መከላከያ ከ20 የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች በሁዋላ ከአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ጋር ተለያይቷል፡፡ እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ቡድኑ በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ ምንያምር የሚመራ ይሆናል፡፡ መከላከያ በዚህ ወቅት በ18 ነጥብ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
አሰልጣኝ ስዩም ከዚህ ቀደም ሰበታ ከተማ ፣አ.አ ከተማ ፣አዳማ ከተማ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አልሳቅር ፣ አልዋሂዳ ሰንአ ፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ብድንን በረዳት አሰልጣኝነት ማሰልጠን ችለዋል፡፡