነገር ያሟላ እና ኳስ ልሰጠው ስልም በአቋቋም /ፖዚሽን/ ደረጃም የት ስፍራ ላይ መገኘት እንዳለበትም ስለሚያውቅ እንደዚሁም ደግሞ ፈጣንም ስለሆነ በእዚሁ አጋጣሚ ለእሱ ችሎታና አብረንም እየተጫወትን ላለንበት የመከላከያ ክለብም ያለኝ ፍቅር ተዝቆም የማያልቅ ነው፡፡
ሊግ፡- ምንይህሉ በእግር ኳስ ተጨዋችነቱ ዘመን ብዙ ተጠብቆና ከፍተኛ ደረጃ ላይም ይደርሳል ተብሎ ጉዳት ብዙም እንዳይጓዝ እያደረገው ይገኛል፤ ስለ ምንይህሉ ከዚህ በኋላስ ስለሚኖረው የኳስ ጉዞ ምን ትላለህ?
ቴውድሮስ፡- በመጀመሪያ ምንይህሉ በኳሱ በሚፈልገው ስፍራ ላይ እንዳይደርስ ያደረገው ጉዳት ነበር፤ ያ ባይኖር በኳሱ ትልቅ ደረጃም ላይ ይደርስ ነበር፤ ይሄን ደግሞ እሱ ፈልጎት ሳይሆን ፈጣሪ ያለውም ነውና ያን እንደ አመጣጡ ትቀበለዋለህ፤ ያኔ ለእሱ ጥሩ ያልነበረውን የጉዳት ጊዜ አልፎ ደግሞ የአሁን ሰዓት ላይ በጣም አሪፍ እና ጥሩ በሆነበት ሁኔታም ላይ ይገኛል፤ ስለዚህም በቀጣይ ጊዜ የኳስ ህይወቱ በግሌ ከዚህ በላይም ነው እሱን የምጠበቀውና ለጓደኛዬ ጥሩ ነገር እንዲያጋጥመውም ነው የምመኘው፡፡
ሊግ፡- በወቅታዊ የእግር ኳስ አቋምህ ዙሪያ ምን የምትለው ነገር አለ? እንዳለህ ጥሩ አቅምና ችሎታስ በምፈልገው ስፍራ እና ደርሻለውስ ትላለህ?
ቴውድሮስ፡- በፍፁም፤ እንደዛ ብዬ አላስብም፤ ምክንያቱም ገና ነኝ ብዬ ስለማስብ፤ ስለዚህም የአሁን ሰዓት ላይ ካለኝ አቋም በመነሳት ለማለት የምፈልገው የእግር ኳስን መጫወት ገና ጀምሬያለው ብዬ ስለማምን እና ሁሉም ነገር የሚሆነው ደግሞ በጊዜውም ስለሆነ ፈጣሪ በፈቀደው ጊዜና መንገድ ጥሩ ደረጃ ላይ የምደርስበት ሁኔታም ስለሚኖር እስከዛው በርትቼ እሰራለው፡፡
ሊግ፡- መከላከያ በታችኛው ሊግ በመሳተፉ ዙሪያ ምን አይነት ስሜትን ይዘህ ነው የምትጫወተው?
ቴውድሮስ፡- በእውነቱ ለመናገር መከላከያን በከፍተኛ ሊግ ሲጫወት ማየት በጣም ያማል፤ ስለ ክለቡ መስማትም ይከብዳል፤ ቡድኑ ወደታችኛው ሊግ መውረድ አልነበረበትም፤ ግን ወርዷል፤ ተቋሙ ለስፖርቱ ከሚያደርገው ነገር በመነሳት በእዛ ደረጃ ላይ መድረስም አይገባውምም ነበር፤ ታችኛው ሊግ ላይ መታየት ባልነበረበት ሰዓትም ነው የታየው፤ ያ ደግሞ ሁላችም ተጨዋቾች ላይ የቁጭት ስሜትም ፈጥሮብን ነበር፤ ከዛ ተነስተን በአንድ ዓመትም ወደላይኛው ሊግ ልንመልሰው ተዘጋጅተንም ነበር፤ አንተ ትለፋለህ ፈጣሪ የሚሰጥህን ደግሞ በፀጋ ተቀብለህ ነውና የምትኖረው በቀጣይ ዓመት ላይ የተሻለ ነገር ሰርተን ተቋሙም ለእዚያ የሚሆንን ነገር ስለሚያደርግ ወደምንታወቅበት ሊግ ዳግም ለመመለስ ከፍተኛ ጥረተን እናደርጋለን፡፡
ሊግ፡- ካላችሁበት ደረጃ እና ውጤት አንፃር የሀገሪቱ አጠቃላይ ውድድሮች ስለተቋረጡ በጃችሁ እንጂ የፕሪምየር ሊጉን ውድድር ዳግም ለመቀላቀል ትቸገሩ ነበር ይባላል፤ በእዚህ ዙሪያ ምን የምትለው ነገር አለ?
ቴውድሮስ፡- እንደዛ ብዬ አላስብም፤ ምክንያቱም ኮቪድ 19 በዓለም ላይ ጭምር የተከሰተ ወረርሽኝ ስለሆነና ወድድሩሩም መቋረጡ ትክክል ስለሆነ ሁኔታውን በዛ መልኩ ነው የማየው፤ ውድድሩ የተቋረጠው ምንም እንኳን በመሪው ክለብ በነጥቦች ልዩነት ተበልጠን በምንገኝበት ደረጃ ላይ ቢሆንም ጨዋታው የተቋረጠው በጥሩ አቋም ላይ በነበርንበት ሰዓት ነው፤ ወደአሸናፊነት መንፈስ ላይም እየመጣንም ነው የተቋረጠው፤ ሊጉ ቢቀጥል ውጤታችንም ያምርልናል ብለንም ነበር ያሰብነውና ይሄን ነው ማለት የምፈልገው፡፡
ሊግ፡- የአሁን ሰዓት ላይ በጣም የሚናፍቁህ ነገሮች ምን ምን ናቸው?
ቴውድሮስ፡- የእግር ኳሱ ነዋ! በተለይ ደግሞ በተመልካች እና በደጋፊዎች ፊት ኳስ መጫወት፤ ደጋፊ ሲኖርም ነው የኳሱ ድምቀት የሚጨምረው ያ ናፍቆኛል፤ ስለዚህም ፈጣሪ ብሎ ወደምንወደው ኳሳችን እንድንመለስ እሱ ይርዳን ነው የምለው፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ….?
ቴውድሮስ፡- ከኮቪድ 19 ለመዳን ሁላችንምእንጠንቀቅ፤ በያለንበትም እንቆይ፤ ፈጣሪ በሰላም እስኪያገናኘን ድረስም እሱን በፀሎታችን እንለምነው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P