ሊግ ስፖርት ጋዜጣ በሀገር ውስጥ እና በባህር ማዶ ዘገባ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?
በሀገር ውስጥ ስለ አዲስ አበባ ከተማ ሲቲ ካፕ ዋንጫ ለፍፃሜ ከቀረቡት የቅዱስ ጊዮርጊስና የሰበታ ከተማ ክለብ ተጨዋቾች ውስጥ በግማሽ ፍፃሜው ጨዋታ ለቡድኖቻቸው ጥሩ በመንቀሳቀስ የጨዋታ ኮከብ ከተባሉት ውስጥ አቤል ያለው እና ታደለ መንገሻን በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ አናግረናቸው የሰጡን መልስ የሚገኝ ሲሆን ከዛ ውጪ ደግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያው ጨዋታ ላይ እያደረገ ስላለው ተሳትፎና ብዙዎች ባልጠበቁት ሁኔታም ኮትዲቭዋርን ድል ስላደረግንበት ጨዋታ ከዋልያዎቹ ተጨዋቾች ውስጥ ጥሩ እንቅስቃሴ ካደረጉት መካከል ይሁን የአማካይ ስፍራ ተጨዋቹን እንዳሻውን በማነጋገር እሱም ምላሽ ሰጥቶናል፡፡
ሊግ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባም ተጠባቂ ስለሆነው የማንቸስተር ሲቲና የቼልሲ ጨዋታ ሰፋ ያለ ዘገባን ይዛ የወጣች ሲሆን ሌሎችም መረጃ አላት፤ ሊግ ጋዜጣ አታምልጦት፡፡
ሊግ ስፖርትን ያንብቧት ሊግ ስፖርት ጋዜጣ ሳምንታዊዋ ቀኗን ቅዳሜ ጠብቃ ገበያ ላይ ውላለች፡፡
ተመሳሳይ ጽሁፎች