ሊግ ስፖርትን በቅዳሜ
20ኛ ዓመቷን ልትደፍን የአንድ ዓመት ዕድሜ የቀራት ተወዳጇና ተናፋቂዋ ጋዜጣችን ሊግ ስፖርት እንደተለመደው በዕለተ ቀኗ ነገ ቅዳሜም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህርማዶ ዘገባዎችን አጣምራ ይዛ ለንባብ ትቀርብሎታለች፤ የእኛ እና የእርስዎ ጋዜጣ የሆነችው ሊግ ስፖርት ቅዳሜ በገበያ ላይ ስትውልም፦
?በሀገር ውስጥ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የውጤት መሻሻል እያሳየ ስለመጣው ሲዳማ ቡና የክለቡ ተጨዋች ሙሉዓለም መስፍን /ዴኮ/ ይናገራል።
ሙሉዓለም ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ከሰጠው አስተያየት ውስጥ “የዋንጫ ርሃቤን በሲዳማ ቡና ማሳካት እፈልጋለሁ” ሲል ለጅማ አባጅፋር የሚጫወተው እዮብ አለማየሁም ስለ ቡድናቸው እና ስለ ራሱ ይናገራል። ምን ብሎ ይሆን?
የቅዳሜዋ ሊግ በባህርማዶ ዘገባዋም የተለያየ መረጃዎች አላት፤ ምን ጉዳዮችን ታስነብቦት ይሆን?
ሊግ በዕለቱ ይዛሎት ከምትቀርበው መረጃዎች መካከልም ስለ ካራባኦ ካፕ ቼልሲ እና ሊቨርፑል ስለሚያደርጉት የፍፃሜ ጨዋታ
-ሳካና ስሚዝ ሮው የአርሰናል የውጤት ሚስጥር ስለመሆናቸው
-ኤላንጋ የዩናይትድ አዲሱ ሚስጥር ስለመባሉ እና ሌሎችን ተጨማሪ መረጃዎችን በመያዝ ነገ በንባብ ታስኮመኩሞታለች።
ሊግ ስፖርት አታምልጦት፤ ይወዷታል።
የሊግ ስፖርት የነገ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል።
ሊግ ስፖርትን በቅዳሜ 20ኛ ዓመቷን ልትደፍን የአንድ ዓመት ዕድሜ የቀራት ተወዳጇና ተናፋቂዋ ጋዜጣችን ሊግ ስፖርት እንደተለመደው በዕለተ ቀኗ ነገ ቅዳሜም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህርማዶ ዘገባዎችን አጣምራ ይዛ ለንባብ ትቀርብሎታለች
ተመሳሳይ ጽሁፎች