ሊግ ስፖርትን በቅዳሜ እትሟ በምን መልኩ ታገኟት ይሆን?
የሁለት አስርት ዓመታትን ዕድሜ ልታስቆጥር የአንድ ዓመት ዕድሜ የሚቀራት ተወዳጇ ሊግ ስፖርት ጋዜጣ ነገም ቅዳሜ ውድ አንባቢዎቿ በሚጠብቋት መልኩ ለንባብ በመቅረብ ልታስደስቶት ከጫፍ ደርሳለች፡፡
የእርስዎ እና የእኛ የሆነችው ተወዳጇ ጋዜጣዎ ነገስ ገበያ ላይ ስትውል ምን ምን ጉዳዮችን ይዛሎት ትቀርብ ይሆን?
ሊግ ስፖርት በሀገር ውስጥ አምዷ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን አስመልክቶ ከሲዳማ ቡናው የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ይገዙ ቦጋለ ጋር በኳስ ህይወቱ ዙሪያና ከክለባቸው ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሚለው ይኖራል፡፡
ይገዙ ከተናገረው ውስጥ ኳስ ተጨዋች እንዳይሆን ከመፈለጉ አንፃር ትጥቁ ይደበቅበት እንደነበር ሀሳቡን ሲገልፅ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎአቸውም ዘንድሮ ክለባቸውን በኢንተርናሽናል ውድድር መድረክ የሚያሳትፉበትን ውጤት እንደሚያስመዘግቡ ይናገራል፡፡
ሊግ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿም ዙሪያ የማንቸስተር ዩናይትዱ ሳንቾ በክለቡ ቆይታው እየደበዘዘ ስለመምጣቱ፣ ግሪሊሽ በሲቲ ቆይታው ከክለቡ አጨዋወት ጋር ለመጣጣም ስለመቸገሩና በአዲስ ምዕራፍ ላይ የሚገኘው የአርሰናሉ ስሚዝሮው የሚነግሩኝን የማልሰማ ሰነፍ ተጨዋች ነበርኩ ስለማለቱ ጥልቅ የሆነ ዘገባን ሊግ አቅርባሎታለች፡፡
ሊግ ስፖርት ፈፅሞ አታምልጦት፤ የሊግ ስፖርት ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅም ይህንን ይመስላል፡፡
ሊግ ስፖርትን በቅዳሜ እትሟ በምን መልኩ ታገኟት ይሆን?
ተመሳሳይ ጽሁፎች