Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

ለዋንጫው አሁንም ተስፋ አንቆርጥም፤ እስከመጨረሻው እንታገላለን” ፍቃዱ ዓለሙ /ፋሲል ከነማ/

 

የፋሲል ከነማው የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ፍቃዱ ዓለሙ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የ22ኛው ሳምንት ጨዋታ ቡድናቸው ሲዳማ ቡናን እሱ ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ 1-0 ያሸነፈ ሲሆን ተጨዋቹ  ያገኙትን ድል አስመልክቶ ውጤቱ ጣፋጭ ነው ሲል ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል፤ ፋሲል ከነማ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የትናንቱን ውጤት ሳይጨምር ከመሪው ክለብ ቅ/ጊዮርጊስ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት 11 የደረሰ ሲሆን የቡድኑ ተጨዋች የሆነው ፍቃዱ አለሙ ካላቸው በርካታ ግጥሚያዎች አኳያ ዋንጫውን የማንሳት እድላቸው እንዳላከተመ እና ዋንጫውን ለማንሳትም እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስ ተስፋ እንደማይቆርጡ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

ሊግ፡- ሲዳማ ቡናን በአንተ ብቸኛ ግብ ለማሸነፍ ችላችኋል፤ ስለ ድሉና ግብ ስለማስቆጠርህ ምን የምትለው ነገር አለ?

ፍቃዱ፡- ሲዳማ ቡናን አሸንፈን ባገኘነው ድል በጣም ተደስቻለው፤ ውጤቱ ለእኛን ለደጋፊዎቻችን በጣም አስፈላጊ ስለነበር በጣም ጣፋጭ ውጤት ነው ያገኘነው፤ ወደ ሜዳ ተቀይሬ ስገባ አንድ ነገር አሳካለው ብዬ ጠብቄ ነበር፤ ያንም በተግባር ላይ አውዬዋለሁ፡፡ ግብ በማስቆጠሬም ከድሉ ውጪ ሌላው ተደራራቢ ደስታዬም ነው፡፡

ሊግ፡- በሜዳ ላይ የነበረው የጨዋታ ፉክክር ምን መልክ ነበረው?

ፍቃዱ፡- በመጀመሪያው አጋማሽ የጨዋታው ሜዳ አመቺ ስለነበር በሁለታችንም በኩል ጥሩ የኳስ ፍሰት ነበር፤ የጎል እድሎችን እነሱ አግኝተው ሳይጠቀሙበትም ቀርተዋል፤ እኛም የተወሰነ ሙከራ አድርገናል፤ ኳስ ይዘን ለመጫወትም ሙከራ አድርገናል፤ በሁለተኛው አጋማሽም ጥሩ ለመጫወት ችለን ጣፋጯን ድል ከሜዳ ይዘን ልንወጣ ችለናል፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማ በመሪው ቅ/ጊዮርጊስ በሰፊ ነጥብ ስለመበለጡ ምን የምትለው ነገር አለ?

ፍቃዱ፡- ውጤቱ እና የነጥብ ልዩነቱ በእዚህን ያህል ልዩነት መሆኑ ለእኛ ክለብ ፈፅሞ የሚመጥነው አይደለም፤ በጣምም ያስቆጫል፡፡  ያም ቢሆን ግን አሁንም ሊጉ ያልጠጠናቀቀ ስለሆነ እና በርከት ያሉ ግጥሚያዎችም ስለሚቀሩ ዋንጫውን ለማንሳት ተስፋ አንቆርጥም፤ ዋንጫው ባይሳካልን ራሱ ሁለተኛ ወጥተን ለኮንፌዴሬሽን ካፕ ማለፋችን ግን የማይቀር ነው፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማ ዘንድሮ ላጣው ውጤት የቱ ምክንያት ይጠቀሳል?

ፍቃዱ፡- ለውጤቱ መጥፋት የእኛ የመዘናጋት ችግር ይመስለኛል የጎዳን፤ ስንጀምር በድል ነበር፤ በቀሪዎቹ ግጥሚያዎች ትኩረት አለመስጠታችን ዋጋ ሊያስከፍለን ችሏል፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማ የሊጉን ዋንጫ ካጣ ሌላ የሚያልመው ውጤት ምንድን ነው?

ፍቃዱ፡- ከላይ ገልጬዋለሁ፤ አሁንም የምንጫወተው ለዋንጫ ነው፤ ውጤት ካጣን ደግሞ ሁለተኛነታችንን ማንም ቡድን አይነጥቀንም፤ ኢትዮጵያን ወክለን ለኮንፌዴሬሽን ካፑ የምናልፈውም እኛ ነን፡፡

ሊግ፡- ለፋሲል ከነማ ተጠባባቂ ሆነህም ጎሎችን እያስቆጠርክ ነው፤ ተጠባባቂ ከመሆንህ አኳያ ምን የምትለው ነገር አለ?

ፍቃዱ፡- ተጠባባቂ የመሆኔ ሁኔታ የአሰልጣኝ እይታ ነው፤ አንድ አንዴ መጫወት በነበረብኝ ሰዓት የማልጫወትበት ጊዜ ነበር፤ እነዛ ነገሮች ባያስደስቱኝም ለእኔ ግን ጠንክሬ እንድሰራ ስላደረገኝ እና ወደ ኋላ እንዳልልም ስላደረገኝ ለቡድኔ ጎል የማስቆጥርባቸው እድሎች ሊፈጥሩልኝ ችለዋል፡፡

ሊግ፡- የተጠባባቂ ተጨዋች ስትሆን ትከፋለህ?

ፍቃዱ፡- አንድ አንዴ ደስ የማይሉ ጊዜያቶች አሉ፤ ይህም መጫወት ባለብኝ ሰዓት ስላልተጫወትኩም ነው፡፡

ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ዘንድሮ ለአንተ ምርጡ ቡድን ማን ነው?

ፍቃዱ፡- እሱማ መጨረሻ ላይ ይታወቃል፡፡

ሊግ፡- ምርጡ ተጨዋችስ ማን ነው?

ፍቃዱ፡- የእኛው በረከት ደስታ ነዋ! ጥሩ ብቃቱን እያሳየ ይገኛል፡፡

ሊግ፡- በቀጣይ ጊዜ ስለሚኖርህ የኳስ ቆይታና ተስፋ ምን የምትለው ነገር አለ?

ፍቃዱ፡- አሁን ከምሰራቸው ልምምዶች አኳያ ጠንክሬ በመስራት በቀጣዩ ጊዜ ወደ ብሔራዊ ቡድን ዳግም መመረጥ እፈልጋለሁ፡፡

ሊግ፡- ቤትኪንጉን እንዴት ተመለከትከው?

ፍቃዱ፡- የዲ ኤስ ቲቪ መምጣት ሊጉን  አንድ ደረጃ ወደ ላይ ከፍ አድርጎልናል ማለት ይቻላል፤ ከዛ ውጪም የተጨዋቾችን የመጫወት ፍላጎትንም ጨምሮልናል፡፡

ሊግ፡- የፍቃዱ የኳስ ህይወት በሀገር ውስጥ ብቻ ተወስኖ የሚያበቃ ነው?

ፍቃዱ፡- አሁን ላይ ወደ ውጪ ወጥቶ የመጫወት ሀሳቡ ፈፅሞ የለኝም፤ ከዛ በፊት እኔ ላሳካው የምፈልገው ውጤት በሀገሪቱ ውስጥ ምርጥ /ቶፕ/ ከሚባሉት ተጨዋቾች መካከል አንዱ ስለመሆን ነው፤  ከዛ በኋላ ሌላውን ነገር አስብበታለው፡፡

ሊግ፡- ፋሲል ከነማ በቀጣይነት ስለሚያደርጋቸው  ጨዋታዎች ምን የምትለው ነገር አለ? /ያነጋገርነው ሐሙስ ጠዋት ነው/፡፡

ፍቃዱ፡- ቀጥሎ ከባህርዳር ከተማ ጋር የሚኖረን የደርቢ ጨዋታ አለ /ትናንት የተደረገ ግጥሚያም ነው/ እሱን ጨምሮ ሌሎቹን ጨዋታዎች በማሸነፍ መሪውን ቡድን ቅ/ጊዮርጊስ መከተል ነው የምንፈልገው፡፡

ሊግ፡- በዘንድሮ ውድድር ለአንተ ክስተት የሆነብህ ቡድን ማን ነው?

ፍቃዱ፡- ሐዋሳ ከተማ ነዋ!

ሊግ፡- ወደ ትዳር ህይወትህ እናምራ፤ ባለቤትህ ማን ትባላለች? እንዴትስ ትገለፃለች?

ፍቃዱ፡- የትዳር ህይወቴ በጣም ጥሩ ነው፤ ለደብረ ማርቆስ ስጫወት ያወቅኳት ጥሩ ባለቤትም አለችኝ፤ ስድስት አመትም ሆኖናል፤ የባለቤቴ ስም ሰላማዊት ኮከብ ይባላል፤ እሷ በኳሱ ዛሬ ለደረስኩበት ደረጃ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክታልኛለች፤ በተለይም ደግሞ አህምሮዬ ጥሩ በማይሆንበት ሰዓት ነፃ የምታደርገኝ እሷ ነችና ከልብ ላመሰግናት እፈልጋለው፡፡

ሊግ፡- እናጠቃል?

ፍቃዱ፡- በእግር ኳሱ ዛሬ ላይ ለደረስኩበት ደረጃ ከፈጣሪ ቀጥሎ ብዙ የምጠቅሳቸው ሰዎች አሉ፤ ሁሉንም ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P