ሊግ ስፖርት ጋዜጣ በአዲሱ ዓመት
እንኳን አደረሳችሁ የረጅም ዓመታት ጊዜን ያስቆጠረችሁ የእርስዎ እና የእኛ የሆነችው ሊግ ስፖርት ጋዜጣዎ በአዲሱ ዓመትም የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህርማዶ እግር ኳስ ዘገባዎችን ልታስነብቦት ዝግጁ ነች።
ሊግ በነገው እትሟም በሀገር ውስጥ ፋሲል ከነማና ኢትዮጵያ ቡና በሚያደርጓቸው የሳምንቱ የኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ዙሪያ ከሁለቱ ቡድን ተጨዋቾች ጋር ቆይታ አላት። የፋሲሉ አብዱልከሪም መሐመድ በሜዳችን ከሱዳኑ አል ሂላል ባደረግነው ጨዋታ ሁለት ግብ ማስተናገዳችን ድክመታችንን ቢያሳይም ጨዋታው ገና አልተጠናቀቀም ወደ ተከታዩ ዙር የምናልፍበት ዕድሉ አለን ሲል የቡናው ወንድሜነህ ደረጄ ደግሞ በጥሩ ጨዋታ ወደ ተከታዩ ዙር እናልፋለን ይላል።
ሁለቱ ተጨዋቾች ሌሎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም ምላሽን ሰጥተዋል። ተከታተሏቸው።
ሊግ በቅዳሜ ጋዜጣዋ በባህርማዶስ ምን ዘገባን ታስነብቦት ይሆን?
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አርሰናልን በተመለከተ መድፈኞቹ ያገግሙ እንደሆነ ቶተንሃምን በሚመለከት ከቼልሲ ስለሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ማንቸስተር ዩናይትድን ይታደግ እንደሆነና በስፔን ላሊጋ ደግሞ ስለ ባርሴሎና መፍረክረክ መረጃ ቀርብሎታል።
ነገ ከሊግ ጋር ቀጠሮዎን ያድርጉ።
የሊግ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህን ይመስላ
https://t.me/Leaguesport