ሊግ ስፖርት በነገው ዕለት ለንባብ ስትቀርብም በሀገር ውስጥ እትሟ ስለ ኢትዮጵያ ቡና ቤተሰባዊ ሩጫን አስመልክቶ እና በዛሬው ዕለት አዲስ ፈራሚ ተጨዋቾችን ከደጋፊው ጋር በሚያስተዋውቅበት ዘገባ ዙሪያ እንደዚሁም ደግሞ የሐዋሳ ከተማው መድሃኔ ብርሀኔ ስለ ክለቡ፣ ስለ ራሱ እና ስለ ሊጉ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል።
የሐዋሳ ከተማው መድሃኔ ለጋዜጣው ከሰጣቸው አስተያየቶች ውስጥም “ዘንድሮ ስኳዳችን ጠባብ መሆኑ እንጂ እስከ ዋንጫው ተፎካካሪነት እንጓዝ ነበር” ሲል በባህርማዶ ዘገባዋ ዙሪያ ደግሞ ስለ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የአዲሱ የውድድር ዘመን መጀመርን አስመልክቶ /ዳግም ሊጉ በመመለሱ ዙሪያ/ እና ሌሎችን መረጃዎችንም ሊግ ስፖርት ለእናንተ ለንባብ በሚያመች መልኩ አቅርቦሎታለች።
ሊግ ስፖርት የእርስዎ ናት፤ አታምልጦት።
የሊግ ስፖርት የነገው የፊት ለፊት ገፅም ይህን ይመስላል።