Google search engine

ሊግ ስፖርትን በቅዳሜ 20ኛ ዓመቷን ልትደፍን የአንድ ዓመት ዕድሜ የቀራት ተወዳጇና ተናፋቂዋ ጋዜጣችን ሊግ ስፖርት እንደተለመደው በዕለተ ቀኗ ነገ ቅዳሜም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህርማዶ ዘገባዎችን አጣምራ ይዛ ለንባብ ትቀርብሎታለች

ሊግ ስፖርትን በቅዳሜ
20ኛ ዓመቷን ልትደፍን የአንድ ዓመት ዕድሜ የቀራት ተወዳጇና ተናፋቂዋ ጋዜጣችን ሊግ ስፖርት እንደተለመደው በዕለተ ቀኗ ነገ ቅዳሜም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህርማዶ ዘገባዎችን አጣምራ ይዛ ለንባብ ትቀርብሎታለች፤ የእኛ እና የእርስዎ ጋዜጣ የሆነችው ሊግ ስፖርት ቅዳሜ በገበያ ላይ ስትውልም፦
በሀገር ውስጥ፦ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የአምናው ሻምፒዮናን ፋሲል ከነማን ድል ካደረጉት የሐዋሳ ከተማ ተጨዋቾች ውስጥ በአምናው የሊጉ ውድድር ተስፈኛው ኮከብ ተጨዋች ወንድማገኝ ሀይሉ ስለ ቡድኑ፣ ስለ ራሱ እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ይናገራል።
የሐዋሳ ከተማው አማካይ ወንድማገኝ ከተናገረው ውስጥ በሊጉ “እኛን አሳምኖ ያሸነፈን ቡድን ማንም የለም፤ ሊጉን መምራት ነበረብን” ሲል ሌላው የአዲስ አበባ ከተማ የአጥቂ ስፍራው ተጨዋች ፍፁም ጥላሁንም ሰበታ ከተማን በሰፊ ግብ ካሸነፉ በኋላ በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሹን ሰጥቷል።
የቅዳሜዋ ሊግ በባህርማዶ ዘገባም የተለያየ መረጃ አላት፤ ምን ጉዳዮችን ታስነብቦት ይሆን?
-የፒ ኤስ ጂ ምትሀተኛው ተጨዋች ምባፔ ለማድሪድ በረከት ይሆናል ስለመባሉ
-መድፈኞቹ ከስህተታቸው ለመማር ስለመዘጋጀታቸው
-አስፈሪው ሲቲ የስተርሊንግ ጉዳይ ራስ ምታት ሆኖበታል ስለመባሉ
-ጆታና የሊቨርፑል ጭንቀት
በሚሉ እና ሌሎችን ተጨማሪ መረጃዎችን በመያዝ ነገ በንባብ ታስኮመኩሞታለች።
ሊግ ስፖርት አታምልጦት፤ ይወዷታል።
የሊግ ስፖርት የነገ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P