ሊግ ስፖርትን በቅዳሜ እትሟ በምን መልኩ ታገኟት ይሆን
የሁለት እስርት ዓመታትን ዕድሜ ልታስቆጥር የአንድ ዓመት ዕድሜ የሚቀራት ሊግ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ቅዳሜም ውድ አንባቢዎቿ በሚጠብቋት መልኩ ለንባብ ለመቅረብ ከጫፍ ደርሳለች፡፡
የእርስዎ እና የእኛ የሆነችው ተወዳጇ ጋዜጣ ነገ ገበያ ላይ ስትውልም በሀገር ውስጥ አምዳ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን ከሚመራው ፋሲል ከነማ ተጨዋቾች ውስጥ ጅማ አባጅፋርን በሰፊ ግብ ባሸነፉበት ጨዋታ ሁለት የድል ግቦችን ከማስቆጠር ባሻገር ምርጥ እንቅስቃሴውን በማሳየት ላይ የሚገኘውን በዛብህ መላዮን በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ አናግረነዋል፡፡
ለተጨዋቹ ከቀረቡለት ጥያቄዎች መካከልም አንዱ የሰጠው ምላሽ ይህን ይመስላል፤ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ተሳትፎአቸው ዙሪያ “ፋሲል ከነማን በቀላሉ ማቆም የማይታሰብ ነው” በማለት ዘንድሮም የሊጉን ዋንጫ እንደሚያነሱ ይናገራል፡፡
ሊግ በሌላ ሀገር ውስጥ ዘገባዋ ከአዳማ ከተማው አማካይ አማኑኤል ጎበናም ጋር ቆይታ አላትና አታምልጦት፡፡
ሊግ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿም ዙሪያ በነገው ዕለት በኦልድትራፎርድ ስታዲየም ስለሚካሄደው የማንቹኒያን ደርቢ ጨዋታ ጥልቅ ዘገባ ያላት ሲሆን ይህን ጨዋታ የሶልሻየሩ ማንቸስተር ዩናይትድ ወይንስ የጋርዲዮላው ማንቸስተር ሲቲ በአሸናፊነት ይወጡታል የሚለው ጉዳይ ትኩረትን ስቧል፡፡
በሁለቱ ቡድኖች የእርስ በርስ ፍልሚያም ሶልሻየርና ጋርዲዮላ ቡድኖቻቸውን ከያዙበት ጊዜ አንስቶም የማሸነፍ አጋጣሚው ወደ ሶልሻየር አዳልቶ የነበረ ሲሆን ነገስ ማን ሊያሸንፍ ይችላል በሚል የ9 ሰዓት ከ30 ጨዋታው አጓጊ ሆኗል፡፡
ሊግ በሌላ የባህር ማዶ ዘገባዋ ስለ ቶተንሃም፣ እና ከሉዊስ ሱዋሬዝ ጋር በተገናኘም የምታስነብቦት ይኖራል፡፡
ሊግ አታምልጦት፤ የሊግ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ምስል ይህንን ይመስላል፡፡
https://t.me/Leaguesport