ሊግ ስፖርት ዳግም ብቅ ብላለች፤ ቅዳሜ ይጠብቋት
ለዓለም ከፍተኛ ስጋት በነበረው እና ወደ አገራችንም ገብቶ በነበረው ኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለሳምንታት ተቋርጣ የነበረችው ተወዳጇ ጋዜጣዎ ሊግ ስፖርት ነገ ቅዳሜ ዳግም ለንባብ ልትበቃሎት ብቅ ብላለች፤ ሊግ ስፖርት ነገ በገበያ ላይ ስትውልም ከሀገር ውስጥ እና ከባህር ማዶ የተሰናዱ ዘገባዎችን ታቀርብሎታለች፡፡
ከሀገር ውስጥ የታላቁን የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ታሪካዋ ዳታ የሚዳስሰው ወድቆ የተነሳው ባንዲራ ታሪክ የሚለውን ስናቀርብሎት ሌላው ደግሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንና የሰበታ ከተማ ክለብ የመሀል ሜዳ ተጨዋች የሆነውን ታደለ መንገሻን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ እና ሌሎችንም ጥያቄዎች አቅርበንለት ምላሹን ሰጥቶናል፤ ተከታተሉት፡፡
ሊግ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዋም ኩቲኒኦ ወደ ሊቨርፑል የማይመለስበት ምክንያት ምንድንነው? የአርሰናሉ ኦባምያንግ እስካሁን ሚናው አለየለትም በሚል እንደዚሁም ደግሞ የፓትሪክ ቬየራ የሲቲ ታማኝነትን አስመልክቶ እና ሌሎች የሚወዷቸው ምርጥ ዘገባዎች ቀርቦላታል፡፡ ሊግ አታምልጦት፡፡
ሊግ ስፖርት ዳግም ብቅ ብላለች፤ ቅዳሜ ይጠብቋት ለዓለም ከፍተኛ ስጋት በነበረው እና ወደ አገራችንም ገብቶ በነበረው ኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለሳምንታት ተቋርጣ የነበረችው ተወዳጇ ጋዜጣዎ ሊግ ስፖርት ነገ ቅዳሜ ዳግም ለንባብ ልትበቃሎት ብቅ ብላለች፤
ተመሳሳይ ጽሁፎች