ሊግ ስፖርት ቅዳሜስ በእትሟ በምን መልኩ ትቀርብ ይሆን?
የሁለት አስርት ዓመታትን ዕድሜ ልታስቆጥር የአንድ ዓመት ዕድሜ የሚቀራት ተወዳጇ ጋዜጣዎ ሊግ ስፖርት ነገም ቅዳሜ ውድ አንባቢዎቿ በሚጠብቋት መልኩ ለንባብ በመቅረብ ልታስደስቶት ከጫፍ ደርሳለች፡፡
የእርስዎ እና የእኛ የሆነችው ጋዜጣዎ ነገስ ገበያ ላይ ስትውል ምን ምን ጉዳዮችን ይዛሎት ትቀርብ ይሆን?
ሊግ በሀገር ውስጥ ዘገባዋ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉን አስመልክቶ የዓምናውን ሻምፒዮና ፋሲል ከነማን ከረቱት የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ቡድናችን ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ የሆነውና የድሉን ግብ ያስቆጠረው ኤልያስ አህመድ ፋሲል ከነማን ማሸነፋችን አያስገርምም ሲል ኢትዮጵያ ቡናን ድል ባደረጉበት ግጥሚያ ሁለት ግቦችን ለክለቡ ወላይታ ድቻ ያስቆጠረው ስንታየሁ መንግስቱ ደግሞ ቡናን መርታታችን አያስኮፍሰንም ሲል አስተያያቱን ሰጥቷል፡፡
ሊግ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ነገ ከሚጠበቁት ጨዋታዎች መካከል ቼልሲና ማንቸስተር ዩናይትድ ስለሚያደርጉት ጨዋታ ስለ በርናንዶ ሲልቫና ፖቸቲኖ እንደዚሁም በርካታ የሚወዷቸውን ሌሎች መረጃዎችን ለእናንተ በማስኮምኮም ቀኑን በጥሩ ሁኔታ እንዲያሳልፉ ዝግጅቷን አጠናቃለች፡፡
ሊግ ስፖርት ፈፅሞ አታምልጦት፤ የሊግ ስፖርት የነገው የፊት ለፊት ምስልም ይህንን ይመስላል፡፡
ሊግ ስፖርት ቅዳሜስ በእትሟ በምን መልኩ ትቀርብ ይሆን? የሁለት አስርት ዓመታትን ዕድሜ ልታስቆጥር የአንድ ዓመት ዕድሜ የሚቀራት ተወዳጇ ጋዜጣዎ ሊግ ስፖርት ነገም ቅዳሜ ውድ አንባቢዎቿ በሚጠብቋት መልኩ ለንባብ በመቅረብ ልታስደስቶት ከጫፍ ደርሳለች፡
ተመሳሳይ ጽሁፎች