ሊግ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ቅዳሜም በገበያ ላይ
ጋዜጣዋ 20ኛ ዓመቷን ልትደፍን የአንድ ዓመት ዕድሜ ነው የቀራት፤ ተወዳጅና ተናፋቂም ጋዜጣ ናት።
ሊግ ስፖርት እንደተለመደው በዕለተ ቀኗ የተለያዩ የሀገር ውስጥና የባህርማዶ ዘገባዎችን በማጣመር ይዛሎት የምትቀርብ ሲሆን በነገው የቅዳሜ እትሟም በሀገር ውስጥ ዘገባ በሸገር ደርቢው ቅ/ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን በሰፊ የግብ ልዩነት ማሸነፉን ተከትሎ የቡድኑ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች እና ከተቆጠሩት አራት ግቦች መካከልም አንዱን ያስቆጠረው አቤል ያለው “በኢትዮጵያ ቡና ላይ ያስቆጠርናቸው አራት ግቦች ቢያንስ እንጂ የሚበዛ አይደለም” ብሎ ሲናገር ከዛ ውጪም በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያም ይናገራል። ሊግ ስፖርት ሌላ ይዛሎት የምትቀርበው ዘገባ የምንጊዜውም የቻምፒየንስ ሊግ ምርጡ ተጨዋች ክሊራንስ ሲዶርፍ እና የቻምፒዮንስ ሊጉ ዋንጫ አዲስ አበባ ስለመምጣቱም ዘገባ አላት።
ሊግ ስፖርት በባህርማዶ ዘገባዋም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የዋንጫውን ባለቤት ስለሚጠቁመው የማንቸስተር ሲቲና የሊቨርፑል ተጠባቂ ጨዋታ፣ ማን. ዩናይትድን ማን ይታደገው በሚለው መረጃና የተለያዩ መረጃዎችንም ይዛሎት ትቀርባለች።
ሊግ ስፖርት አታምልጦት፤ ይወዷታል።
የሊግ ስፖርት የነገው የፊት ለፊት ገፅም ይህንን ይመስላል።
ሊግ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ቅዳሜም በገበያ ላይ ጋዜጣዋ 20ኛ ዓመቷን ልትደፍን የአንድ ዓመት ዕድሜ ነው የቀራት፤ ተወዳጅና ተናፋቂም ጋዜጣ ናት።
ተመሳሳይ ጽሁፎች