ሊግ ስፖርትን በቅዳሜ እትሟ
ነገ ጠዋት እንዳታመልጦት
የዘወትር ቅዳሜ ተወዳጅ ጋዜጣዎ ሊግ ስፖርት ነገም የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎችን በዕለተ ቀኗ ይዛሎት ከተፍ ትላለች።
ሊግ በሀገር ውስጥ መረጃዋ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግን አስመልክታ ስለ ሻምፒዮኑ ፋሲል ከነማ ከአሰልጣኙ ስዩም ከበደ ጋር ቆይታን ያደረገች ሲሆን ሌላው ለወላይታ ድቻ ጥሩ እንቅስቃሴን በማድረግ ላይ የሚገኘው ቸርነት ጉግሳም ቡድናቸው ከሊጉ ላለመውረድ የሚጫወትበት ጊዜ እንዳበቃም ለጋዜጣው አስተያየቱን ሰጥቷል።
ሊግ በባህርማዶ ዘገባዋም የተለያዩ ሀገራትን የውስጥ ውድድሮች እና ስለ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የእንግሊዝ ክለቦች ለፍፃሜ መቅረባቸውን አስመልክቶ ስለመድመቃቸው እና በስፔን ላሊጋ ባርሴሎና ከአትሌቲኮ ማድሪድ ስለሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታም የምትሎት አለ። ሊግን ነገ ስታገኟት በበርካታ መረጃዎችም ታጅባ ነው። ተከታተሏት።
የሊግ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅም ይህንን ይመስላል።