ሊግ ስፖርት ጋዜጣን በቅዳሜ እትሟ ጠብቋት
የ20ኛ ዓመቷን ለመያዝ እየተንደረደረች የምትገኘው ተወዳጇ ጋዜጣዎ ሊግ ስፖርት በነገው ዕለት ለንባብ ትቀርባለች።
በአዲስ ዓመት ዋዜማ ለንባብ የምትቀርበው ይህቺው ጋዜጣዎም በነገው ዕለት ለንባብ ስትቀርብም በሀገር ውስጥ እትሟ የባንክ አብዮቱን ያቀጣጠለው አማራ ባንክና የጣና ዋንጫ ተጣምረዋል በሚል ዘገባ መስከረም 6 በባህርዳር ከተማ ስለሚጀመረው የአማራ ባንክ ጣና ዋንጫ ሰፊ ዘገባ ይዘናል።
ሊግ ስፖርት ሌላዋ ዘገባዋ ዋልያዎቹ ለቻን አፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን በማስመልከት የቡድኑ ተጨዋች ጋቶች ፓኖም ይናገራል።
ሊግ ስፖርት ሌላ ዘገባዋ ማንቸስተር ሲቲ ከቶተንሃም ጋር ስለሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታና ሌላም የሚወዱትን ዘገባ ይዛሎት ትቀርባለች።
ሊግ ስፖርት አታምልጦት፤ የሊግ ስፖርት ጋዜጣ የነገው እትሟም ይህን ይመስላል።