ሊግ ስፖርት ጋዜጣ ቅዳሜ ለንባብ ስትቀርብም በሀገር ውስጥ አምዷ፦
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን በመምራት ላይ ከሚገኘው የኢትዮጵያ መድን ተጨዋቾች ውስጥ ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑሪ ስለ ቡድናቸው እና ስለ ራሱ ይናገራል።
አቡበከር ወይንም ደግሞ በልጅነቱ ዕድሜ ይጠራበት በነበረው ቫንደርሳር ስም ይጠራ የነበረው ይኸው ተጨዋች “በሊጉ ሁሉም ከእዚህ በኋላ ለእኛ ጠንክሮ ስለሚመጣ በቂ ምላሽ ለመስጠት ተዘጋጅተናል/ ሲል ይኸው ተጨዋች በሌላ አስተያየቱ “መድንም ሆነ አሰልጣኝ ገ/መድህን ሀይሌ ሶስታችንን ግብ ጠባቂዎች ከሀገር ውስጥ መርጠውን እየተጠቀሙብን መሆኑ ለሌላው ትምህርት ሰጪ ነው” ብሎም ይናገራል።
ሊግ ስፖርት በባህርማዶ ዘገባዎቿም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶና ሌላም ዘገባ አላት ከእነዛ መካከልም የሊጉን ውድድር ስለሚመራው አርሰናልም ይህን ዘገባ በነገው ዕለት ያንብቡ የአርሴናሎቹ አጥቂዎች በወሳኝ መለኪያዎች ሲነፃፀሩ በሚለው ፅሁፍ ዙሪያ ንኬቲያክ ከጄሱስን ጨምሮ ጥሩ መረጃን ያገኙበታል።
ሊግ ስፖርት የእርስዎ ናት፤ አታምልጦት፤ ይወዷታል።
የሊግ ስፖርት የነገው የፊት ለፊት ገፅም ይህንን ይመስላል።