Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“መቐለን በማሸነፍ ወደ ዋንጫው ፉክክር እንጠጋለን” ሙሉዓለም መስፍን /ቅ/ጊዮርጊስ/

በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/

የቅ/ጊዮርጊሱ ጠንካራው የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሙሉዓለም መስፍን /ዴኮ/ ክለባቸው የሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታን በሚፋለምበት የማክሰኞው የሜዳው ላይ ጨዋታ ግጥሚያውን በማሸነፍ ወደ ዋንጫው ፉክክር ለመጠጋት ጥረት እንደሚያደርግ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ወሳኝ እና ተጠባቂ ከሚባሉት ግጥሚያዎች መካከል አንዱ የሆነውን ጨዋታ የፊታችን ማክሰኞ የሚያደርገው ከሐዋሳ ከተማ ጋር ካደረገው ጨዋታ በኋላ ሲሆን ይህን ተጨዋች ረቡዕ ዕለት ባናገርነው መሰረት የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ በአሁን ሰዓት ጥሩ የቡድን መንፈስ እየታየ ነው፤ በችግሮቻችንም ዙሪያ የተነጋገርንባቸው ጉዳዮች ስላሉም የቀጣይ ጊዜ ጨዋታዎቻችንም የምናደርገው ዋንጫውን ለማንሳትም ነው ሲል ተናግሯል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች ሙሉዓለም መስፍንን በሊጉ የውድድር ተሳትፎአቸው ዙሪያና ሌሎችንም ተያያዥ ጥያቄዎችን አንስተንለት ምላሾቹን በሚከተለው መልኩ ሰጥቷቸዋል፤ ተከታተሉት፡፡

ሊግ፡- ለፋሲካ በዓል እንኳን አደረሰህ?
ሙሉዓለም፡- አመሰግናለው፤ እናንተንም እንኳን አደረሳችሁ፡፡
ሊግ፡- የፋሲካ በዓልን ዘንድሮ የት ነው የምታሳልፈው? ከእዚህ በፊትስ የት አሳለፍክ? ከበዓሉ ጋር በተያያዘስ ምን ገጠመኝ አለህ?
ሙሉዓለም፡- የአርባ ምንጭ ከተማ ተጨዋች እያለው የፋሲካ በዓልን ከእዚህ ቀደም ሳሳልፍ የነበረው ጨዋታችን ክልል ላይ ካልሆነ በስተቀር በጣም ከምወዳቸው ቤተሰቦቼ ጋር ነበር፤ ከአርባ ምንጭ ስወጣ እና ወደ ሲዳማ ቡና ስገባ ግን ከቡድኔ ተጨዋቾች ጋር በዓሉን አሳልፌያለው፤ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ስመጣ ደግሞ የዓምናውን በዓል ያሳለፍኩት የቡድናችን ተጨዋች የነበረው አዳነ ግርማ በመኖሪያ ቤቱ ጠርቶን ስለነበር እሱ ጋር ነው፡፡ የዘንድሮውን በዓል ደግሞ የማሳልፈው ቡድናችን ወሳኝ ጨዋታ የፊታችን ማክሰኞ ከመቐለ 70 እንድርታ ጋር ያለበት ቢሆንም ከቡድኔ ተጨዋቾች ጋር በዓሉን የማሳልፍ ነው የሚሆነው፡፡
የፋሲካ በዓል ጋር በተያያዘ በዓሉን ከሁሉም በበለጠ በጣም የምወደው እና በልዩ መልኩም የማከብረው ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግን በገጠመኝ ደረጃ የምነግርህ ነገር ምንም የለኝም፡፡
ሊግ፡- ወደ ቅ/ጊዮርጊስ የገባሁት ክለቡ ካለው ከፍተኛ ስምና ዝና አንፃር እንደዚሁም ደግሞ ውጤታማነቱንም ተመልክቼ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ነው ብለህ ነበር፤ ይሄን ዋንጫ ክለብህ ዓምና አጣ? ያኔ ምን ተሰማህ? ዘንድሮስ ይሄን ዋንጫ ቡድንህ ቢያጣ ምን ስሜት ይኖርሃል?
ሙሉዓለም፡- የቅ/ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብን ያለፈው ዓመት ላይ ከሲዳማ ቡና በመምጣት ስለተቀላቀልኩበት ዋንኛ ምክንያቶች ከላይ በጠቀስካቸው ሁኔታዎች የተናገርኳቸው ቢሆንም ይሄ የምወደው ቡድኔ ዓምና በጎል ክፍያ ተበልጦ የሊጉን ዋንጫ ሲያጣ የተሰማኝ የሀዘን ስሜት የመልበሻ ክፍል ውስጥ እስከ ማልቀስ ደረጃ ያደረሰኝ እና የቡድን ጓደኞቼም በቃ ተው አታልቅስ በሚልም እኔን እስከማፅናናት የደረሱበት ስለነበር የተፈጠረውን ሁኔታ መቼም ቢሆን አልረሳውም፤ የሀዘን ስሜቱም ለአንድ ሳምንት ያህል አብሮኝም ነበር፤ የዓምናውን የሊግ ዋንጫ በማጣታችን ለእኛ ብዙ ነገር የሆኑልንን ደጋፊዎቻችንን አሳዝነንበታል፤ ከእዛ ውጪም እንደ ግል የሊጉን ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ አነሳበታለው አንድ ታሪክም ከክለቡ ጋር እሰራበታለው ብለህ መጥተህ ይሄን ዋንጫ ሳታገኝ ስትቀር እና እንደዚሁም ደግሞ እንደ ቡድንም ዋንጫ ከለመደ ቡድን ጋር በእኛ ጊዜ ይሄን ስኬት ሳንጎናፀፍ በቀረንበት ወቅት ሀዘኔ ድርብ ሆኖ ነበር፤ በእዚህ ዓመት ደግሞ ይሄ ነገር ዳግም እንዲከሰት ፈፅሞ አልፈልግምና በቀሪዎቹ ጨዋታዎቻችን ይሄን የሊግ ዋንጫ ላለማጣት እስከመጨረሻው ጨዋታዎች ድረስ እንታገላለን፡፡
ሊግ፡- ይሄን ዋንጫ ብታጡስ ለሚለው ጥያቄዬ ምላሽ አልሰጠከኝም?
ሙሉዓለም፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አሁን ላይ ስምንት ግጥሚያዎች የሚቀሩት እና ውድድሩም ገና ያልተጠናቀቀ በመሆኑ የእኛ ቡድን ተጨዋቾች ላይ በአሁን ሰዓት ላይ ያለው ስሜት ዋንጫ ስለማጣት ባለመሆኑ ከወዲሁ ስለሚሰማኝ ነገር ዋንጫ ስላላጣን ብዙ የምለው ነገር የለኝም፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋቾች የአሁን ሰዓት ላይ ሁላችንም እያሰብን የምንገኘው ጠንክረንና በርትተን በመስራት ከፈጣሪ ፈቃድ ጋር የሊጉን ዋንጫ ለመውሰድ የምንጫወት መሆናችን ነው፤ በክለቡ ቆይታዬ በተለይ ለእኔና ለአንድ አንድ ተጨዋቾች ይሄን ዋንጫ ካጣን ለሁለተኛ ጊዜ ስለሚሆንና ቡድኑ ደግሞ በተከታታይ ሁለት ዓመታት የሊግ ዋንጫን ያጣበት ጊዜ ስለሌለ እና ይሄም በእኛ የተጨዋችነት ጊዜ እንዲሆን ስለማልፈልግ የውድድሩ አሸናፊ ስለመሆን ብቻ ነው እያሰብኩ ያለሁት፤ የኳስ ነገር ሆኖ ይህን ዋንጫ ብናጣ ደግሞ ጊዜው ሲደርስ ስለሚሰማኝ ስሜት ብዙ የምለው ነገር አለኝ፤ ግን ዋንጫውን የምናጣው አይመስለኝም፡፡
ሊግ፡- ከፕሪምየር ሊጉ መቐለ 70 እንደርታ ጋር ማክሰኞ ተጠባቂ የሊግ ጨዋታ አላችሁ፤ ስለሁለታችሁ ፍልሚያ ምን ትላለህ?
ሙሉዓለም፡- ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ማክሰኞ የሚኖረን ጨዋታ የሞት ሽረት ትግል የሚደረግበት ግጥሚያ ነው፤ ይሄን ጨዋታ በሜዳችን የምናደርግ በመሆኑም ግጥሚያውን አሸንፈን እና ከመሪው ክለብ ጋር ያለንን የነጥብ ልዩነት አጥበን ወደ ዋንጫው የምንጓዝበትን ተስፋ እናለመልምበታለን፤ የእዚህን ጨዋታ ማሸነፍ መቻል ደግሞ ሌላው የሚጠቅመን ነገር ቢኖር በቀሪዎቹ ጨዋታዎች እኛ ጠንካራና ብዙ ግጥሚያዎችን በሜዳችን የምናደርግ እና እነሱ ደግሞ ጠንካራ ጨዋታዎችን ከሜዳቸው ውጪ ስለሚያደርጉ በእዚህ በኩል ተጠቃሚ የምንሆንበትም ነገር አለና ጠንካራ ፉክክር የሚደረግበትን የማክሰኞ ጨዋታችንን እናሸንፋለን፡፡
ሊግ፡- በቅዱስ ጊዮርጊስ ውስጥ የአሁን ሰዓት ላይ ያለው ስሜት ምንድንነው የሚመስለው?
ሙሉዓለም፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥም ሆነ የቡድኑ ተጨዋቾች ላይ የአሁን ሰዓት ላይ ያለው የቡድን መንፈስ በጣም ጥሩ ነው፤ ሁላችንም የሊጉን ዋንጫ በምን መልኩ ለማንሳት እንደምንችልም ነው እየተነጋገርን የምንገኘው፤ በዛ ላይ የክለባችን ምርጦቹ ደጋፊዎቻችንም አይዞአችሁ ከጎናችሁ ነን በሚልም እያበረታቱን ስለሆነ ሙሉ ትኩረታችንን ስለ ዋንጫው ነገር እያሰብን ነው የምንገኘው፡፡
የፕሪምየር ሊግ ውድድሩ አሁን ላይ ገና ባልተጠናቀቀበት እና ቀሪም 9 ግጥሚያዎች በቀሩበት የአሁኑ ወቅት ከላይ ሊጉን የሚመራውም ሆነ ተከታታይ ስፍራ ላይ የሚገኙት ክለቦች እኛን እንደሚፈሩም እናውቃለንና ከእዚህ በኋላ የሚኖሩንን ግጥሚያዎች በማሸነፍ እና በስራ የምንታወቅበትንም ውጤታማነት ወደ ተግባር በመመለስ የውድድሩ ሻምፒዮና ለመሆን ከፍተኛ ጥረትን እናደርጋለን፡፡
ሊግ፡- ቅ/ጊዮርጊስ ከእዚህ ቀደም በነበሩት የሊግ ውድድሮቹ በመሪነቱ ይታወቃል፤ ይሄን መሪነት ግን ዘንድሮ በጣላቸው ነጥቦች ሊያጣ ችሏል፤ ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ?
ሙሉዓለም፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን ዘንድሮ ውጤት አሳጥቶት የመሪነት ደረጃ ላይ እንዳይቀመጥ ያደረገው የተለያዩ ምክንያቶች ናቸው፤ ከእነዚህ ውስጥ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ቡድኑን የተቀላቀሉት አንድ አንድ ተጨዋቾች ለክለቡ አዲስ ከመሆናቸው አኳያ እና ወደ ቡድናችን ከመጣው አሰልጣኝ አጨዋወት ጋርም በፍጥነት ያለመዋሀድ ችግር ስለነበር፤ እንደዚሁም ደግሞ ቀደም ሲል በነበረው የውድድር ጅማሬ ላይ በ5 ጨዋታዎች ላይ ቡድናችን ድል ሲያደርግ ጎሎችን ያስቆጥሩልን የነበሩትና ለክለባችን ወሳኝ የሚባሉት ተጨዋቾች ላይ በኋላ ላይ የደረሱት ጉዳቶች በተለይ ደግሞ የአጥቂውን ክፍል በሚመሩት ሳላህዲን ሰይድ እና ጌታነህ ከበደ ላይ የሚደርሱት ጉዳቶች የአጥቂውን ክፍል ስላሳሳብን እና በጎል አጨራረስ ላይ እንድንቸገር ስላደረገን እነዚህ ችግሮች በዋናነት ውጤት አሳጥቶናል፡፡ የሁለተኛው ዙር ሲጀመር ግን ክለባችን ባሉበት ችግሮች ዙሪያ ከአሰልጣኙም ጋር የተነጋገረባቸው በርካታ ጉዳዮች ስላሉ አሁን ላይ ጥሩ ለውጦችን በተወሰነ መልኩ እያሳየን ይገኛል፤ ከእዚህ በኋላ ደግሞ ያሉብንን ችግሮች ሙሉ ለሙሉ ቀርፈን ጠንካራውንና ውጤታማውን ቡድን የምናሳይ ነው የምንሆነው፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስን ሌላው ውጤት ያሳጣው ከላይ እንደገለፅኳቸው የገዘፈ ችግር ባይሆንም የቡድናችን አሰልጣኝ በሜዳችንም ከሜዳችንም ውጪ ስንጫወት የሚከተለው የጨዋታ ፍልስፍና ተመሳሳይ መሆኑም ይሄ ጎድቶናል፤ በሊጉ ጨዋታ ብዙ ጊዜ በሜዳችንም ወደ ክልል በመውጣት ከሜዳችን ውጪም ስንጫወት ከኋላ በሶስት ተከላካዮች ነው የምንጫወተው እና ይሄን ተመሳሳይ አጨዋወት መከተላችንም ጎድቶናል፡፡
ሊግ፡- የቅ/ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ በሜዳ ላይ እየሰጠ ስላለው ግልጋሎት?
ሙሉዓለም፡- የቅ/ጊዮርጊስ ክለብን ከተቀላቀልኩበት ጊዜ አንስቶ ቡድኑን ውጤታማ ለማድረግ በምችለው አቅም ሁሉ ከፍተኛ ጥረቶችን እያደረግኩ ቢሆንም የቡድኑ ቆይታዬ ላይ በስኬታማነቱ የሚታወቀውን ክለብ ሙሉለሙሉ ደግሞ ጠቅሜዋለው ብዬ ፈፅሞ አላምንም፤ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስጫወት ክለቡን ከተቀላቀልኩበት ጊዜ አንስቶ ሳላርፍ ነው የተጫወትኩት ተቀይሬ የወጣሁበት ጊዜ በራሱ ብዙም የለም፤ በእዚህ መልኩ መጫወቴ ድካም ቢኖርብኝም ይህን ቡድን ለማገልገል ሁሌም ከፍተኛ ፍላጎት ነው ያለኝና ከእዚህ በኋላ የሚኖሩት ጨዋታዎች ላይም ቡድኔን ውጤታማ ለማድረግ የምችለውን ነገር ሁሉ አደርጋለው፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ….ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ምን ትላለህ?
ሙሉዓለም፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችን በተመለከተ ስለ እነሱ ለእኛ ብዙ ነገር ስለሆኑና የሚሰጡንም ድጋፍ በጣም ምርጥ ስለሆነ በጣም እንደምናመሰግናቸው ለመናገር እፈልጋለው፤ ስለ እነሱ ለማውራት ቃላትም የለኝም እና አሁን ላይም የሊጉን ውድድር እስከምናጠናቅቅበት ጨዋታ ድረስ ከጎናችን ለመቆም እና የተለመደውን ድጋፋቸውንን ሊሰጡን ስለተዘጋጁ ለእኛ ብርታት ነው የሚሆኑልን በተረፈ ነገ ስለሚከበረው የፋሲካ በዓል ቤተሰቦቼን፤ መላው የኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮችን፣ የቡድን አጋር ጓደኞቼንና የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎችን እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እፈልጋለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P