Google search engine

“መከላከያን ወደ ውጤታማነቱ ለመመለስ ዝግጁ ነን”ሽመልስ ተገኝ

ሽመልስ ተገኝ

የመከላከያው የቀኝ መስመር የኮሪደር ስፍራ ተጨዋች ሽመልስ ተገኝ ክለባቸው በመጀመሪያው ዙር ያስመዘገበው ውጤት በጣም የሚያስቆጭ እና የማይመጥናቸው መሆኑን በመግለፅ የሁለተኛው ዘር ላይ ውጤታማ ቡድን ይዘው እንደሚቀርቡ አስተያየቱን ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ሰጥቷል፡፡
የመከላከያው ሽመልስ ተገኝን በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ አናግረነው የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቶናል፡፡
የመከላከያ የአንደኛ ዙር የፕሪምየር ሊግ ተሳትፎን በተመለከተ
“መከላከያ በመጀመሪያው ዙር የውድድር ተሳትፎው ከዝግጅት ጊዜ አንስቶ ጥሩ ነገር እናስመዘግባለን ብሎ ቢነሳም የፕሪምየር ሊግ ጉዞው ላይ የገጠመው ነገር ጥሩ አልነበረም፤ በሊጉ የሚመጥነንም ውጤት አላስመዘገብንም ይሄንን ችግራችንንም በደንብ ከተረዳን እና በአግባቡ ከፈተሽን በኋላም ለሁለተኛው ዙር ተስተካክለን ለመምጣት ተዘጋጅተናል”፡፡
የፕሪምየር ሊጉ ላይ ውጤት ያጡበት ችግር
“የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ለውጤት ማጣታችን ዋናው የጎዳን ምክንያት ቀደም ሲል በነበረን የጥሎ ማለፍ እና የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታዎች ላይ ዋንጫን ስላነሳን ክለቦች ለእኛ የሰጡን ግምት ከፍተኛ ስለነበር ጠንክረውብን የመጡበት እና በቡድናችን ተጨዋቾች ላይም ተደጋጋሚ ጉዳቶች ነበሩና እነዚህ ጎድተውናል፤ ሌሎቹ ችግሮቻችን ድካም እና የአቋም መዋዠቅም በብዙ ተጨዋቾች ላይ ተከስቶ ስለነበር እነዚህ ውጤት ሊያሳጡን ችለዋል”፡፡
የመከላከያ የተጨዋቾን ስብስብ በተመለከተ
“የመከላከያን የተጨዋቾች ስብስብ ጥሩ ነው ልል ብችልም ካስመዘገብነው ውጤት አንፃር ደግሞ በዚህ መልኩ ሀሳቤን መግለፄ ላያስኬድ ይችላል፤ ስለዚህም ስበብስባችንን የተሻለ ነው ለማለት ከዚህ በኋላ በሚኖሩት የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች ላይ ማስመስከር ስላለብን የሁለተኛው ዙር ላይ ጥሩ ነገር ልንሰራ ይገባናል”
በፕሪምየር ሊጉ የሁለተኛው ዙር ስለሚቀርቡበት መንገድ እና ምን ውጤት እንደሚያመጡ
“መከላከያ በሁለተኛው ዙር የሚቀርበው የአንደኛው ዙር ድክመቱን በማስተካከል ነው፤ በእያንዳንዳቸው ጨዋታዎች ላይ ውጤታማ እና ጥሩ የነበረውን ቡድኑንም ዳግም ለማሳየትም ዝግጁ ነው፤ ለእዚህ ደግሞ ከክለቡ አመራሮች እና ከኮቺንግ ስታፉ ጋር ጠለቅ ባለ መልኩ የተነጋገረበትም መንገድ ስላለ ሊጉን ከ1-6 ባለው ደረጃ ውስጥ ሆነን ለማጠናቀቅ ዝግጁ ነን”፡፡
የመከላከያ ክለብ ውስጥ በቋሚነት የመሰለፍ እድልን አጥተህ እንደነበር እና አሁን ስለማግኘትህ
“የመከላከያ ክለብ ቆይታዬ ላይ በቋሚነት የመሰለፍ እድልን ያጣሁት በአቋሜ ወርጄ ሳይሆን ከባህር ዳር ጨዋታችን መልስ ጉዳትም የነበረብኝ ተጨዋች ስለነበርኩም ነው፤ ያኔ ከእነጉዳቴም ነበር የተጫወትኩም፤ ከኩዳቴ በኋላ ደግሞ ተጠባባቂ በነበርኩበት ሰዓት ላይም አሰልጣኙ የራሱ የጨዋታ ታክቲክ ስለነበረውም በዚሁም ሳልሰለፍ ቀርቼ ነበር በኋላ ላይ ግን አሰልጣኙ በቋሚነት የመሰለፍ እድሉን ሰጥቶኝ በአሁን ሰዓት እየተጫወትኩ ነው የምገኘው”፡፡
ከአሰልጣኝ ስዩም ጋር ግጭት ስለመፍጠራቸው
“በአሰልጣኝ ስዩም እና በእኔ መካከል ተፈጥሮ የነበረው ግጭት ሳይሆን በመሰለፍ እና ባለመሰለፍ ጉዳይ ላይ ነው እሱ የፈለገው የጨዋታ ታክቲክ ነበር፤ በኋላ ላይ ሁለታችንም ልንግባባ ስለቻልን ልንስማማ ችለን ለቡድኑ ለመጫወት ችያለው”
ለመከላከያ በቀጣይ ጊዜ ምን ግልጋሎትክን ትሰጣለህ
“ለመከላከያ ውጤት ማማር በቀጣዩ ዙር ይዤ የምቀርበው አቋም ከእዚህ በፊት ከነበረኝ አቋም የተሻለ የሚባለውን ነው፤ ወደ ብሔራዊ ቡድን ዳግም መመለስም እፈልጋለውና ይሄን በእርግጠኝነት አሳካዋለው”
ስለግል ህይወቱ
“ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ነኝ፤ የልጆቼ ስምም አሜን እና ኢያብ ይባላሉ፤ ባለቤቴም አስና ግርማ ትባላለች፤ ጥሩ ሚስት እና እናትም ነች፤ ቤተሰቦቼንም በጥሩ ሁኔታ እየመራው ነው የምገኘው”፡፡
በመጨረሻ
“የመከላከያን ክለብ ደጋፊዎች እና የሰራዊቱን አባላቶች በዘንድሮው የመጀመሪያው ዙር የሊግ ውድድር አስከፍተናቸው ነበርና ቡድኑን ካለበት የውጤት ማጣት ችግር አላቀን ወደ ቀድሞ አቋሙ በመመለስ ልነስደስታቸው ተዘጋጅተናልና ይሄን ነው ማለት የምፈልገው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

%d bloggers like this:
P