ሊግ ስፖርትን በቅዳሜ እትሟ ጠብቋት
የ20ኛ ዓመቷን ልትይዝ በመቃረብ ላይ የምትገኘው ሊግ ስፖርት ጋዜጣ ነገም እንደተለመደው ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህርማዶ ዘገባዎችን ይዛሎት ትቀርባለች።
ሊግ ስፖርት ነገ ለንባብ ስትቀርብም፦
– በሀገር ውስጥ መረጃዋ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ከሻምፒዮናው ቅ/ጊዮርጊስ ወደ ባህርዳር ከተማ ዝውውር ያደረገውን የአብስራ ተስፋዬን በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ አናግረነው ምላሹን ሰጥቶናል።
የአብስራ ምን ብሎ ይሆን? እሱ ከተናገራቸው ንግግሮች ውስጥ የሊግ ስፖርት የፊት ለፊት ገፅ ላይ አንዱ ሊቀርብላችሁም ችሏል።
-ሊግ ስፖርት በባህርማዶ ዘገባዋም እሁድ ዕለት በማንቸስተር ዩናይትድ እና በአርሰናል መካከል በሚደረገው ጨዋታ የመድፈኞቹ ያለመሸነፍ ጉዞ በቀያይ ሰይጣኖቹ ይገታ ይሆን? በሚል እና ሌሎችንም መረጃዎች የምታቀርብሎት ሲሆን የነገዋ ጋዜጣም እንዳታመልጦት ጋብዘንዎታል።
ሊግ ስፖርት አታምልጦት፤ ይወዷታል።
የሊግ ስፖርት የፊት ለፊት ገፃም ይህንን ይመስላል።