ሊግ ስፖርትን በቅዳሜ
20ኛ ዓመቷን ልትደፍን የአንድ ዓመት ዕድሜ ነው የቀራት፤ ተወዳጅና ተናፋቂም ጋዜጣ ናት። ሊግ ስፖርት እንደተለመደው በዕለተ ቀኗ ነገ ቅዳሜም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህርማዶ ዘገባዎችን በማጣመር ይዛሎት ትቀርባለች። የእኛ እና የእርስዎ ጋዜጣ የሆነችው ሊግ ስፖርት ቅዳሜ በገበያ ላይ ስትውልም፦
በሀገር ውስጥ፦ የኢትዮጵያ ቡናው አማካይ አማኑኤል ዩሃንስ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና በአንደኛው ዙር ስላደረገው የውድድር ጉዞ እና ስለ ዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እንደዚሁም በውድድሩ አንድ ጨዋታ ላይ የግጥሚያው ኮከብ ተብሎ ስለ መሸለሙ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል።
አማኑሄል በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ዙሪያ ስለ ክለባቸው ከሰጠው አስተያየት ውስጥም በሊጉ “የሚመጥነንን ውጤት ባናስመዘግብም አሁንም ከዋንጫው አልራቅንም” ይላል።
ሊግ ስፖርት ከእዚህ ዘገባ በተጨማሪ ከወላይታ ድቻው ቃልኪዳን ዘላለም ጋርም ቆይታ አላት። ቃልኪዳን ምን ብሎ ይሆን? ነገ ሊግን ያንብቧት። ሊግ በባህርማዶ ዘገባዋም ነገ የተለያየ መረጃዎችን ይዛሎት የምትቀርብ ሲሆን ከእነዛም መካከል እሁድ ምሽት ስለሚደረገው የኤልክላሲኮ ጨዋታም የምትሎት ይኖራል።
ከእነዛም መካከል ከአናት የተቀመጠው ሪያል ማድሪድ መሻሻሎችን ካሳየው ባርሳ ስለሚፋለምበት ጨዋታ፣ የሲቲ መሪነት የዛፍ ላይ እንቅልፍ ስለመባሉ፣
ማንቸስተር ዩናይትድ ከሻምፒዮንስ ሊግ መሰናበቱ አጣብቂኝ ውስጥ እንዲገባ ስላደረገው ሁኔታ እና ሌሎችን መረጃዎች ጨምራ ሊግ በነገው እትሟ ታስነብቦታለች።
ሊግ ስፖርት አታምልጦት፤ ይወዷታል።
የሊግ ስፖርት የነገ የፊት ለፊት ገፅም ይህንን ይመስላል።
ሊግ ስፖርትን በቅዳሜ 20ኛ ዓመቷን ልትደፍን የአንድ ዓመት ዕድሜ ነው የቀራት፤ ተወዳጅና ተናፋቂም ጋዜጣ ናት። ሊግ ስፖርት እንደተለመደው በዕለተ ቀኗ ነገ ቅዳሜም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህርማዶ ዘገባዎችን በማጣመር ይዛሎት ትቀርባለች።
ተመሳሳይ ጽሁፎች