የቅዳሜ እትም ጋዜጣዎ ሊግ ስፖርት በሚወዱት መረጃዎች ታጅባ ለንባብ ትቀርብሎታለች።
ሊግ ጋዜጣ ነገ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ በመውጣት ታስነብቦት ይሆን?
በሀገር ውስጥ ቅዳሜ ዕለት ከተሞሸረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሀይደር ሸረፋ ጋር ስለ ጋብቻ ስነ ስርዓቱን ከኳስ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ አናግረነው የሰጠን ምላሽ ይኖራል። ሀይደር ምን ብሎ ይሆን?
ሊግ ስፖርት በሀገር ውስጥ ሌላ ዘገባዋ ከወልቂጤ ከተማ ወደ ሲዳማ ቡና የተዛወረው ፍሬው ሰለሞንም የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርቦለት የሚሰማውን ተነፍሷል።
ሊግ ስፖርት በባህርማዶ ዘገባዋስ ምንን ጉዳይ ይዛሎት ቀርባ ይሆን? ከሁሉም በላይ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂ ከሆኑት ጨዋታዎች መካከል አንዱ ስለሆነው የአርሰናል እና የቼልሲ ጨዋታ ሰፋ ያለ ትኩረትን ሰጥታ ታስነብቦታለች።
ሊግ ሌሎችም ምርጥ መረጃዎች አሏት። አታምልጦት። በእሷ የነገ ጊዜዎን ያሳልፉ።
የሊግ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል።