ሊግን በቅዳሜ
ሊግ ስፖርት በዕለተ ቅዳሜ ከእጅዎ ትገባለች፤ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
በሀገር ውስጥ አምዷ የሲዳማ ቡናው ይገዙ ቦጋለ ስለ ራሱና ቡድኑ ይናገራል፡፡
ስለ ብሄራዊ ቡድን ምርጫ አስመልክቶም ከእኔ የተሻሉ አጥቂዎች ስላሉ ለዋልያዎቹ አለመመረጤ አያስከፋኝም ሲል፡፡
የሐዋሳ ከተማው በቃሉ ገነነም በቡድናቸው አቋምና በራሱ ዙሪያ የሚላችሁ ይኖራል፡፡
ሊግ በባህርማዶ ዘገባዋም አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ከአስቸጋሪ እውነታ ጋር ስለመፋጠጣቸው ፣ የሊቨርፑሉን የርገን ክሎፕን ስላበሳጨው የገና ሳምንት ጨዋታ፣ የጋርዲዮላ ቡድን ወደ ዋንጫው እየገሰገሰ ይሆን በሚሉትና ሌሎችም የሚወዷቸውን መረጃዎች ታቀርብለበታለች፡፡
ሊግ ስፖርትን ያንብቧት ይወዷታል፡፡
የሊግ ስፖርት የነገው የፊት ለፊት ገፇም ይህን ይመስላል፡፡