Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

ለፋይናንስ ችግሮቻችን መፍትሔ ይገኝ ዘንድ ዝምታው ይሰበር (በመንሱር አብዱልቀኒ)

ቀድሞው የአየር ኃይል ባልደረባ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ወታደራዊ ስብዕና አሁንም አብሯቸው አለ። በመሰላቸው ቆፍጠን ብለው ይሟገታሉ። ይመኑበት እንጂ ነገሮችን በመሸፋፈን ማለፍ አይፈልጉም። ባለፈው ወር በኔክሰስ ሆቴል በተደረገው የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የቦርዱ ሊቀመንበር በክለባቸው ፊት የተጋረጠውን የፋይናንስ ፈተና በይፋ ለመናገርም አላመነቱም። ተጋኖ ያልተነገረ ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ቡና ዓመታዊ በጀቱን መሙላት ዳገት ሆኖበታል። ከቡናው ኢንደስትሪ እና ከሌሎች ገቢዎች የሚያገኘው ገንዘብ የዓመት “አስቤዛውን”ና የሰራተኞች ደመወዙን የመሸፈን አቅም ያንሰዋል። በበጀት ጉድለት “ነገ ለራሱ ይወቅበት” በሚል የውድድር ዘመኑን ጀምሯል።
ቡናዎች የፋይናንስ ምስጢሮቻቸውን ሚድያን በይፋ በጋበዙበት መድረክ ላይ የመግለፅ ልማድ በማዳበራቸው ጉዱን ሰማን እንጂ የስንቱ ችግር ተዳፍኖ እየተብሰለሰለ እንደሆነ ቤቱ ይቁጠረው።
የፋይናንስ ጉዳይ አደናቅፎት የማያውቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ እንኳን በመጨረሻ ገንዘብን በተመለከተ ወገቤን ማለት ጀምሯል። በአየር ጤና አካባቢ የክለቡ ደጋፊዎች ባዘጋጁት ፕሮግራም ላይ የክለቡ የስራ አመራር ቦርድ አባል አቶ ዳዊት  ውብሸት በሚያስመሰግን ሁኔታ ከክለቡ ደጋፊ ኩባንያዎች የቢዝነስ መቀዛቀዝ ጋር ተያይዞ ስፖርት ማህበራቸው የፋይናንስ ትንፋሽ እያጠረው መሆኑን አሳውቀዋል።
ከፍተኛ የደጋፊ መሰረት ያላቸው ሁለቱ የአዲስ አበባ ክለቦች ይፋ ያደረጉት ችግር መጪው ዘመን ለእግር ኳሳችን ብሩህ ይሆናል ብሎ ለማብሰር አያስችልም። የፕሪምየር ሊጉ የተዟዙሮ ፎርማት የሊጉ ተሳታፊ ክለቦችን ከተሞች ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ የተራራቀ እንዲሆኑ እያደረገ ነው። ከሁለት ዓመት በፊት አንድ የአዲስ አበባ ክለብ ለሊጉ ውድድር አንድም ጊዜ ወደ ትግራይ ክልል አይጓዝም ነበር። ዘንድሮ ግን አራት ጊዜ መጓዝ ግድ ሆኖበታል። አንድ የኢትዮጵያ ቡና ከፍተኛ አመራር እንደገለፁልኝ ክለባቸው ለአንድ ጨዋታ የሚያስፈልገው አማካይ ወጪ እስከ ብር 1.5 ሚሊዮን ደርሷል። ወደ ክልል ተጉዞ ለመጫወት ለትራንስፖርትና የሆቴል ወጪ ብቻ እስከ ብር 270 ሺህ  ያስፈልገዋል። ከአንድ ዓመት በፊት የቦርዱ ሰብሳቢ በአንድ መድረክ ላይ ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ ቡና ለአንድ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ብር 1 ሚሊዮን እንደሚያስፈልገው መግለፃቸው ይታወሳል። በአጭር ጊዜ ውስጥ እስከ 50% ጭማሪ ያሳየ ይመስላል።

ሌሎችም የአዲስ አበባ ክለቦች ተመሳሳይ የወጪ ሸክም ነበረባቸው ማለት ነው። ዘንድሮ ደግሞ ባለፉት ሶስት የውድድር ዘመናት በየዓመቱ አንድ አንድ የመዲናችን ክለቦች ከሊጉ መውጣታቸውን ተከትሎ (አዲስ አበባ ከተማ፣ ንግድ ባንክ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክና ደደቢት) ከአምና እና ከካቻምና ይልቅ የአዲስ አበባ ክለቦች ለበለጠ ጊዜያት ወደ ክልሎች እየተጓዙ ለመጫወት ተገደዋል። በመዲናችን የሚከናወኑ የፕሪምር ሊግ ጨዋታዎች ብዛት ሊጉ ከተጀመረ አንስቶ ቁጥሩ እንደ ዘንድሮው አንሶ አያውቅም። ክለቦቹ ብዙ በተጓዙ ቁጥር መጪያቸው መናሩን ልብ ይሏል።
ለብዙሃኑ የክልል ክለቦች ደግሞ ችግሩ ይበልጥ ብርቱ ነው።  በየወሩ ለተጫዋቾቹ ደመወዝ መክፈል የተቸገረው ጅማ አባ ጅፋር ለካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ 15 ተጫዋቾችን ብቻ ይዞ ወደ ሞሮኮ የተጓዘው በፋይናንስ ችግር ነበር። አንድ የአባጅፋር ምንጭ እንደነገረኝ ለሞሮኮው ጉዞ ክለቡ ለአንድ የልዑካን ቡድኑ አባል (በነፍስ ወከፍ) ብር 38,000 ገደማ ያስፈልገው ነበር። ችግሩ ከአቅም በላይ በመሆኑ ከአዲስ አበባ ጨዋታዎች በኋላ በጋዜጣዊ መግለጫዎች ላይ ቃላቸውን ሲሰጡ የነበሩት ረዳት አሰልጣኝ እንኳን ወደ አጋዲር፣ ሞሮኮ እንዳይጓዙ ተደርጓል።  ከቋሚ 11 ተጨዋቾቹ እና አራት ተቀያሪዎች በስተቀር ሃገርን በወከለ ውድድር ላይ ወደ ሞሮኮ መላክ አለመቻላቸው ቢብስባቸው እንጂ ተገቢ እንዳልሆነ የማያውቅ የለም። በዚህ ረገድ የጅማ አባ ጅፋር ኢንተርናሽናል ጉዞ በጊዜ መገታቱ ለበጎ ነው ያስብላል። ከዚህ በላይ በውጤት ወደፊት ቢራመድ ቀጣይ ወጪውን እንዴት ይሸፍን ነበር? ነገሩ ጭራሹኑ በሃገር ውስጥ ሊግ የሚኖረው የውድድር ሂደት ክለቡ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ የማይቀር ነበር። ሁሉም አልገለጠው እንደሁ እንጂ በዚህ አካሄዳችን ማንም የፋይናንስ መተማመኛ የለውም። የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ አንድ ቀን ጉልበት ከድቶት መቆሙ አይቀርም። ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሲዝኑን ሲጀምር ለተጨዋቾቹ የወር ደመወዛቸውን በሰዓቱ መክፈል አቅቶት ነው። ፋሲል ከነማ የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት እያሰበ ይገኛል። ኢትዮጵያ ቡና የስታዲየም ገቢ ጉዳይ ክለሳ እንዲደረግበት ግፊት ያደረገው በኪሳራ ጊዜ ያበደርከውን ፋይል እንደማገላበጥ ሆኖ ውዝፍ የቲኬት ገቢውን ከፌዴሬሽኑ ለማግኘት አስቦ የተነሳ ቀን ነበር።  የቡናማዎቹ ከፍተኛ አመራሮች ከአዲስ አበባ ስታዲየም የሚገኘው ገቢያቸው ቀቢፀ ተስፋ ቢሆንባቸው፣ አቤቱታቸውን ለአዲሱ አመራር አቀረቡ። የአቶ ኢሳያስ ጅራ አስተዳደር በተንከባለለ ውዝፍ ዕዳ ጫንቃው ጎብጧል። የአቶ ጁነይዲ ባሻ አስተዳደር ሲመጣ በካዝናው ገንዘብ ወርሶ፣ ሲወጣ የ34 ሚሊዮን ብር ባለዕዳ አድርጎታል። በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በሰበሰቡት የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ምክክር ላይ አቶ ኢሳያስ በይፋ እንደተናገሩት ከከተማዋ ክለቦች የስታዲየም ቲኬት ያልተከፈለ የ9.8 ሚሊዮን ዕዳ አናታቸው ላይ ይጨፍራል።
ፌዴሬሽኑ ዕዳውን ማመኑ መልካም ቢሆንም ለእነ አቶ ኢሳያስ ጅራ ግን የመክፈያው ጊዜ መቼ እንደሆነ አይታወቅም። የወረሱት ካዝና ባዶ በመሆኑ ነው።
እነ አቶ ኢሳያስ ያልተበደሩትን የመክፈል ግዴታ ውስጥ ብቻ አልገቡም። ያለፈው አስተዳደር በስታዲየም ቲኬት ሽያጭና አሰባሰብ ላይ የተፈራረመውን ስምምነት ከእነስህተቱ ለማክበር ተገድደዋል።

ስምምነቱ የቲኬት አቆራረጥ ዘመናዊ ስርዓት ወደ እግር ኳሳችን አምጥቷል። በመርህ ደረጃ “ክፍያ” ከተባለው ተቋም ጋር የገባው ውል ዝርዝር ግን ኢትዮጵያ ቡናን አላስደሰተም። በስምምነቱ መሰረት ከስታዲየሙ ቲኬት ሽያጭ ከሚገኘው እያንዳንዱ ብር 10፣ “ክፍያ” ብር 4.50  ይካፈላል። ይህም ከተቀዳሚ እሴት ታክስ በፊት ነው። ከዚያም ፌዴሬሽኑ ብር 3.20 (32%) ይካፈላል። እንግዲህ የክለቡን ድርሻ ስንት እንደሚሆን እናንተ አስሉት። ስምምነቱ ጥቅሙን ይጎዳልና ኢትዮጵያ ቡና እንደማይቀበለው ለፌዴሬሽኑ አሳውቋል።
ፌዴሬሽኑ ደግሞ ውሉን አሁኑኑ ለመቅደድ እንደሚቸገር በመግለፅ ከኢትዮጵያ ቡና ለተጨማሪ መፍትሔ አፈላላጊ  ድርድር ቀነ ቀጠሮ ይዟል። እስከዚያው ገንዘቤን ራሴ ልሰብስብ ያለው ክለብ “ራስህ መሰብሰብ አትችልም” በመባሉ ተቃውሞውን አሰማ። በኋላም ከፌዴሬሽኑ ጋር በታዛቢነትም ቢሆን የቲኬት  ሽያጩን እንዲያካሂድ ተስማሙ። ከዚያም ኢትዮጵያ ቡና የሽያጩን ቁጥጥር ሲያጠብቅ ቀድሞ በአንድ የጨዋታ ዕለት ከሚሰበስበው ገቢ በላይ  ማግኘቱን አንድ የክለቡ ከፍተኛ አመራር ነግረውኛል።
በቅርብ ክትትሉ ምክንያት ቡናማዎቹ እንግዳ ነገሮችን ማስተዋላቸውን ሰምቻለሁ። ለምሳሌ፣ ቡና ከሃዋሳ ከነማ ጋር ሲጫወት የክፍያን ባጅ ያንጠለጠለ ሰራተኛ 95 የታተሙ ቲኬቶችን ደብቆ እጅ ከፍንጅ ተይዟል። ለጥቁር ገበያ የተዘጋጀ መሆኑ በተጠረጠረው በዚህ ቲኬት መያዝ በየጨዋታው ላይ ድብቅ ሸፍጥ ሊሰራ እንደሚችልና ለስርቆት የተጋለጡ እድሎች ለመኖራቸው ማሳያ ሊሆን ይችላል።የኢትዮጵያ ቡና የፋይናንስ ፈተና በዚህ የሚገታ አይመስልም። በመንግስት ህግ አውጪ አካል በሂደት ላይ በሚገኘው የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያዎች ገደብና እገዳ አዋጅ ሊባባስ ይችላል። በዚህ ሳምንት የኢ·ፌ·ዴ·ሪ· ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች ከድርሻ አካላት ጋር በተወያዩበት ወቅት የኮሚቴዎቹ አባላት አስተያየት በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የቢራ ማስታወቂያዎችን የማገድ አዝማሚያ እንዳለ ተስተውሏል። አጠቃላይ እገዳው ከፀና ኢትዮጵያ ቡና ከሃበሻ ቢራ ጋር ያለው አጋርነት አደጋ ላይ ይወድቃል። በቀጥታ ካሽ ክፍያ እና በዓይነት ክለቡ ከአጋሩ የሚያገኘውን ጥቅም በዓመት እስከ ብር 20 ሚሊዮን የሚያደርሱ ገማቾች አሉ።
ፋሲል ከነማም ቢሆን ከዳሽን ቢራ ጋር ባለው የማሊያ ላይ አጋርነት በዓመት የሚያስገኝለት 8 ሚሊዮን ብር በርካታ ቀዳዳዎችን እንደሚደፍንለት ግልፅ ነው። የቢራ ማስታወቂያዎች እገዳ ከተጣለባቸው ክለቦች ብቻ ሳይሆኑ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑም በብሔራዊ ቡድኑ ከበደሌ ቢራ ጋር ያለው የ24 ሚሊዮን ብር የአጋርነት ጥቅል ስምምነትም ማሳረጊያ ይበጅለት ዘንድ ግድ ይላል።
የፕሪምየር ሊጉ የክልል ከተሞች ጂኦግራፊያዊ መራራቅ በየዓመቱ እየሰፋ መምጣቱን ያስተዋለ ደግሞ በመጪዎቹ ዓመታት በሊጉ ላይ በተወዳዳሪነት ለመቆየት የሚያስፈልገው በጀት መጠን እየናረ እንደሚሄድ ያምናል። ከዚህ በላይ አዳዲስና በተራራቁ ከተሞች ላይ መቀመጫቸውን ያደረጉ ክለቦች ወደ ሊጉ በመጡ ቁጥር የክለቦቻችን ወጪ የዚያኑ ያህል ያድጋል።
በሊጉ የተጫዋቾች ደመወዝ ባልተጠና መንገድ ተመንድጓል። ጃኮ አራፋት በወላይታ ዲቻ ሳለ በወር 250ሺህ ብር ይከፈለው ነበር። ይፋዊ ያልሆኑ መረጃዎች የጌታነህ ከበደን የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊርማ ክፍያ በወር ከዚህ በላይ ያደርሱታል።  የኢትዮጵያ ቡና የ2010 የሂሳብ ሪፖርት እንደሚያረጋግጠው ከ2006 ጀምሮ፣ በአራት ዓመት ልዩነት ውስጥ የተጫዋቾችና ስታፍ ደመወዝ ከብር 3.1ሚሊዮን ወደ ብር 30,244,000 ንሯል።
የአሰልጣኞችም ደመወዝ አድጎ ጣሪያ ነክቷል። ከ20 ዓመት በፊት በኢንተር ስፖርት ጋዜጣ ጀማሪ ሪፖርተር ሳለሁ ከአሰልጣኝ አስራት ኃይሌ ጋር ቃለምልልስ አደረግን። አሰልጣኙ ከቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝነት በፈቃዱ መልቀቁን እንዳሳወቀ የተሰራ ኢንተርቪው ነበር። እናም በወቅቱ  ወርሃዊ ደመወዙ ብር 2ሺህ ብቻ እንደነበርና በኋላም ብር 500 ተጨምሮለት በድምሩ በወር ብር 2,500.00 ይከፈለው እንደነበር ገልጿል።
ከ20 ዓመታት በኋላ የብር የመግዛት አቅም ምንም እንኳን በከፍተኛ መጠን የወረደ ቢሆንም በዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ  ከኢትዮጵያዊያን አሰልጣኞች እስከ 90ሺህ ብር የሚከፈላቸው እንዳሉ ይፋዊ ያልሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
ተጫዋቾችን ለማስፈረም የሚደረገው ሩጫ ደግሞ ከምንጊዜውም በላይ ጠንክሯል። በብሔርና ክልል ስሜት የጦዘው የማስፈረም ፉክክር ደግሞ ያለ አርቆ አሳቢነት ከፍተኛ ገንዘብን ለተጫዋቾችና አሰልጣኞች እየከፈሉ ቡድን ለመስራት መሯሯጡን አብዝቶታል። ገደብ የለሽ የተጫዋቾች ብዛት በአንድ ሲዝን የማስመጣቱ ነገር ደግሞ በክረምቱ 16 ተጫዋቾችን አስፈርሞ ሻምፒዮን ከሆነው ጅማ አባጅፋር በኋላ በበርካታ ክለቦች እንደ ልማድ መታየቱ ደግሞ የክለቦቻችንን የፋይናንስ አቅም ክፉኛ መፈታተኑን ይቀጥላል።
ታዲያ ወዴት እየሄድን ነው? የወጪ እድገት ጣሪያው  ቀና ብለን መጨረሻውን የማናይበት ደረጃ ደርሰናል። የገቢ መንገዶች ደግሞ በሁኔታዎች ትንበያ የመቀነስ አዝማሚያ ያሳያሉ። 2012፣ 2013፣ 2014 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ከወዲሁ አዳዲስ የገቢ ማግኛ ዕድሎችን እየሻቱ ራሳቸውን ካላጠናከሩ በስተቀር እነዚያ ዘመናት የህልውና ጥያቄም ይጋርጡባቸዋል። ለመጪው ዘመን ፈተና ከወዲሁ የተዘጋጀ ክለብ ብቻ ከፊት ለፊቱ ያለውን ተራራ ለመውጣት አይቸገርም። ለዚህም ክለቦቻችን ምስጢራዊነትን ትተው እንደ ኢትዮጵያ ቡና ሁሉ ክለቦቻችን የገቢ ወጪ ዝርዝራቸውን ይፋ እያደረጉ  ወይም እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጋረጠባቸውን የፋይናንስ ፈተና ለደጋፊዎቻቸው እያዋዩ ለፈተናዎቻቸው የጋራ መፍትሔ ለመሻት መስራት ይጠበቅባቸዋል።
(ፀሐፊው በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ዘወትር ረፋድ ላይ የሚተላለፈው ብስራት-ስፖርት ዋና አዘጋጅ ናቸው)

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P