ሊግ ስፖርት ጋዜጣን በገበያ ላይ
ቅዳሜ ጠብቋት
ሊግ ስፖርት ጋዜጣ 20ኛ ዓመቷን ልትደፍን የአንድ ዓመት ዕድሜ ነው የቀራት፤ ሊግ ስፖርት በእስከዛሬና ሳታቋርጥ እያወጣች ባለው እትሟ ተወዳጅና ተናፋቂ የሆነች ጋዜጣ ስትሆን በዕለተ ቀኗ ቅዳሜ ለንባብ ስትበቃም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህርማዶ ዘገባዎችን በማጣመር ለእርስዎ አመቺ በሆነ መልኩ ይዛሎት ትቀርባለች።
ሊግ ስፖርት በነገዋ የቅዳሜ እትሟም በሀገር ውስጥና በባህርማዶ ዘገባዎች ላይ ያተኮረ መረጃን የምታስኮመኩሞት ሲሆን በሀገር ውስጥ ኢትዮ ኤሌክትሪክን ከከፍተኛው ሊግ ወደ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ እንዲሸጋገር ካስቻሉት ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ምንያህል ተሾመ /ቤቢ/ ስለ ቡድናቸው ሊጉን መቀላቀሉ ስለ ራሱና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየቱን ሰጥቷል። ምንያህል ከሰጣቸው ምላሾች መካከልም ስለ ራሱ ከተጠየቀው ውስጥ “እግር ኳስን ጠግቤ አልተጫወትኳትም” የሚል ይገኝበታል።
ሊግ ስፖርት በሀገር ውስጥ ሌላ ይዛሎት የቀረበችው ዘገባ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር አቻ መለያየታቸውን ተከትሎና ስለ ቡድናቸው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎ የሲዳማ ቡናው የኮሪደር ስፍራ ተጨዋች መሀሪ መና ጥያቄ ቀርቦለት ምላሽንም ሰጥቷል።
መሀሪ መና ለጋዜጣው ከሰጣቸው አስተያየቶች ውስጥም ከቡና ጋር ስላደረጉት ጨዋታ “የአቻ ውጤቱ አይገባንም፤ ኢትዮጵያ ቡናንም ማሸነፍ ነበረብን” ሲል በሌላው አስተያየቱ ደግሞ “አስፈሪው ሲዳማ ቡናን በሁለተኛው ዙር ላይ እንመለከታለን” ሲልም ይናገራል። መሀሪ ከራሱ ብቃት ጋር በተያያዘም
“በእግር ኳሱ የእኔ ደካማው ጎን በአንድ እግሬ ብቻ ኳሱን መጫወቴ ነው” ሲልም ሀሳቡን አቅርቧል።
ሊግ በባህርማዶ ዘገባዋም ነገ ለንባብ ስትቀርብ የተለያየ መረጃዎችንም ይዛሎት ትቀርባለች።
ከእነዛ መካከልም ሊቨርፑል ለምን የዋንጫ እድል ተሰጠው? ኦዚል ዳግም ውዝግብ ውስጥ ስለመግባቱ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ታሪክ መስራቱን ስለመቀጠሉ፣ ኦዴጋርድ የአርሴናል ብርታት ስለመሆኑ እና ሌሎችንም መረጃዎች በማካተት ነገ ከእጅዎ ለንባብ ትቀርባለች።
ሊግ ስፖርት አታምልጦት፤ ይወዷታል።
የሊግ ስፖርት የነገው የፊት ለፊት ገፅም ይህንን ይመስላል።
ሊግ ስፖርት ጋዜጣን በገበያ ላይ ቅዳሜ ጠብቋት ሊግ ስፖርት ጋዜጣ 20ኛ ዓመቷን ልትደፍን የአንድ ዓመት ዕድሜ ነው የቀራት፤ ሊግ ስፖርት በእስከዛሬና ሳታቋርጥ እያወጣች ባለው እትሟ ተወዳጅና ተናፋቂ የሆነች ጋዜጣ ስትሆን በዕለተ ቀኗ ቅዳሜ ለንባብ ስትበቃም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህርማዶ ዘገባዎችን በማጣመር ለእርስዎ አመቺ በሆነ መልኩ ይዛሎት ትቀርባለች።
ተመሳሳይ ጽሁፎች