Google search engine

ሊግ ስፖርት፤ ሊግ ስፖርት፤ ሊግ ስፖርት ተወዳጇን ጋዜጣችን ነገ ቅዳሜ ጠብቋት ሊግ ስፖርት ጋዜጣ 20ኛ ዓመቷን ልትይዝ ተቃርባለች፤ ዘወትር ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ይህቺው ተወዳጇ ጋዜጣ ነገ እንደተለመደው ገበያ ላይ ስትውልም በሀገር ውስጥ እትሟ ለኢትዮጵያ ቡና በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ከወልቂጤ ከተማ በመምጣት ፊርማውን ለማኖር የቻለው ጫላ ተሺታ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽን ሰጥቷል።

ሊግ ስፖርት፤ ሊግ ስፖርት፤ ሊግ ስፖርት
ተወዳጇን ጋዜጣችን ነገ ቅዳሜ ጠብቋት
ሊግ ስፖርት ጋዜጣ 20ኛ ዓመቷን ልትይዝ ተቃርባለች፤ ዘወትር ቅዳሜ ለንባብ የምትበቃው ይህቺው ተወዳጇ ጋዜጣ ነገ እንደተለመደው ገበያ ላይ ስትውልም በሀገር ውስጥ እትሟ ለኢትዮጵያ ቡና በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ከወልቂጤ ከተማ በመምጣት ፊርማውን ለማኖር የቻለው ጫላ ተሺታ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽን ሰጥቷል።
አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና ፈራሚ ጫላ ተሺታ ከሰጣቸው አስተያየቶች ውስጥም ወደ ደቡብ አፍሪካ በፕሮፌሽናል ተጨዋችነት ለመጫወት ስላመራው አቡበከር ናስር ተጠይቆ “በአቡበከር ናስር መንፈሳዊ ቅናት አድሮብኛል” የሚል ምላሽ የሰጠ ሲሆን በባህርማዶ ዘገባዋ ደግሞ ገብርሄል ጀሱስ አርሰናልን ወደ ተስፋው ምድር ያደርሰው ይሆን? በሚል እንዲሁም ቼልሲ ጥርስ የሌለው አንበሳ ነው ስለመባሉ እና ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ የቁልቁለት ጉዞ የምትሎት ይኖራል።
ሊግ ስፖርት ሌሎች ምርጥ ምርጥ መረጃዎችንም በነገው እትሟ ይዛሎት ትቀርባለች።
ሊግ ስፖርትን ሁሌ ያንብቧት፤ ይወዷታል።
የሊግ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅም ይህንን ይመስላል።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P