Google search engine

“መልበሻ ክፍል ውስጥም ይሁን ሜዳ ላይ በኸለኝነት የምናገረው ለክለቤ ውጤታማነት ስል ነው፤ ወደፊትም እቀጥልበታለሁ” ጌታነህ ከበደ /ቅዱስ ጊዮርጊስ/

በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሸገር ደርቢ ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስን ከኢትዮጵያ ቡና ጋር አገናኝቶ ቅዱስ ጊዮርጊሶች በሙሉዓለም መስፍን /ዴኮ/ አማካኝነት ባስቆጠሩት ብቸኛ ግብ 1ለ0 አሸንፈዋል፡፡ በሸገር ደርቢው ጨዋታ ቡናዎች በመጀመሪያው አጋማሽ በኳስ ቁጥጥሩ ተሽለውና በልጠው የተጫወቱ ቢሆንም በአጠቃላይ የጨዋታ እንቅስቃሴው ግን አልፎ አልፎ በተቃራኒ ቡድን የግብ ክልል ላይ የሚያገኟቸውን የግብ ዕድል ለመጠቀም አለመቻላቸው እና እንደዚሁም ደግሞ የተቃራኒ ቡድንንም የመከላከል አጨዋወትን አስከፍቶ የመጫወት እንቅስቃሴ ላይ የሚቀራቸው ነገር ስላለ በዛ ተጠቃሚ ሳይሆኑ ቀርተው ውጤትን ሊያመጡ አልቻሉም፤ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ደግሞ በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ቡድኑ በሚፈልገው መልኩ ለመጫወት ባይችልም በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ግን ቡድኑ በመረጠው የረጅም ጨዋታና ተጭኖም የመጫወት እንቅስቃሴው ላይ ከተጋጣሚው የተሻለ እና የግብ ሙከራም በማድረግ ጥሩ ሆኖ በመቅረቡ ጨዋታውን ለማሸነፍ ችሏል፤ በሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ ጌታነህ ከበደ /ሰብሮም/ ለቡድኑ ውጤታማነት ጉልህ ድርሻ እንደነበረው የክለብ አጋር ተጨዋቾቹን ቡድኑ በኳስ ቁጥጥር በተበለጠበት የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ የእልህ እና የብስጭት ስሜት በተቀሰቀሰበት መልኩ የአነሳሽነትን ባህሪ በማሳየት እና ተጨዋቾቹንም እየተናገረ ክለቡን ሊጠቅም የቻለበትን ሁኔታ የተመለከትን ሲሆን ከዛ ውጪም ለግብ ባይታደልበትም ጥሩ ጥሩ የጎል ሙከራዎችንም ሲያደርግም ነበርና የጌታነህ ሚና ከፍ ያለ ነበር፤ ይህንን የሸገር ደርቢ ጨዋታ አስመልክቶ እና በሌሎች ተዛማች ጉዳዮች ዙሪያ እንደዚሁም ደግሞ ከራሱም አቋም ጋር በተገናኘ ጌታነህ ከበደን ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ አናግሮት ነበርና ተጨዋቹ ምላሾቹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቷል፤ ተከታተሉት፡፡

ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን በሸገር ደርቢው አሸንፏል፤ በአንተ እይታ ጨዋታው እንዴት ይገለፃል?
ጌታነህ፡- የኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበረን ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ እነሱ ጥሩ ነበሩ፤ ከእኛ በተሻለ መልኩም ጨዋታውን ጥሩ ተንቀሳቅሰውበታል፤ ከእረፍት በኋላ ግን እኛ ተጭነን በመጫወት በፍጥነት እነሱ ኳስ እንዳይመሰርቱና እንዳይቆጣጠሩ በማድረግ ተሽለን ስለቀረብን ግጥሚያውን በአሸናፊነት ተወጥተነዋል፡፡
ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስን ለድል እንዲበቃ ያደረገው ዋንኛው እና ጠንካራ ጎኑ ምን ነበር?
ጌታነህ፡- ኢትዮጵያ ቡናን በሸገር ደርቢው ጨዋታ ስናሸንፍ ለእኛ በተለየ መልኩ ብዙ ረድቶናል የምለው ጠንካራ ነገር ባይኖረኝም የእረፍት ሰዓት ላይ የእነሱን ኳስ መስርቶ የመጫወት እንቅስቃሴን መቆጣጠርና በዛ በያዙት አጨዋወት ውስጥም ተጭነን ለመጫወት ከቻልን የሁለተኛው አጋማሽ ላይ ግጥሚያውን ለማሸነፍ የምንችልበት ዕድል እንደሚኖረን መነጋገር መቻላችን ያ ጠቅሞናል፤ በዛ ክፍለ ጊዜ ውስጥም ከበረኛ ጀምሮ ሁሉም ተጨዋች ምን ማድረግ እንዳለበት ተነግሮት ነበርና በተቻለው አቅም ሜዳ ላይ ተጭኖ መጫወቱን ለመተግበር ይሞክር ነበር፤ በተለይ በረኛችን ካለፈው ጊዜ ጨዋታ ጀምሮም በጥሩ ብቃት ላይም ይገኝ ነበርና ቡናም ላይ ላስቆጠርነው ጎል የእሱ አስተዋፅኦም ከፍተኛ ነበር፤ በረኛችን እንደ እኔ ሁሉ ተጭነን እንድናጠቃ በመፈለግ እሱ በረጅሙ የለጋልኝን ኳስም ነው እኔ ወደ ግብ ሞክሬው ኮርና እንዲሆን ካደረግኩት በኋላ ያ ግብም ሊቆጠር የቻለውና ቡድናችን በሁለተኛው አጋማሽ ከእነ ደጋፊው በጥሩ መነቃቃት ላይ ስለነበርም ነው ለድል ሊበቃ የቻለው፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡናን ከያዙት የጨዋታ እንቅስቃሴ አንፃር ከእናንተ ጋር ሲጫወቱ በምን መልኩ ተመለከትካቸው?
ጌታነህ፡- ኢትዮጵያ ቡና በሲቲ ካፑ ይዞት ከቀረበው አጨዋወት አኳያ በጣም ተሻሽሏል፤ ያኔ ትንሽ ቀርፈፍ ይሉ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ ፍጥነት ያለውን ጨዋታ በመጫወት እየተለወጡ መጥተዋል፡፡
ሊግ፡- ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበራችሁ የሸገር ደርቢው ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ እነሱ ኳስን በተቆጣጠሩበት ሰአት አንተ በራሳችሁ ልጆች በመበሳጨት ስትናገርና እጅህንም ስታወራጭባቸው ታይተሃል፤ ያን ያደረግክበት ምክንያት ምን ነበር?
ጌታነህ፡- በዛ ስሜት ውስጥ ሆኜ ተጨዋቾቻችንን ስናገር የነበረው ያለምክንያት አልነበረም፤ የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂዎች በጨዋታው ላይ ሶስት ሆነን ሳለ እኔ ብቻ የፊት መስመሩ ላይ ስለነበርኩ ነው ሁለቱን የመስመር አጥቂዎቻችን ጋዲሳ መብራቴና አቤል ያለውን ወደ ኋላ እየተመለሱ በሚጫወቱበት ሰዓት አትሽሹ ወደፊት ኑና ተጫወቱ በሚል እነሱን ስናገርና ስቆጣቸው የነበረው፡፡ ምክንያቱም እኛ ተጭነን እና እያጠበብን ከተጫወትን ቡና ኳስን መስርቶ የሚጫወት ቡድን ስለሆነ ይቸገራል ለማለት ነው ይሄን ሀሳቤን ለተጨዋቾች ስነግራቸው የነበረው፤ በእግር ኳስ ጨዋታ ኳስን መስርቶ የሚጫወት ቡድንን ተጭነህ ካልተጫወትክ ለአንተ ነገሮች ሁሉ አስቸጋሪ ይሆንብሃልና ለዛም ነው ስሜታዊ ሆኜ ስናገራቸው የነበረው፡፡ እኔ ደግሞ ሁሌም የምናገረው ለክለቤ ውጤታማነት ስል እንጂ ሌላ ምክንያት ኖሮኝ አይደለምና ወደፊትም ከመናገር ወደ ኋላ የምል አይነት ተጨዋች አይደለውም፡፡
ሊግ፡- በከዚህ ቀደሙ የኳስ ተጨዋችነት ህይወትህ ኢትዮጵያ ቡና ላይ ጎል በማግባት ብዙዎች ያውቁሃል፤ በሸገር ደርቢው ጨዋታ ላይ ግን ተደጋጋሚ ሙከራን ብታደርግም ጎል ለማግባት ሳትችል ቀርተሃል?
ጌታነህ፡- አዎን፤ አምና አብዛኛውን ጊዜ በጉዳት ላይ ነበርኩና ከሜዳም ስለራቅኩ ያንን ለማሳካት አልቻልኩም፤ ከዛ አንፃር ደግሞ ወደ ጎል አስቆጣሪነቱ በአንዴ በፍጥነት ለመምጣት ይከብዳልና ለሁሉም ነገር ጊዜ ይፈልጋል፤ ስለዚህም በዚህ በኩል ወደጎል አግቢነቱ አሁን ላይ ለመምጣት ጥረትን እያደረግኩ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበረን የሸገር ደርቢው ጨዋታ ጎል ባላገባም ቡድናችን በማሸነፉ ብቻ ጎል እንዳገባው አድርጌ ነው ራሴን የምቆጥረው፤ ጥሩ ጥሩ ጎል የማስቆጠር ሙከራዎችን አድርጌያለው፤ ጨዋታውንም በማሸነፋችን በጣም ተደስቻለው፡፡
ሊግ፡- እንደ ኢትዮጵያ ቡና ተቃራኒ ተጨዋችነትህ አንድ ነገር ልጠይቅህና….ቡና አሁን ይዞት የመጣው አጨዋወት ለየት ብሎብሃል? እንቅስቃሴውስ ጥሩ ነው ማለት ይቻላል?
ጌታነህ፡- ኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ብቻ አይደለም እኮ እንደዚህ እየተጫወተ ያለው፤ ከበፊት ጀምሮም ነው በምመለከተው ሁኔታ እንዲህ እየተጫወተ የሚገኘውና ለእኔ ለየት ያለብኝ ነገር ብዙም የለም፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ኳስን ይዞና መሰረት አድርጎም የሚጫወት ቡድን ነው፡፡ በሚያዋጣቸውም አጨዋወት ነው እየተጫወቱ የሚገኙት፡፡ ጥሩ እንቅስቃሴም እያደረጉ ነው ያሉት፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም የዚህ እንቅስቃሴ ተፅዕኖ አድሮበትም ጥሩ ውጤት አምጥቶበታል፡፡ ያም ሆኖ ግን በተቃራኒነት ቡድኑ ከሚከተለው አጨዋወት አንፃር የሚቸገርበትም ሀኔታ አለ እንደዚህ አይነት አጨዋወት አፍሪካ ውስጥ ከሜዳ ወጥተህ ስትጫወት በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆንብህና ለዛ ሌላ የአጨዋወት ስልትን ልትፈጥርለት ይገባል፤ ምክንያቱም አንተ ኳስ ይዘህና መስርተህ ልትጫወት ስትል በቁመናና በተክለ ሰውነት እነሱ በጣም ትልልቅ ናቸውና አንተን ተጭነው በመጫወት ያስቸግሩሃል፡፡ እንደገና ደግሞ የኢትዮጵያ ሜዳዎች በጣም አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ እንደዚህ አይነት ጨዋታ ለመጫወት በፍፁም አይሆኑም፤ አሁን አዲስ አበባ ስቴድየም ራሱ ሰሞኑን ትንሽ ይሻላል እንጂ ሜዳው በፊት ውሃ አይጠጣ ስለነበር በጣም አስቸጋሪ ነበር፤ ኢትዮጵያ ቡና የባህርዳር፣ የመቐለ፣ የሐዋሳ ስቴድየም ላይ ቢጫወት እንጂ ሌላ ክልል ላይ ሄዶ ቢጫወት በጣም ይቸገራል፤ ስለዚህም ለቡናዎች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ክለቦች ተመልካቹ ጥሩ ኳስን ሁሌም እንዲመለከት ከተፈለገ አዲስ የተቋቋመው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኮሚቴ አሁን ላይ አጥሩን ብቻ ነው እያየ ያለውና የሜዳቸውን ጥራት እያየ ስላልሆነ እዛ ላይም ትኩረት ሊያደርግ ይገባል፤ በተለይ ቡናን አሁን በያዘው አጨዋወት የተወሰኑ የፕሪምየር ሊግ ሜዳዎች በጣም ይጎዳዋል ብዬም አስባለሁ፡፡
ሊግ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ከባህርዳር ከተማ ባደረገው ጨዋታ የተጨዋች ቅያሪ ሰአት ላይ አሰልጣኙን የመቃወም ነገር አሳይተህ ነበር፤ ያን ለምን ነበር ያደረግከው?
ጌታነህ፡- አዎን፤ መቃወሜን ሁሉም ሰው የተመለከተው ነበርና ያን ፈፅሞ አልክድም፡፡ በዛን እለት ጨዋታ ቡድናችን የሚጫወተው በሜዳውና በደጋፊው ፊት ነበርና በሜዳው የሚጫወት ቡድን ደግሞ ከተጋጣሚው ክለብ በሁሉም ነገር ተሽሎ መቅረብ አለበት የሚል እምነት ስለነበረኝ ነው የእኛ ቡድን በሁለት የተከላካይ አማካዮች ወደሜዳ ገብቶ ይጫወት ስለነበርና በተጋጣሚው ቡድንም በኳስ ቁጥጥር እየተበለጠ በሄደበት ሰዓት ነው እኔ መቃወምን የጀመርኩት፤ በዓለም ላይ አሁን የተከላካይ አማካይ የሚል ተጨዋች እየቀረ መጥቷል፡፡ ለምሳሌ ማንቸስተር ሲቲን ብትወስድ እነሱም ጋር ያ ቀርቷል፤ እኛ በቀደም ስንጫወት በሁለት የተከላካይ አማካይ ነበርና ቡድናችን እንዳለ ተከላካይ ሲሆን ጊዜ እኔ ወደኋላ እየተመለስኩ ነበር ኳሱን እየመሰረትኩ ለመጫወት ስሞክር የነበረውና በመሀል ተጨዋቾቻችን አካባቢ ያን ለማድረግ አለመቻላችን ነው እኔን ሲያበሳጨኝ የነበረው፤ ባህር ዳሮች ያንን ተጠቅመው የማሸነፍ እድሉን አላገኙም እንጂ ከእኛ በተሻለ መልኩ ነው የተጫወቱት፤ በዛን ጊዜም ነው እኔ ኳስ የሚጫወት ሰው ይግባ በማለት የተቃወምኩት፤ ምክንያቱም እኔ አሁን ቤንች ብሆን ምንም ማለት አይደለም እንኳን እኔ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ላይ ምርጡ አጥቂ ሰርጅዮ አጉዌሮን ብትወስድ አንድ ቀን ይጫወታል አንድ ቀን ደግሞ ላይጫወትም ወይንም ደግሞ ተቀይሮም ሊወጣ ይችላልና ማንም ከማንም ስለማይበልጥ የሚሻለው ልጅ እንደዚሁም ደግሞ መሀል ላይ ጥሩ የሚጫወት ልጅ ይገባ ለማለት ብዬ ነው የተቃወምኩት፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ አንተ የምትጫወትበት ቡድን በኳስ ቁጥጥር ሲበለጥ ሁሌም ትበሳጫለህ ማለት ነው?
ጌታነህ፡- አዎን፤ በጣም ነው የምናደደው፤ በቡና ጨዋታም ተመልክተካል፤ ባለፈው ከባህር ዳር ከተማ ጋር በነበረን ጨዋታም መልበሻ ክፍል ሄጄ ከእነ ጋዲሳ ጋር ጭምር ነው ተጭነን እንጫወት በሚል ሀሳብ ለመደባደብ የሞከርኩት፤ ኳስን ስጫወት ሁሌም የሚሰማኝን ነገር ከመናገር ወደ ኋላ አልልም፤ አሰልጣኙንም ቢሆን እናገራለሁ፡፡
ሊግ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ውስጥ በመናገርህ ቡድናችሁ ላይ ለውጥ አይተህበታል….? ቅዱስ ጊዮርጊስስ በእንቅስቃሴ ደረጃ ከዚህ በኋላ በጣም ይሻሻላል..?
ጌታነህ፡- በጣም፤ የኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበረን ጨዋታ በሁለተኛው አጋማሽ ተጭነን በመጫወታችን ነው አንዱ የለውጡ አካል፤ ይህ ለውጥ የመጣውም በእረፍት ሰዓት ላይ በቡድናችን አጨዋወት ላይ ለመነጋገር በመቻላችን ነው፡፡ የአብስራ ከጉዳት መልስ ተቀይሮ የገባበት ሁኔታ ቢኖርም እኔ በተደጋጋሚ እል የነበረው እንደ እሱና ሌላው ጉዳት ላይ እንደነበረው አሁን ላይ ደግሞ ወደሜዳ ወደተመለሰው አቤልን የመሳሰሉ ተጨዋቾች ተቀይረው ቢገቡ ተጭኖ መጫወቱ ላይ ብዙ ለውጥን ያመጣሉ ከማለት ነው በቡድናችን ውስጥ ከውጤት አንፃር ጥሩ ነገር እንዲፈጠር ከመፈለግ የምናገረው እና እነዛ ተጨዋቾች ባይገቡ ሁሉ ተጭኖ መጫወት በራሱ ስኬታማ ያደርግሃልና ያ ሊጠቅመን ችሏል፤ በቀጣዩ ጊዜ ደግሞ ቡድናችን የእነዚህን መሰል ተጨዋቾች ግልጋሎት ተጨዋቾቹ ሙሉ ጤነኛ ይሁኑለት እንጂ በአግባቡ የምንጠቀምባቸው ከሆነ ቡድናችን አሁን ከያዘው እንቅስቃሴ በጣሙን ነው የሚሻሻለው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ምርጥ አጥቂውን ጌታነህ ከበደን በበፊት አቋሙና ቁመናው እንደዚሁም ደግሞ በግብ አዳኝነቱ ዳግም እንመለከተዋለን?
ጌታነህ፡- በሚገባ፤ ከጉዳቴ አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ መቶ ፐርሰንት ድኜ ለመጫወት ከፍተኛ ትግልን እያደረግኩ ነው፤ በጤንነቴ 80% ላይም ነው የምገኘው፡፡ በቡድናችን ላይ ያለውን የአጥቂ ችግር በተመለከተ ሁሉም ይረዱኛል፤ ወደኋላ ተመልሼ የምጫወተው አሰልጣኙ ቀስ ብዬ እንድጫወትና ጉዳቱ እንዳይባባስብኝ ፈልጎ ነውና ወደበፊቱ አቋሜ በእርግጠኝነት መመለሴ አይቀሬ ነው፡፡
ሊግ፡- መቐለ 70 እንደርታ ፕሪምየር ሊጉን አሁንም መምራቱን ቀጥሏል፤ ቅዱስ ጊዮርጊሶችም በቅርብ ርቀት እየተከተሉት ይገኛል፤ ከዚህ አንፃር?
ጌታነህ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ የአንደኛው ዙር ውድድር ከመጠናቀቁ በፊት ከዚህ በኋላ ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች በሜዳው ላይ አሉት፤ ከመሪው ጋር ያለው የነጥብ ልዩነትም ሁለት ነው፤ ዘጠኝ ነጥብን አስበን ስለምንጫወት በቅርቡ የመሪነት እርከኑ ላይ እንቀመጣለን፡፡
ሊግ፡- የሊቨርፑል ደጋፊ ነህ ልበል?
ጌታነህ፡- አዎን፤ ያውም ቅልጥ ያልኩ ነዋ!
ሊግ፡- የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን አንተ የምትደግፈው ቡድን ሊያነሳ ነው? ወይንስ ገና ይቀረዋል?
ጌታነህ፡- የፕሪምየር ሊጉ ውድድር ባይጠናቀቅም፤ ገና 14 ጨዋታ ቢቀርም፤ የኳስ ነገርም ባይታወቅም ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ ማግኘቱ ፈፅሞ አይቀርም፡፡ አሁን ሁለተኛውን ክለብ ማንቸስተር ሲቲን በ19 ነጥብ ልዩነትም እየመራው ነው የሚገኘው፤ ዋንጫውን ለማረጋገጥ ጥቂት ጨዋታ ብቻም ይቀረዋልና አሁን ላይ የዋንጫውን አንዱን ጆሮ ጨብጦታል፤ ሁለተኛውን ጆሮ ደግሞ በቅርቡ ይጨብጥና እኛን በጣም ያስደስተናል፡፡
ሊግ፡- ሊቨርፑል የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ዘንድሮ ካነሳ ደስታህን በተለየ መልኩ የምትገልፅ ይመስልሃል?
ጌታነህ፡- አዎን፤ ከዛ በተሻለ መልኩ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስም የዘንድሮውን የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ስለሚያነሳ ድሉን በጋራ በአንድ ላይ አከብረዋለሁ፡፡
ሊግ፡- ወልዋሎ አዲግራትን በሰፊ ግብ ያሸነፈውን ሲዳማ ቡናን ነገ እሁድ ትገጥማላችሁ? ምን ውጤት ትጠብቃለህ?
ጌታነህ፡- ቅ/ጊዮርጊስ ከሲዳማ ቡና የሚያደርገው ጨዋታ ጥሩ ፉክክር የሚደረግበት ነው፤ ከዛ ውጪም ሁለታችንም ያለፈውን ጨዋታ አሸንፈን ከመምጣታችን አኳያም በጥሩ ስነ-ልቦናም ሆነን የምንቀርብበት ስለሆነ ያ ግጥሚያውን በጣም እንዲጠበቅ ያደርገዋል፤ በመጨረሻ የሚመዘገበው ውጤት ግን የእኛ ቡድን ሶስት ነጥብ ሲዳማ ቡና 0 ነጥብ የሚያገኙበት ይሆናል፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ…..?
ጌታነህ፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ክለቦች በስፖርታዊ ጨዋነቱ ላይ አስቀድመው የሰሩት ስራ በሸገር ደርቢው ጨዋታ ላይ ጥሩ ነገርን እንድንመለከትበት እያደረጉ ይገኛል፤ ከዛ ባሻገር ወደ ክልልም ሄዶ መልካም የሆኑ ነገሮችን እንድናይበትም እያደረገን ይገኛል፤ ሁለቱ ቡድኖች በሲቲ ካፑ ላይ ያሳዩት ነገርም ነው ወደ ክልል ሄዶም ኳስን በሰላምም እንድንጫወት እያደረጉን ያለውና ይሄ ስራቸው ይበል ያሰኛል፤ ሊመሰገኑም ይገባል፡፡

ፕሪምየር ሊግ የሸገር ደርቢ ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስን ከኢትዮጵያ ቡና ጋር አገናኝቶ ቅዱስ ጊዮርጊሶች በሙሉዓለም መስፍን /ዴኮ/ አማካኝነት ባስቆጠሩት ብቸኛ ግብ 1ለ0 አሸንፈዋል፡፡ በሸገር ደርቢው ጨዋታ ቡናዎች በመጀመሪያው አጋማሽ በኳስ ቁጥጥሩ ተሽለውና በልጠው የተጫወቱ ቢሆንም በአጠቃላይ የጨዋታ እንቅስቃሴው ግን አልፎ አልፎ በተቃራኒ ቡድን የግብ ክልል ላይ የሚያገኟቸውን የግብ ዕድል ለመጠቀም አለመቻላቸው እና እንደዚሁም ደግሞ የተቃራኒ ቡድንንም የመከላከል አጨዋወትን አስከፍቶ የመጫወት እንቅስቃሴ ላይ የሚቀራቸው ነገር ስላለ በዛ ተጠቃሚ ሳይሆኑ ቀርተው ውጤትን ሊያመጡ አልቻሉም፤ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ደግሞ በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ቡድኑ በሚፈልገው መልኩ ለመጫወት ባይችልም በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ግን ቡድኑ በመረጠው የረጅም ጨዋታና ተጭኖም የመጫወት እንቅስቃሴው ላይ ከተጋጣሚው የተሻለ እና የግብ ሙከራም በማድረግ ጥሩ ሆኖ በመቅረቡ ጨዋታውን ለማሸነፍ ችሏል፤ በሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ ጌታነህ ከበደ /ሰብሮም/ ለቡድኑ ውጤታማነት ጉልህ ድርሻ እንደነበረው የክለብ አጋር ተጨዋቾቹን ቡድኑ በኳስ ቁጥጥር በተበለጠበት የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ የእልህ እና የብስጭት ስሜት በተቀሰቀሰበት መልኩ የአነሳሽነትን ባህሪ በማሳየት እና ተጨዋቾቹንም እየተናገረ ክለቡን ሊጠቅም የቻለበትን ሁኔታ የተመለከትን ሲሆን ከዛ ውጪም ለግብ ባይታደልበትም ጥሩ ጥሩ የጎል ሙከራዎችንም ሲያደርግም ነበርና የጌታነህ ሚና ከፍ ያለ ነበር፤ ይህንን የሸገር ደርቢ ጨዋታ አስመልክቶ እና በሌሎች ተዛማች ጉዳዮች ዙሪያ እንደዚሁም ደግሞ ከራሱም አቋም ጋር በተገናኘ ጌታነህ ከበደን ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ አናግሮት ነበርና ተጨዋቹ ምላሾቹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቷል፤ ተከታተሉት፡፡
ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ ቡናን በሸገር ደርቢው አሸንፏል፤ በአንተ እይታ ጨዋታው እንዴት ይገለፃል?
ጌታነህ፡- የኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበረን ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ እነሱ ጥሩ ነበሩ፤ ከእኛ በተሻለ መልኩም ጨዋታውን ጥሩ ተንቀሳቅሰውበታል፤ ከእረፍት በኋላ ግን እኛ ተጭነን በመጫወት በፍጥነት እነሱ ኳስ እንዳይመሰርቱና እንዳይቆጣጠሩ በማድረግ ተሽለን ስለቀረብን ግጥሚያውን በአሸናፊነት ተወጥተነዋል፡፡
ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስን ለድል እንዲበቃ ያደረገው ዋንኛው እና ጠንካራ ጎኑ ምን ነበር?
ጌታነህ፡- ኢትዮጵያ ቡናን በሸገር ደርቢው ጨዋታ ስናሸንፍ ለእኛ በተለየ መልኩ ብዙ ረድቶናል የምለው ጠንካራ ነገር ባይኖረኝም የእረፍት ሰዓት ላይ የእነሱን ኳስ መስርቶ የመጫወት እንቅስቃሴን መቆጣጠርና በዛ በያዙት አጨዋወት ውስጥም ተጭነን ለመጫወት ከቻልን የሁለተኛው አጋማሽ ላይ ግጥሚያውን ለማሸነፍ የምንችልበት ዕድል እንደሚኖረን መነጋገር መቻላችን ያ ጠቅሞናል፤ በዛ ክፍለ ጊዜ ውስጥም ከበረኛ ጀምሮ ሁሉም ተጨዋች ምን ማድረግ እንዳለበት ተነግሮት ነበርና በተቻለው አቅም ሜዳ ላይ ተጭኖ መጫወቱን ለመተግበር ይሞክር ነበር፤ በተለይ በረኛችን ካለፈው ጊዜ ጨዋታ ጀምሮም በጥሩ ብቃት ላይም ይገኝ ነበርና ቡናም ላይ ላስቆጠርነው ጎል የእሱ አስተዋፅኦም ከፍተኛ ነበር፤ በረኛችን እንደ እኔ ሁሉ ተጭነን እንድናጠቃ በመፈለግ እሱ በረጅሙ የለጋልኝን ኳስም ነው እኔ ወደ ግብ ሞክሬው ኮርና እንዲሆን ካደረግኩት በኋላ ያ ግብም ሊቆጠር የቻለውና ቡድናችን በሁለተኛው አጋማሽ ከእነ ደጋፊው በጥሩ መነቃቃት ላይ ስለነበርም ነው ለድል ሊበቃ የቻለው፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡናን ከያዙት የጨዋታ እንቅስቃሴ አንፃር ከእናንተ ጋር ሲጫወቱ በምን መልኩ ተመለከትካቸው?
ጌታነህ፡- ኢትዮጵያ ቡና በሲቲ ካፑ ይዞት ከቀረበው አጨዋወት አኳያ በጣም ተሻሽሏል፤ ያኔ ትንሽ ቀርፈፍ ይሉ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ ፍጥነት ያለውን ጨዋታ በመጫወት እየተለወጡ መጥተዋል፡፡
ሊግ፡- ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበራችሁ የሸገር ደርቢው ጨዋታ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ እነሱ ኳስን በተቆጣጠሩበት ሰአት አንተ በራሳችሁ ልጆች በመበሳጨት ስትናገርና እጅህንም ስታወራጭባቸው ታይተሃል፤ ያን ያደረግክበት ምክንያት ምን ነበር?
ጌታነህ፡- በዛ ስሜት ውስጥ ሆኜ ተጨዋቾቻችንን ስናገር የነበረው ያለምክንያት አልነበረም፤ የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂዎች በጨዋታው ላይ ሶስት ሆነን ሳለ እኔ ብቻ የፊት መስመሩ ላይ ስለነበርኩ ነው ሁለቱን የመስመር አጥቂዎቻችን ጋዲሳ መብራቴና አቤል ያለውን ወደ ኋላ እየተመለሱ በሚጫወቱበት ሰዓት አትሽሹ ወደፊት ኑና ተጫወቱ በሚል እነሱን ስናገርና ስቆጣቸው የነበረው፡፡ ምክንያቱም እኛ ተጭነን እና እያጠበብን ከተጫወትን ቡና ኳስን መስርቶ የሚጫወት ቡድን ስለሆነ ይቸገራል ለማለት ነው ይሄን ሀሳቤን ለተጨዋቾች ስነግራቸው የነበረው፤ በእግር ኳስ ጨዋታ ኳስን መስርቶ የሚጫወት ቡድንን ተጭነህ ካልተጫወትክ ለአንተ ነገሮች ሁሉ አስቸጋሪ ይሆንብሃልና ለዛም ነው ስሜታዊ ሆኜ ስናገራቸው የነበረው፡፡ እኔ ደግሞ ሁሌም የምናገረው ለክለቤ ውጤታማነት ስል እንጂ ሌላ ምክንያት ኖሮኝ አይደለምና ወደፊትም ከመናገር ወደ ኋላ የምል አይነት ተጨዋች አይደለውም፡፡
ሊግ፡- በከዚህ ቀደሙ የኳስ ተጨዋችነት ህይወትህ ኢትዮጵያ ቡና ላይ ጎል በማግባት ብዙዎች ያውቁሃል፤ በሸገር ደርቢው ጨዋታ ላይ ግን ተደጋጋሚ ሙከራን ብታደርግም ጎል ለማግባት ሳትችል ቀርተሃል?
ጌታነህ፡- አዎን፤ አምና አብዛኛውን ጊዜ በጉዳት ላይ ነበርኩና ከሜዳም ስለራቅኩ ያንን ለማሳካት አልቻልኩም፤ ከዛ አንፃር ደግሞ ወደ ጎል አስቆጣሪነቱ በአንዴ በፍጥነት ለመምጣት ይከብዳልና ለሁሉም ነገር ጊዜ ይፈልጋል፤ ስለዚህም በዚህ በኩል ወደጎል አግቢነቱ አሁን ላይ ለመምጣት ጥረትን እያደረግኩ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበረን የሸገር ደርቢው ጨዋታ ጎል ባላገባም ቡድናችን በማሸነፉ ብቻ ጎል እንዳገባው አድርጌ ነው ራሴን የምቆጥረው፤ ጥሩ ጥሩ ጎል የማስቆጠር ሙከራዎችን አድርጌያለው፤ ጨዋታውንም በማሸነፋችን በጣም ተደስቻለው፡፡
ሊግ፡- እንደ ኢትዮጵያ ቡና ተቃራኒ ተጨዋችነትህ አንድ ነገር ልጠይቅህና….ቡና አሁን ይዞት የመጣው አጨዋወት ለየት ብሎብሃል? እንቅስቃሴውስ ጥሩ ነው ማለት ይቻላል?
ጌታነህ፡- ኢትዮጵያ ቡና ዛሬ ብቻ አይደለም እኮ እንደዚህ እየተጫወተ ያለው፤ ከበፊት ጀምሮም ነው በምመለከተው ሁኔታ እንዲህ እየተጫወተ የሚገኘውና ለእኔ ለየት ያለብኝ ነገር ብዙም የለም፡፡ ኢትዮጵያ ቡና ኳስን ይዞና መሰረት አድርጎም የሚጫወት ቡድን ነው፡፡ በሚያዋጣቸውም አጨዋወት ነው እየተጫወቱ የሚገኙት፡፡ ጥሩ እንቅስቃሴም እያደረጉ ነው ያሉት፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም የዚህ እንቅስቃሴ ተፅዕኖ አድሮበትም ጥሩ ውጤት አምጥቶበታል፡፡ ያም ሆኖ ግን በተቃራኒነት ቡድኑ ከሚከተለው አጨዋወት አንፃር የሚቸገርበትም ሀኔታ አለ እንደዚህ አይነት አጨዋወት አፍሪካ ውስጥ ከሜዳ ወጥተህ ስትጫወት በጣም አስቸጋሪ ነው የሚሆንብህና ለዛ ሌላ የአጨዋወት ስልትን ልትፈጥርለት ይገባል፤ ምክንያቱም አንተ ኳስ ይዘህና መስርተህ ልትጫወት ስትል በቁመናና በተክለ ሰውነት እነሱ በጣም ትልልቅ ናቸውና አንተን ተጭነው በመጫወት ያስቸግሩሃል፡፡ እንደገና ደግሞ የኢትዮጵያ ሜዳዎች በጣም አስቸጋሪዎች ናቸው፡፡ እንደዚህ አይነት ጨዋታ ለመጫወት በፍፁም አይሆኑም፤ አሁን አዲስ አበባ ስቴድየም ራሱ ሰሞኑን ትንሽ ይሻላል እንጂ ሜዳው በፊት ውሃ አይጠጣ ስለነበር በጣም አስቸጋሪ ነበር፤ ኢትዮጵያ ቡና የባህርዳር፣ የመቐለ፣ የሐዋሳ ስቴድየም ላይ ቢጫወት እንጂ ሌላ ክልል ላይ ሄዶ ቢጫወት በጣም ይቸገራል፤ ስለዚህም ለቡናዎች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ክለቦች ተመልካቹ ጥሩ ኳስን ሁሌም እንዲመለከት ከተፈለገ አዲስ የተቋቋመው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ኮሚቴ አሁን ላይ አጥሩን ብቻ ነው እያየ ያለውና የሜዳቸውን ጥራት እያየ ስላልሆነ እዛ ላይም ትኩረት ሊያደርግ ይገባል፤ በተለይ ቡናን አሁን በያዘው አጨዋወት የተወሰኑ የፕሪምየር ሊግ ሜዳዎች በጣም ይጎዳዋል ብዬም አስባለሁ፡፡
ሊግ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ከባህርዳር ከተማ ባደረገው ጨዋታ የተጨዋች ቅያሪ ሰአት ላይ አሰልጣኙን የመቃወም ነገር አሳይተህ ነበር፤ ያን ለምን ነበር ያደረግከው?
ጌታነህ፡- አዎን፤ መቃወሜን ሁሉም ሰው የተመለከተው ነበርና ያን ፈፅሞ አልክድም፡፡ በዛን እለት ጨዋታ ቡድናችን የሚጫወተው በሜዳውና በደጋፊው ፊት ነበርና በሜዳው የሚጫወት ቡድን ደግሞ ከተጋጣሚው ክለብ በሁሉም ነገር ተሽሎ መቅረብ አለበት የሚል እምነት ስለነበረኝ ነው የእኛ ቡድን በሁለት የተከላካይ አማካዮች ወደሜዳ ገብቶ ይጫወት ስለነበርና በተጋጣሚው ቡድንም በኳስ ቁጥጥር እየተበለጠ በሄደበት ሰዓት ነው እኔ መቃወምን የጀመርኩት፤ በዓለም ላይ አሁን የተከላካይ አማካይ የሚል ተጨዋች እየቀረ መጥቷል፡፡ ለምሳሌ ማንቸስተር ሲቲን ብትወስድ እነሱም ጋር ያ ቀርቷል፤ እኛ በቀደም ስንጫወት በሁለት የተከላካይ አማካይ ነበርና ቡድናችን እንዳለ ተከላካይ ሲሆን ጊዜ እኔ ወደኋላ እየተመለስኩ ነበር ኳሱን እየመሰረትኩ ለመጫወት ስሞክር የነበረውና በመሀል ተጨዋቾቻችን አካባቢ ያን ለማድረግ አለመቻላችን ነው እኔን ሲያበሳጨኝ የነበረው፤ ባህር ዳሮች ያንን ተጠቅመው የማሸነፍ እድሉን አላገኙም እንጂ ከእኛ በተሻለ መልኩ ነው የተጫወቱት፤ በዛን ጊዜም ነው እኔ ኳስ የሚጫወት ሰው ይግባ በማለት የተቃወምኩት፤ ምክንያቱም እኔ አሁን ቤንች ብሆን ምንም ማለት አይደለም እንኳን እኔ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ላይ ምርጡ አጥቂ ሰርጅዮ አጉዌሮን ብትወስድ አንድ ቀን ይጫወታል አንድ ቀን ደግሞ ላይጫወትም ወይንም ደግሞ ተቀይሮም ሊወጣ ይችላልና ማንም ከማንም ስለማይበልጥ የሚሻለው ልጅ እንደዚሁም ደግሞ መሀል ላይ ጥሩ የሚጫወት ልጅ ይገባ ለማለት ብዬ ነው የተቃወምኩት፡፡
ሊግ፡- በእግር ኳስ አንተ የምትጫወትበት ቡድን በኳስ ቁጥጥር ሲበለጥ ሁሌም ትበሳጫለህ ማለት ነው?
ጌታነህ፡- አዎን፤ በጣም ነው የምናደደው፤ በቡና ጨዋታም ተመልክተካል፤ ባለፈው ከባህር ዳር ከተማ ጋር በነበረን ጨዋታም መልበሻ ክፍል ሄጄ ከእነ ጋዲሳ ጋር ጭምር ነው ተጭነን እንጫወት በሚል ሀሳብ ለመደባደብ የሞከርኩት፤ ኳስን ስጫወት ሁሌም የሚሰማኝን ነገር ከመናገር ወደ ኋላ አልልም፤ አሰልጣኙንም ቢሆን እናገራለሁ፡፡
ሊግ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ ውስጥ በመናገርህ ቡድናችሁ ላይ ለውጥ አይተህበታል….? ቅዱስ ጊዮርጊስስ በእንቅስቃሴ ደረጃ ከዚህ በኋላ በጣም ይሻሻላል..?
ጌታነህ፡- በጣም፤ የኢትዮጵያ ቡና ጋር በነበረን ጨዋታ በሁለተኛው አጋማሽ ተጭነን በመጫወታችን ነው አንዱ የለውጡ አካል፤ ይህ ለውጥ የመጣውም በእረፍት ሰዓት ላይ በቡድናችን አጨዋወት ላይ ለመነጋገር በመቻላችን ነው፡፡ የአብስራ ከጉዳት መልስ ተቀይሮ የገባበት ሁኔታ ቢኖርም እኔ በተደጋጋሚ እል የነበረው እንደ እሱና ሌላው ጉዳት ላይ እንደነበረው አሁን ላይ ደግሞ ወደሜዳ ወደተመለሰው አቤልን የመሳሰሉ ተጨዋቾች ተቀይረው ቢገቡ ተጭኖ መጫወቱ ላይ ብዙ ለውጥን ያመጣሉ ከማለት ነው በቡድናችን ውስጥ ከውጤት አንፃር ጥሩ ነገር እንዲፈጠር ከመፈለግ የምናገረው እና እነዛ ተጨዋቾች ባይገቡ ሁሉ ተጭኖ መጫወት በራሱ ስኬታማ ያደርግሃልና ያ ሊጠቅመን ችሏል፤ በቀጣዩ ጊዜ ደግሞ ቡድናችን የእነዚህን መሰል ተጨዋቾች ግልጋሎት ተጨዋቾቹ ሙሉ ጤነኛ ይሁኑለት እንጂ በአግባቡ የምንጠቀምባቸው ከሆነ ቡድናችን አሁን ከያዘው እንቅስቃሴ በጣሙን ነው የሚሻሻለው፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ምርጥ አጥቂውን ጌታነህ ከበደን በበፊት አቋሙና ቁመናው እንደዚሁም ደግሞ በግብ አዳኝነቱ ዳግም እንመለከተዋለን?
ጌታነህ፡- በሚገባ፤ ከጉዳቴ አሁን ላይ ሙሉ ለሙሉ መቶ ፐርሰንት ድኜ ለመጫወት ከፍተኛ ትግልን እያደረግኩ ነው፤ በጤንነቴ 80% ላይም ነው የምገኘው፡፡ በቡድናችን ላይ ያለውን የአጥቂ ችግር በተመለከተ ሁሉም ይረዱኛል፤ ወደኋላ ተመልሼ የምጫወተው አሰልጣኙ ቀስ ብዬ እንድጫወትና ጉዳቱ እንዳይባባስብኝ ፈልጎ ነውና ወደበፊቱ አቋሜ በእርግጠኝነት መመለሴ አይቀሬ ነው፡፡
ሊግ፡- መቐለ 70 እንደርታ ፕሪምየር ሊጉን አሁንም መምራቱን ቀጥሏል፤ ቅዱስ ጊዮርጊሶችም በቅርብ ርቀት እየተከተሉት ይገኛል፤ ከዚህ አንፃር?
ጌታነህ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ የአንደኛው ዙር ውድድር ከመጠናቀቁ በፊት ከዚህ በኋላ ሶስት ተከታታይ ጨዋታዎች በሜዳው ላይ አሉት፤ ከመሪው ጋር ያለው የነጥብ ልዩነትም ሁለት ነው፤ ዘጠኝ ነጥብን አስበን ስለምንጫወት በቅርቡ የመሪነት እርከኑ ላይ እንቀመጣለን፡፡
ሊግ፡- የሊቨርፑል ደጋፊ ነህ ልበል?
ጌታነህ፡- አዎን፤ ያውም ቅልጥ ያልኩ ነዋ!
ሊግ፡- የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን አንተ የምትደግፈው ቡድን ሊያነሳ ነው? ወይንስ ገና ይቀረዋል?
ጌታነህ፡- የፕሪምየር ሊጉ ውድድር ባይጠናቀቅም፤ ገና 14 ጨዋታ ቢቀርም፤ የኳስ ነገርም ባይታወቅም ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ ማግኘቱ ፈፅሞ አይቀርም፡፡ አሁን ሁለተኛውን ክለብ ማንቸስተር ሲቲን በ19 ነጥብ ልዩነትም እየመራው ነው የሚገኘው፤ ዋንጫውን ለማረጋገጥ ጥቂት ጨዋታ ብቻም ይቀረዋልና አሁን ላይ የዋንጫውን አንዱን ጆሮ ጨብጦታል፤ ሁለተኛውን ጆሮ ደግሞ በቅርቡ ይጨብጥና እኛን በጣም ያስደስተናል፡፡
ሊግ፡- ሊቨርፑል የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ዘንድሮ ካነሳ ደስታህን በተለየ መልኩ የምትገልፅ ይመስልሃል?
ጌታነህ፡- አዎን፤ ከዛ በተሻለ መልኩ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስም የዘንድሮውን የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ስለሚያነሳ ድሉን በጋራ በአንድ ላይ አከብረዋለሁ፡፡
ሊግ፡- ወልዋሎ አዲግራትን በሰፊ ግብ ያሸነፈውን ሲዳማ ቡናን ነገ እሁድ ትገጥማላችሁ? ምን ውጤት ትጠብቃለህ?
ጌታነህ፡- ቅ/ጊዮርጊስ ከሲዳማ ቡና የሚያደርገው ጨዋታ ጥሩ ፉክክር የሚደረግበት ነው፤ ከዛ ውጪም ሁለታችንም ያለፈውን ጨዋታ አሸንፈን ከመምጣታችን አኳያም በጥሩ ስነ-ልቦናም ሆነን የምንቀርብበት ስለሆነ ያ ግጥሚያውን በጣም እንዲጠበቅ ያደርገዋል፤ በመጨረሻ የሚመዘገበው ውጤት ግን የእኛ ቡድን ሶስት ነጥብ ሲዳማ ቡና 0 ነጥብ የሚያገኙበት ይሆናል፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ…..?
ጌታነህ፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ቡና ክለቦች በስፖርታዊ ጨዋነቱ ላይ አስቀድመው የሰሩት ስራ በሸገር ደርቢው ጨዋታ ላይ ጥሩ ነገርን እንድንመለከትበት እያደረጉ ይገኛል፤ ከዛ ባሻገር ወደ ክልልም ሄዶ መልካም የሆኑ ነገሮችን እንድናይበትም እያደረገን ይገኛል፤ ሁለቱ ቡድኖች በሲቲ ካፑ ላይ ያሳዩት ነገርም ነው ወደ ክልል ሄዶም ኳስን በሰላምም እንድንጫወት እያደረጉን ያለውና ይሄ ስራቸው ይበል ያሰኛል፤ ሊመሰገኑም ይገባል፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P