Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ለፋሲል ከነማ ውጤት መጥፋት ተጠያቂው ስዩም ከበደ አይደለም” “የሊጉን ዋንጫ እኛ እናነሳለን፤ እኛ ካላነሳን ደግሞ  ቅ/ጊዮርጊስ ድሉን ይጎናፀፋል” ዓለምብርሃን ይግዛው /ፋሲል ከነማ/

“ለፋሲል ከነማ ውጤት መጥፋት ተጠያቂው ስዩም ከበደ አይደለም”

ዓለምብርሃን ይግዛው /ፋሲል ከነማ/

“የሊጉን ዋንጫ እኛ እናነሳለን፤ እኛ ካላነሳን ደግሞ  ቅ/ጊዮርጊስ ድሉን ይጎናፀፋል”

የዓምናው የሊጉ ሻምፒዮና ፋሲል ከነማ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎው  በሚታወቅበት ጥንካሬው እና  ስኬታማነቱ  አለመቀጠሉን ተከትሎ  በክለቡ ታሪክ ለመጀመሪያ  ጊዜ   ሻምፒዮና  ካደረጋቸው  አሰልጣኝ  ስዩም ከበደ ጋር  በስምምነት መለያየታቸው የሚታወቅ ሲሆን  ይህንንም   ያለፉትን  የውጤታማነት   እና የጥንካሬያቸውን   ጉዞ  አስመልክቶም  የቡድኑ የወደፊቱ ተስፈኛ ተጨዋች የሆነው  ዓለምብርሃን ይግዛው  የዘንድሮ   የቡድናቸው   ድክመት   የእነሱ  የተጨዋቾች  የትኩረት ማነስ   ችግር  እንጂ የአሰልጣኙ  ስዩም ከበደ  አለመሆኑን  በመናገር  አሰልጣኛቸው  ለውጤቱ መጥፋት  ተጠያቂ አለመሆኑን ከሊግ  ስፖርት  ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር   ባደረገው ቆይታ አስተያየቱን ሰጥቷል።

ሊግ  ስፖርት  በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ   የዘንድሮ የውድድር ዘመን ተሳትፎው  እንዳለፉት ሁለት እና ሶስት ዓመታቶች  የውድድር ጉዞው በሚታወቅበት  ስኬት ለመጓዝ ካልቻለውና  በመሪው ቅ/ጊዮርጊስ ክለብም በዘጠኝ ያህል ነጥብ በመበለጥ  በአራተኛ  ደረጃ ላይ ስለተቀመጠው ፋሲል ከነማ  የቡድኑ  ስኬታማ እና ተስፈኛ  ተጨዋች  የሆነውን  ዓለምብርሃን ይግዛውን  በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ አናግራው  የተሰጣት ምላሽ በሚከተለው መልኩ ቀርቧል።

ሊግ፦ በመጨረሻዋ ደቂቃ  በጅማ አባጅፋር  ላይ ያስቆጠራችሁት ግብ  እናንተን ባለድል አድርጓችኋል፤ በዕለቱ  ተፈጥሮባችሁ የነበረው  የደስታ ስሜት ምን ይመስላል?

ዓለምብርሃን፦  በእውነቱ በጣም  ደስ የሚልና የሚገርም  አይነት የደስታ ስሜት ነው  በሁላችንም ተጨዋቾች  ውስጥ  ሊፈጠርብን የቻለው። ይሄ የሆነውም  አስቀድሞ ካጣነው ውጤት አኳያና  በቡድናችንም ውስጥ  የተፈጠረ  የጭንቀት ስሜትም   ስለነበር   ነው ግቧን  የግጥሚያው መጠናቀቂያ ሰዓት ላይ  ስናስቆጥር ደስታችን  በጣም  ከፍ  ሊል  የቻለው።

ሊግ፦ በጨዋታው ላይ እንደነበራችሁ  ልዩነት የድሉ ውጤት  ለእናንተ የሚገባ  ነው?

ዓለምብርሃን፦ አዎን፤  በሜዳ ላይ የሚፈጠረው ነገር አስቀድሞ ባይታወቅም  በጨዋታው ከመጀመሪያው ደቂቃ  አንስቶ እናሸንፋለን ብለን ነበር  ወደ ሜዳ የገባነው።  በቡድናችን ላይ ቀድሞ ጎል  ቢቆጠርብንሞ  ያንንም  የእናሸንፋለን  የእርግጠኝነት መንፈሳችንን   በሜዳ ላይ   ለመተግበር  ስለቻልንና ድሉንምጰ ስላሳካነው   በቡድናችን   ስኬት  በጣም ልንደሰት ችለናል።

ሊግ፦ የአምና  ሻምፒዮናው  ክለባችሁ ከሊጉ መሪው ቅ/ጊዮርጊስ  ጋር  በአስር  ነጥብ ተበልጦ  በአራተኛ  ደረጃ ላይ  ይገኛል፤ ይሄ  የነጥብ  ልዩነት  በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በእዚህ መልኩ   ሲታይ ፋሲልን ጊዜያዊ የድል ቡድን  አያደርገውም?

ዓለምብርሃን፦  በእግር ኳስ ጨዋታ እንዲህ  ያሉ  የውጤት  ልዩነቶች  የሚያጋጥሙ እና የሚፈጠሩ  ናቸው።  አንድ ዓመት ዋንጫ በልተህ  በቀጣዩ ዓመት ዋንጫ ላታነሳ ትችላለህ ይሄ ሲታይ ፋሲልን  የአንድ ዓመት ቡድን አያስብለውም።  ምክንያቱም  ሊጉ ገና የ12  ሳምንታት የጨዋታ ጊዜ ይቀረዋል። ከእዚህ በኋላም የሚፈጠረው ነገር ስለማይታወቅ  እና የየፊቱንም ጨዋታዎቻችንን እያሸነፍን ለመሄድም ስለምንፈልግ ከመሪው ክለብ ጋር  ያለንን የነጥብ ልዩነት በማጥበብ  ወደለመድነው  ስኬታማነታችን እንመለሳለን።

ሊግ፦  ዘንድሮ  ለፋሲል ከነማ  ስኬታማ አለመሆንና  ሲያጣቸው ለነበሩት  ነጥቦች  የቱ  ምክንያት በዋናነት ይጠቀሳል?

ዓለምብርሃን፦ እኛን ውጤት ያሳጣን  የትኩረት ማነስ ችግሮች ናቸው፤  ከዛ ውጪ ሌላ ምክንያት  ፈፅሞ የለም።

ሊግ፦ ፋሲል ከነማን ዋንጫ ባነሳ በዓመቱ በእዚህ ደረጃ ላይ ማየቱ  አያሳዝንሞ?

ዓለምብርሃን፦ በጣም ነው እንጂ የሚያሳዝነው፤ ከክለቡ ትልቅነት አንፃር  በእዚህ ደረጃ ላይ መገኘት ፈፅሞ  አይገባንም ነበር። ምክንያቱም ይሄ ክለብ በስኳድ ደረጃ ምርጥ ተጨዋቾችን ከመያዙ  ባሻገር የአምናም ሻምፒዮና ስለነበር   ነው።  ያም ሆኖ ግን  በእግር  ኳስ እንዲህ ያሉ  የውጤት ማጣት ችግሮች ስለሚያጋጥሙ  ሁኔታውን እንደ አመጣጡ ተቀብለነዋል።  አሁን ላይ  ግን  የሊጉ ጨዋታዎች  ገና  የ13 ሳምንታት ጊዜ ስለሚቀረው እና የምናሻሽላቸውም ነገሮች  ስላሉ   ችግሮቻችንን አስተካክለን በመምጣትና ጨዋታዎችንም በማሸነፍ   እንዳዘንነው ሁሉ የምንደሰትባቸው እና ታሪክም የምንሰራባቸው ጊዜያቶች ይኖሩናል።

ሊግ፦ ፋሲል ከነማ  ባልተለመደ  መልኩ  ዘንድሮ  ላጣው  ውጤት  ተጠያቂነቱን  እናንተ ተጨዋቾች  ላይ አንዳንዶች ደግሞ  አሰልጣኝ ስዩሞ ከበደ ላይ  ሲያደርጉ ይስተዋላል፤  ላጣችሁት ውጤት  ጥፋቱና ተጠያቂነቱ  ከሁለታችሁ  ወገን  ማን ጋር   ነው ያለው?

ዓለምብርሃን፦  ለውጤቱ መጥፋት ተጠያቂውማ አሰልጣኙ ሳይሆን እኛ ተጨዋቾች  ጋር  ነው ያለው።  ይሄ ጥፋታችንም በሜዳ ላይ  ያለብን  የትኩረት  ማጣት እና ማነስም ችግር  ነው።

ሊግ፦  ፋሲል ከነማን  አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከያዘበት ጊዜ አንስቶ  ለወጣት ተጨዋቾች  ስለሚሰጠው የመሰለፍ  እድል እና   በእነሱ ላይ ስላለው እምነትስ ምን የምትለው ነገር አለ?

ዓለምብርሃን፦  አሰልጣኝ ስዩም ከበደ  በወጣት ተጨዋቾች ላይ ያለው እምነት በጣም  ከፍ ያለ ነው። እሱ እንደ አሰልጣኝ ብቻ ሳይሆን እንደ አባትም ጭምር በመሆን ነው ጥሩ ስልጠናን ሲሰጠንም የነበረው። በወጣት ተጨዋቾች ላይም እምነቱ ስላለው  የመሰለፍ እድልንም  ይሰጣል።  እሱ ቀይሮ በሚያስገባን ጨዋታ ላይም ሆነ በቋሚነት  አሰልፎ በሚያጫውተን ጨዋታም  ላይ በምንችለው አቅም ሁሉ  ለቡድኑ   ጥሩ   እና  መልካም የሆኑ ነገሮችንም በመስራት የእውቅናውን  ዓለም  እንድንቀላቀልም አድርጎናልና ይሄ በጣም የዋህ የሆነው አሰልጣኛችን በክለቡ ውስጥ ለነበረው ቆይታና ለሰራቸው መልካም ስራ ሊመሰገንም ይገባል።

ሊግ፦  ድል በተጎናፀፋችሁበት የእዚህ ሳምንት ጨዋታ ተጋጣሚያችሁን ጅማ አባጅፋርን እንዴት አገኘካቸው?

ዓለምብርሃን፦ ጅማ አባጅፋሮች እስከዛሬ ከገጠምናቸው ቡድኖች በጣም ጠንካራ  እና  ጥሩ ናቸው ማለት ይቻላል፤  ኳስ ይዘው ነው የሚጫወቱት። አብዛኛዎቹ ተጨዋቾች ወጣቶችም ናቸው።  ከእነሱ ጋር ያደረግነው ግጥሚያ  ከምልህ በላይም በጣም ፈታኝም ነበር።  ጠንካራ ሆነውም ነበር ያገኘዋቸው። ያም ሆኖ ግን በመጨረሻዋ ደቂቃ ላይ እኛ ያስቆጠርነው  የድል ግብ   ጥሩ  መነሳሻ ስለሆነልን  ያ የድል ውጤት በመገኘቱ   በጣሙን  ሊያስደስተን ችሏል።

ሊግ፦ በሁለታችሁ ጨዋታ በርካታ የግብ ኳሶች ይሳቱ ነበር፤ በእዚህ ዙሪያ ምን የምትለው ነገር ይኖርሃል?

ዓለምብርሃን፦  የእውነት ነው በሁለታችንም በኩል የግብ ኳሶች ሲሳቱ  ነበር።  ያም ሆኖ ግን  ግብ የማስቆጠር ፍላጎታችን በጣም ከፍ ያለ እና የመቻኮሎች ነገሮች  ስለነበሩ  እነዛን ዕድሎች እንዳሰብነው ሳይሆንልን ቀርቶ ልንጠቀምባቸው አልቻልንም።

ሊግ፦  ከጅማ አባጅፋር ጋር በነበራችሁ ጨዋታ  የድሉ ውጤት  የሚገባው  ለእነሱ ነው ያሉም  ነበሩ፤ በእዚህ ዙሪያስ የምትለው ነገር ካለ?

ዓለምብርሃን፦ /እንደ መሳቅ ካለ በኋላ/ ያው እንግዲህ  ሰው ነው  ይሄን ያለው፤  ድሉ ደግሞ ለእኛ ስለሚገባ ለራሳችን  ሆኗል።

ሊግ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ቀጣይ የምትፋለሙት ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ነው፤ ባለፈው ዙር ጨዋታ  በእነሱ ተሸንፋችኋል። አሁንስ የእዚህን  ዙር ጨዋታ  ማን በአሸናፊነት ያጠናቅቃል?

ዓለምብርሃን፦  እኛ ነና!  ለእዚህም ጨዋታ ከሁሉም

ግጥሚያዎች በተለየ መልኩም ከፍተኛ ትኩረትን ሰጥተነዋል፤ አዲስ አበባን አውርደን የምናየው ቡድንም አይደለም፤ በእርግጠኝነትም ግጥሚያውን እናሸንፋለን።

ሊግ፦ ፋሲል ከነማ በመሪው ክለብ በ10 ነጥብ  ተበልጦ በአራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ይሄ ልዩነት ሲታይ ከዋንጫው ፉክክር ወጥቷል ማለት ይቻላል?

ዓለምብርሃን፦ ከዋንጫው ፉክክር ወጥተናልም፤ አልወጣንም አልልም፤ የእኛ ትልቁ ዓላማችን በሊጉ ገና የ12 ሳምንታት ጨዋታ አለ። ከፊት  ላሉብን ጨዋታዎችም  ነው  ትኩረት ማድረግ እና ግጥሚያዎችንም ማሸነፍ የምንፈልገው እና  የመጨረሻው ቀን ውጤታችንን አብረን የምናየው ነው የሚሆነው።

ሊግ፦ በፋሲል ከነማ ክለብ ውስጥ ባለህ የተጨዋችነት ቆይታህ ደስተኛ ነህ?

ዓለምብርሃን፦ አዎን፤  ከምልህ በላይ ደስተኛ ነኝ። አቅሜ በሚችለው መልኩም ቡድኑን በጥሩ ሁኔታም እያገለገልኩት ነው።

ሊግ፦  ለፋሲል ከነማ ከስር ቡድኑ  ያደግክ እና አሁን ላይ ደግሞ በቋሚ ተሰላፊነት   እየተጫወትክ  የምትገኝ ተጨዋች ነህ፤  ይሄ  በአንዴ  እንዴት ሊሆን ቻለ?

ዓለምብርሃን፦  ይህን እድል  ለማግኘት  የቻልኩት ከስር ሳድግ  ነገሮችን ሰብሮ  ወደ ቋሚ ተሰላፊነቱ ለመግባት  ብዙ ነገሮችን ከውጪ ሆኜ  ለመመልከት ስለቻልኩ  እና   በሜዳ ላይ የምሰራው ልምምድ ብቻም በቂ ስላልሆነ ተጨማሪ ልምምዶችን  በግሌና ከጓደኞቼም ጋር ሆኜ  ስለምሰራና  ከእዛ ውጪም ተቀይሬ  በምገባባቸው ጨዋታዎች ላይ አምስት ደቂቃ ሲቀረውም የክለቤን ሰዎች ለማሳመን  የሚጠበቅብኝን ስራን ስለምሰራ  እና ሲኒየር ከሆኑ ተጨዋቾችም ምክሮችን በመስማት ራሴን በጥሩ መልኩም ስለማዘጋጀው ነው።

ሊግ፦ ብዙ ተጨዋቾች  የወደፊቱ ምኞታችሁ ሲባሉ  በእዚሁ በሀገር ውስጥ ለትላልቅ ቡድኖች መጫወት መቻል ይላሉ። የአንተም ምኞት እንደዛ ነው?

ዓለምብርሃን፦  ይሄ ምኞት በእርግጥ አለ። አሁንም የምጫወትበት ክለብ ትልቅ ስለሆነ የኳስ ጫማዬን በራሱ በእዚህ ቡድን ውስጥ ባጠናቅቅ በጣም ነው ደስ የሚለኝ።  ይሄ ባይሳካ እንኳን ነገ ወደ ሌሎች ቡድኖችም ሄጄ የምጫወትበትም እድሉ ይኖረኛልና  ያን  በመጀመሪያ ባሳካ በመቀጠል ደግሞ ለብሄራዊ ቡድንም ተመርጬ ሀገሬን ባገለግል እና በፕሮፌሽናልነት  ደረጃም ወደ ውጪ ሀገር በመውጣት ብጫወት በጣም ነው ደስ የሚለኝ።

ሊግ፦ በቅርቡ ለዋልያዎቹ ተመርጠህ ነበር?

ዓለምብርሃን፦ አዎ፤  ለቡድኑ  ተጠርቼ ተመልሼያለሁ።

ሊግ፦  በእግር ኳሱ አሁን ለመጣክበት መንገድ ምን ሁኔታ ጠቅሞኛል ትላለህ? የእግር ኳስ ተጨዋችስ እሆናለው ብለህ ነበር?

ዓለምብርሃን፦  አዎን፤  ያኔ  ኳስን በጣም  ስለምወድና በሰፈርና  በትምህርት ቤት ደረጃም እጫወት ስለነበር ከእዛ ውጪ  ምንም  ስለመሆን ያሰብኩት ነገር አልነበረም እና  ለእዛም ነው በርትቼ ልምምዴን ስለሰራው በፈጣሪ  እርዳታ  ኳስ ተጨዋች  የሆንኩት።

ሊግ፦ በእግር ኳሱ ለአንተ ተምሳሌትህ የነበረው ተጨዋች ማን ነው? ከባህርማዶ ተጨዋችስ የምታደንቀው?

ዓለምብርሃን፦ ልጅ ሆኜ ኳስን ስጫወት  በመስመር  ተጨዋችነት ነበር የምታወቀው። አሁን ላይም  ነው  ወደ ፉልባክ ቦታ  ተመልሼ ልጫወት  የቻልኩትና በጣም አደንቀው የነበረው ተጨዋች  በወቅቱ ለሲዳማ ቡና ይጫወት የነበረው  አዲስ ግደይ ጎንደር ላይ መጥቶ ሲጫወት  ድሪብሎቹ  ፍጥነቶቹን  እና  የሚሰራቸውን  ነገሮቾ  ሳይ ነገም እኔ እንደ እሱ እሆናለሁ በማለት ነው አድንቄው ተምሳሌቴ ያደረግኩት።  ከውጪ  ተጨዋቾች ደግሞ የኔይማር አድናቂ ነኝ።

ሊግ፦ ቤተሰቦችህን አጠር ባለ ቃላት ስትገልፃቸው? ዓለምብርሃን፦ ቤተሰቦቼ ዛሬ ለደረስኩበት ደረጃ ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ። በብዙ ነገሮችም ያግዙኛል። የልጅነት እልሜንና ፍላጎቴን እንዳሳካም ስላደረጉኝ ለእነሱ  ያለኝ ምስጋና ከፍ ያለ  ነው።

ሊግ፦ ከቤተሰቡ ስፖርተኛ አንተ ብቻ ነህ? ወንድምና እህት አለህ?

ዓለምብርሃን፦ አዎ። አንድ እህት አለኝ። ስፖርተኛው ደግሞ እኔ ብቻ ነኝ።

ሊግ፦ በመጨረሻ የሊጉን ዋንጫ ማን ያነሳል?

ዓለምብርሃን፦ ፋሲል ከነማ ያነሳል። እኛ ካላነሳን ቅ/ጊዮርጊስ ያነሳል ብዬ አስባለው። ይህን ካልኩ በኳሱ እዚህ ደረጃ ላይ እንድደርስ ላደረጉኝ አሰልጣኞችና ቤተሰቦቼ ምስጋናዬን አቀርባለው።

 

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P