Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ሐዋሳ ከተማን ወደ ቀድሞ ውጤታማነቱ የሚመለስ ቡድን አለን” በቃሉ ገነነ /ሐዋሳ ከተማ/

አዳማ ከተማን በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት በመልቀቅ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ለሁለት ጊዜ ላነሳው ሐዋሳ ከተማ በመጫወት ጥሩ እንቅስቃሴን እያሳየ የሚገኘው በቃሉ ገነነ ቡድናቸው በዘንድሮ የሊጉ ተሳትፎ ጥሩ ውጤት እንደሚያመጣና የቀድሞውንም የሐዋሳ ከተማን ውጤታማ ቡድን ዳግም እንደሚመልሱ ከሊግ ስፖርት ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቆይታ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

ሐዋሳ ከተማ በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎው እስካሁን ባደረጋቸው የዘጠኝ ሳምንት ጨዋታዎች በ14 ነጥብ በስደስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከእዚሁ ክለብ የሊጉ ተሳትፎ እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ተጨዋቹን አናግረነው የሚከተሉትን ምላሾች ሰጥቶናል፡፡

 

በዘጠነኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታ አርባምንጭ ከተማን ስለማሸነፋቸውና በጨዋታው ላይ ስለነበረው ፉክክር

“የአርባምንጭ ከተማና የእኛ የዘጠነኛው ሳምንት  ጨዋታ የደቡብ ደርቢ ስለነበር ከፍተኛ ፍትጊያና ጥሩም ፉክክር የነበረበት ነው፤ ሁለታችንም ጨዋታውን ለማሸነፍ እስከመጨረሻው ሰዓት ድረስም ተፋልመንበታል፤ ያም ሆኖ ግን ያገኘነውን ጎል የማስቆጠር እድል እኛ ስለተጠቀምንበትና ካለፈው ጨዋታም ስለተማርን አሸናፊ ለመሆን ችለናል፤ የድል ውጤቱም ለቡድናችን ይገባዋል”፡፡

ከአርባምንጩ ድል በፊት ስለነበረው የቡድናቸው ጉዞ

“ቀድሞ በነበረው የስምንት ሳምንታት ጉዞአችን ያስመዘገብነውን ነጥብ በውጤት ደረጃ ስናየው ብዙ አርኪ አይደለም፤ ነገር ግን ከስተታችን በመማርና ከአሰልጣኛችንም ዘርሃይ ሙሉ ጋር በመነጋገር ከጨዋታ ወደ ጨዋታ   እየተሻሻልን ነው፤ በተለይም ደግሞ የግብ አጨራረስ ላይ ክፍተት ነበረብንና በእዛ ስፍራ ላይ መለወጥ መጀመራችን በጥሩ መልኩም የሚጠቀስልን ነው”፡፡

ሐዋሳ ከተማ ቀጣይ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ወደ አሸናፊነት ይመጣ እንደሆነ

“በእስካሁን ጨዋታዎቻችን ያስመዘገብነውን  የድምር ውጤት ለእኛ አይመጥነንም ብለን ስላሰብን ወደ አሸናፊነት መምጣቱማ የግድ ነው የሚለን፤ በአርባምንጩ ጨዋታም ይሄን ስኬት ጀምረነዋል፤ በቀጣይነትም እነዚህን ውጤቶች ለማምጣት ግን የምትሰራው ልምምድና በሜዳ ላይ የምታደርገው እንቅስቃሴም በየጨዋታው በጣም ፈታኝ ነውና ለእዛ በጣም ልትዘጋጅበት ይገባል፤ የዘንድሮ የሊግ ጨዋታዎች ከሁለት ቀን እረፍቶች በኋላ የሚደረጉ ናቸው፤ ቡድኖች በተቀራረበ ነጥብ ላይም የሚገኙ ናቸው፤ ዛሬ ተጫውተህ በነጋታው ልምምድንም ትሰራለህና ከእዚህ በኋላ በሚኖሩት ጨዋታዎችም ቡድናችን ከስህተቱ በመማር ወደ አሸናፊነት መንፈሱ ይመጣል”፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ተጫውተው በአቻ ውጤት ስላጠናቀቁት ጨዋታ

“ይሄ የሁለታችን ጨዋታ ጥሩ ፉክክር ቢታይበትም ግጥሚያውን ግን እኛ ማሸነፍ ነበረብን፤ ያገኘነውን የግብ እድል እንደ ሌሎች ጨዋታዎች አለመጠቀማችን ነው ጎድቶን ግጥሚያውን በአቻ ውጤት ያጠናቀቅነው፤ በዕለቱ ጨዋታ የእኛ ቡድንጎል ጋር መድረስ መቻሉ ለእኛ ትልቅ ነገር ነው፤ ይሄንን በቀጣይነት ልናስኬደውና የግብ እድሎቹንም ልንጠቀምባቸው ይገባል፤ ስለ ተጋጣሚያችን የአዲስ አበባ ከተማ አቋም በተመለከተ አሪፍ ቡድን ነው ያላቸው፤ ጥሩ ኳስን ይጫወታሉ፤ የያዟቸው ልጆችም ቡድኑን የሚጠቅሙ ናቸው”፡፡

ሐዋሳ ከተማ ስላላቸው ጥንካሬና ክፍተት ጎን

“ስለ ጠንካራ ጎናችን ካነሳን መጀመሪያ ላይ የማስቀምጠው ቡድኑ በአብዛኛው የተገነባው በወጣት ተጨዋቾች ላይ መሆኑና ሁሉም አቅሙን ባልሰሰተ መልኩ ተሯሩጦ የሚጫወት መሆኑ ነው፤ ተጨዋቹ ለነገ የኳስ ህይወቱም ብሎ ተግቶ መስራቱና  ከአሰልጣኛችን በሚሰጠን መመሪያ መሰረትም በምን መልኩ መጫወት እንዳለብን እንደ ቡድን መነጋገር፣ መተጋጋዝና መደማመጥ መቻላችን ያለንን ጥንካሬ ያሳያል፤ ያለብን ክፍትት ጎንን በተመለከተ ደግሞአንድ ቡድን ሁሌም ሙሉ አይሆንም፤ ክፍተት ጎንን ትላልቅ ቡድኖችንም ይገጥማችኋል፤ ከአጨራረስ ውጪ በፋሲሊቲ ደረጃ አንድ አንድ ያልተሟሉልን ነገሮች ስላሉ እዛ ላይ ቡድኑ በሚገባ መስራት ቢችል በሞራል ደረጃ ብዙ ነገሮችን ስለሚያግዘን ሐዋሳ ከተማ የተሻለ ደረጃ ላይ ይደርሳል”፡፡

ስለ አሰልጣኛቸው ዘርዐይ ሙሉ

“እንደ ኮች በስራው ጥሩ ነገርን እያደረገልን ነው የሚገኘው፤ በወጣት ተጨዋቾች ላይ ያለው እምነትም ጥሩ ነው፤ እኛም የእሱን ታክቲክ እየተገበርንለትምነውና በእዚህ መልኩ አብረን እየተጓዝን ነው”፡፡

በቋሚ ተሰላፊነት ለቡድኑ ስለመጫወቱ

“ይሄን የመሰለፍ እድል ያገኘሁት ሁሌም ከእኔ የሚጠበቀውን ነገር በሜዳ ላይ እያደረግኩኝ ስለሆነ ነው፤ በእዚሁ አሰልጣኝ አምና ተመርቼ የሚሰጠኝን ታክቲክ ልሰራ በመቻሌ እሰለፍ ነበር፤ አሁንም ይኸው አሰልጣኝ በልምምድ ሜዳ ላይና በጨዋታ ወቅት ከማሳየው ነገር ተነስቶ በድጋሚ አሰልፎ እያጫወተኝ ይገኛል፤ ለቡድኑ ተሰልፌ እንድጫወትም የምንከተለው አጨዋወትም በጣም ተመችቶኛል”፡፡

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮኑን ዋንጫ ማን ያነሳው እንደሆነና እነሱም ስለሚያመጡት ውጤት

“ሻምፒዮናነቱን በሚመለከትአሁን ላይ በእዚህ የአቋም ደረጃ ላይ ነኝ፤ አሸናፊ ለመሆንም ምቾት ተሰምቶኛል ብሎ የደመደመ ክለብ ስለሌለ ይሄ ነው ብለህ የምታስበው ቡድን ማንም የለም፤ ወራጅ ክለብንም በተመለከተ በተመሳሳይ ውድድሩ ገና በርካታ ጨዋታዎች ስላሉት ምንም የምትለው ነገር የለምና በእዚህ ደረጃ ነው ስለ ውድድሩ መግለፅ የምፈልገው፤ ስለ እኛም ቡድን ልናገር የምፈልገው አሁን ላይ ከመሪው ያለን የነጥብ ርቀት የአራት ነው፤ ዋናው ጠንክሮ መስራት ነው፤ ቢያንስ የደረጃ ተፎካካሪ ሆነን የምናጠናቅቅበትም እድሉ ይኖረናል”፡፡

በመጨረሻ…

“የእግር ኳስ ጨዋታ ብዙ  ውጣውረድ ያለው ነው፤ የዕለት አቋምህ ውጤትህንም ይወስናል፤ በኳሱ ውስጥ ደግሞ ማሸነፍ፣ መሸነፍና አቻ መውጣትም የሚያጋጠም ስለሆነ የኳሱ ትክክለኛ ደጋፊ ይሄን አውቆ ከአንተ ጎን ሊሆን ይገባልና ለእኛም ደጋፊዎች ሁሌም ደስታ እንዳለ ሁሉ ሀዘንም ሊያጋጥም ስለሚችል በዛ ስሜት ውስጥ ሆነው ቡድናችንን እስከ ሊጉ የመጨረሻ ቀን ድረስ እንዲያበረታቱን ሀሳቤን መግለፅ እፈልጋለው፤ እኛም እነሱን በውጤት እንክሳለን”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P