ሳምንታዊዋ እና ተወዳጅዋ ጋዜጣዎ ሊግ ስፖርት ነገ በቅዳሜ በገበያ ላይ ትውላለች፤
የእርስዎ የሆነችው ይህቺ ጋዜጣ ነገ ለንባብ ስትቀርብ በሀገር ውስጥ እትም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ጋር በተያያዘ የክለቡ ፕሬዝዳንትና የቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አብነት ገ/መስቀል በክለቡ ዙሪያ ሰፋ ያለ ቃለ-ምልልስን ከጋዜጣው ሜኔጂንግ ኤዲተር ዓለምሰገድ ሰይፉ ጋር አድርገዋል፤ አቶ አብነት ምን ብለው ይሆን? ከእነዛ ውስጥ የአሰልጣኝን ቅጥር አስመልክቶ “በፉከራ፣ በድሮ ስምና ዝና ብቻ ማንንም የሀገር ውስጥ አሰልጣኝ አንቀጥርም” ያሉት ሲገኝበት ሌለው ደግሞ ሚቾን ልታመጡ አስባችሁ ነበር ለተባለው ጥያቄ በፍፁም አላሰብንም፤ የሚናፈሰውም አሉባልታ ነበር በማለት ከሰርቢያዊው አሰልጣኝ ቅጥር በኋላ ሚቾ በክለቡ ውስጥ ስለሰራው ታሪክ ምስጋናን በማቅረብ ከዚህ በኋላ “ሚቾ በምክትል አሰልጣኝነት ለማገልገል ከፈለገ መምጣት ይችላል” የሚል አስተያየትን ሰጥተዋል፤ ሊግ ነገ አታምልጦት፡፡
ሊግ ስፖርት በባህርማዶ ዘገባዋም ቫራን ለማንቸስተር ዩናይትድ ደጀን ይሆናል ተብሎ ስለመታመኑ፣ አዶይ የቼልሲ እቅድ ስለመሆኑ፣ ስሚዝሮው የቤርግካምፕ አልጋ ወራሽ ሊሆን ይችላል ተብሎ ስለመገመቱና ሌሎችንም መረጃዎች በነገው እትሟ ታስነብቦታለች፡፡
የሊግ ስፖርት ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህን ይመስላል