Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ምርጥ ተከላካይ ለመባል ራሴን እያዘጋጀው ነው፤ የደጉ ደበበ አጨዋወት ሁሌም ይመስጠኛል” ፍቃዱ ደነቀ /ድሬዳዋ ከተማ/

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ለድሬዳዋ ከተማ፣ ለመቐለ 70 እንደርታ እና ለወልዋሎ
አዲግራት ክለቦች የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሆኖ ቡድኖቹን አገልግሏል፤ ከእነዚህ ቡድኖች በተጨማሪ በአሰልጣኝ ዩሃንስ
ሳህሌ የኃላፊነት ዘመን ላይም ለኢትዮጵያ ወጣት ቡድን ለመጫወትም ችሏል፤ ይሄ ተጨዋች ፍቃዱ ደነቀ ሲባል በእዚህ
የዝውውር መስኮት የቀድሞ ቡድኑን ድሬዳዋ ከተማን በድጋሚ ሊቀላቀል ችሏል፤ ከእዚህ ተጨዋች ጋር በተለያዩ
ጥያቄዎች ዙሪያ የሊግ ስፖርቱ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ቆይታ አድርጎ ነበርና የተጨዋቹን ምላሽ በሚከተለው መልኩ
ልናቀርበው ችለናል፤ ተከታተሉት፡፡


በዝውውሩ መስኮት ወደ ድሬዳዋ ከተማ ስላመራበት መንገድ
“በወልዋሎ ከተማ ክለብ ውስጥ የነበረኝን የውል ጊዜዬን ካጠናቀቅኩኝ በኋላ በቅርቡ ወደ ቀድሞ ቡድኔ ድሬዳዋ
ከተማ ላመራ የቻልኩት በእነሱ መፈለጌን ተከትሎ ኤጀንቴ ባመቻቸልኝ ዕድል ነው፤ በእዚህም ከእዚህ በፊት ጥሩ ጊዜን
ያሳለፍኩበትን ቡድን ለአንድ ዓመት ያህል እንድጫወትበት ዳግም ስለተቀላቀልኩ በጣም ተደስቻለሁ”፡፡
በወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ክለብ ውስጥ ስለነበረው የዓምናው ቆይታ
“በእዚህ ቡድን ውስጥ የነበረኝ የተጨዋችነት ቆይታ ምንም እንኳን አልፎ አልፎ ያጋጥመኝ ከነበረው ጉዳት እና
ተጨዋቾቻችን አካባቢ ህብረትከማጣት ጋር በተያያዘ ውጤታችን ላይ የኮቪድ ወረርሽኝ ወደ አገራችን ገብቶ ውድድሩን
እስካቋረጠበት ጊዜ ድረስ መሰናከል ቢኖርበትም እንደዛም ሆኖ ግን በቆይታዬ ጥሩ ጊዜን አሳልፌበታለው”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነት ጉዞውበሚፈልገው ደረጃ ላይ ተገኝቶ እንደሆነ
“የእግር ኳስን ስጫወት የእኔ የመጀመሪያዬ መድረሻ እና መገኛዬም እንዲሆን የምፈልገው በብሔራዊ ቡድን ደረጃ
ተጫውቼ ሀገሬን ማገልገል ነበር፤ ይሄንንም ፍላጎቴን ዓምና አሳካለው ብዬ ጠብቄም ነበር፤ ያም ሆኖ ግን ጉዳት በዛ
ደረጃ ላይ እንዳልገኝ አስችሎኛልና ይሄ ነው እልሜን እንዳላሳካ ያደረገኝ”፡፡
በእግር ኳስ ተጨዋችነት ለመጀመሪያ ጊዜ ስለወጣበት የፕሮጀክት ቡድንና ስለ ትውልድ ሰፈሩ
“ሰፈሬ አስኮ ነው፤ አስኮ ፕሮጀክት ደግሞ እኔን ብቻ ሳይሆን ብዙዎቹን እግር ኳስ ተጨዋቾች አሁንና ከእኛ በፊት
ለተለያዩ ክለቦች ያወጣ አካባቢ ስለሆነ ያን ለማየት በመቻሌ ሁሌም ቢሆን በጣም ያስደስተኛል፤ ይህ ፕሮጀክት
ወደፊትም ቢሆን ለሀገሪቱ እግር ኳስ ሌሎችንም ተጨዋቾች ስለሚያፈራ የሚያግዘው አካል ሊኖር ይገባል”፡፡

በታዳጊነት ዕድሜው የእግር ኳስን መጫወት ሲጀምር ሊጫወትበት ስላሰበው ቡድን
“ማንም እንደሚያስበው እና እንደሚመኘው ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድንና በመቀጠል ደግሞ ወደ ዋናው ቡድን ገብቶ
መጫወት ነበር የእኔ ከፍተኛው ፍላጎቴ፤ ከዛ ደግሞ ለብሔራዊ ቡድን ተመርጦ መጫወትንም አልሜ ነበር፤ ያም ሆኖ
ግን በጊዜው በተተኪው ቡድን ደረጃ ለሁለት ዓመታት ያህል ለመጫወት ብችልም ለዋናው ቡድን ካደግኩኝ በኋላ በሲቲ
ካፕ ላይ የመጀመሪያ ጨዋታዬን አድርጌ ጥሩ ስላልነበርኩና በኋላ ላይ ደግሞ ወደ ተስፋው ቡድን ታድጋለህ ተብዬ
ልምምዴን ከሰራው በኋላ ለብቻችን ተነጥለን የምንሰራበት ሁኔታ ስለተፈጠረ ከአሰልጣኜ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት
ቡድኑን ልለቅ ችያለሁ፤ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተተኪ ቡድን ስለቅ መጀመሪያ ላይ እንድወጣ አልተፈለገም ነበር፤ በኋላ ላይ
ግን ከስምምነት ላይ ስንደርስ ወደ ባንክ ተስፋ ቡድን በአሰልጣኝ ግርማ በመፈለጌ ወደዛ አመራሁኝ”፡፡
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቡድን ውስጥ ስለነበረው ቆይታ እና በመጨረሻም ክለቡ ስለመፍረሱ
“ወደ ባንክ ሳመራ መጀመሪያ የተቀላቀልኩት የተስፋ ቡድኑን ነው፤ እዛም ጥሩ ስለተንቀሳቀስኩ በወቅቱ በነበረው
አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማሪያም አማካኝነት ወደ ዋናው ቡድን አደግኩ፤ በዛ ቡድን በነበረኝ ቆይታዬም አሰልጣኝ ፀጋዬ ለእኔ
የመሰለፍ እድሉን ባይሰጠኝም 18 ውስጥም ባያስገባኝም እሱ ሲለቅ ግን ረዳቱ የነበረው አሰልጣኝ ሲሳይ ከበደ ዋና ሆኖ
ነበርና የመጀመሪያ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዬን በእሱ ስር ሆኜ ከቀድሞ ቡድኔ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በግራ ፉል ባክ

ልጫወት እና በቡድኑ ውስጥም ጥሩ ጊዜን ላሳልፍ ችያለውና እነዚህ ነገሮች ፈፅሞ የማይረሱኝ ናቸው፤ ከዛ ውጪ
ባንኮች የሀገሪቱ ትልቅ ቡድን ሆኖ ከሊጉ በመውረዱ እና በመፍረሱ በጣም አዝኛለሁ”፡፡
ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲጫወት ፈፅሞ የማይረሳቸው ነገሮች
“አንደኛው የቡድኑ አሰልጣኝ በነበረው ሲሳይ ከበደ ከፍተኛ እምነት ተጥሎብኝ በተለያዩ ጨዋታዎች ላይ የመሰለፍ
እድሎችን ለማግኘት መቻሌና እሱም በተደጋጋሚ ጊዜ በርታ ትልቅ ደረጃ ላይም ትደርሳለህ ይለኝ ስለነበር ነው፤ ከዛ
ውጪም ከማንም ራሴን እንዳላሳንስ እና ሳልፈራም በመጫወት ከፍተኛ ተነሳሽነትንም ይፈጥርልኝ ነበርና ያ ሁኔታ
ፈፅሞ አይረሳኝም፤ ይሄ አሰልጣኝ አሁንም ድረስ በመደወልም ያበረታታኛል፤ ሌላው በባንክ ቆይታዬ የማልረሳው
ከቀድሞ ክለቤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር አድርገነው በነበረው የሲቲ ካፕ ጨዋታ ላይ የምንጫወተው ከሀገሪቱ ትልቅ ቡድን
ጋር ነበርና በእዚህ ጨዋታ ላይ ከገባው ጥሩ እሆናለው ብዬ ራሴን አሳምኜው እና ለእኛ ተጨዋች ለነበረው ጁንዶም
ነግሬው ነበርና ጥሩ ልጫወት ችያለው፤ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ አዳነ ግርማም ጥሩ መጫወቴን ካየ በኋላም በርታ
ያለኝን ሁኔታ አስታውሰዋለሁ”፡፡
ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ መውረድ እና መፍረስ ምክንያቱ
“ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ ውጤት ማጣት እና ከሊጉ መውረድ እንደመጀመሪያ ምክንያት የምጠቅሰው በጊዜው
ቡድናችን ጥሩ ስብስብ የነበረው እና ታዳጊ ተጨዋቾችንም የያዘ ቢሆንም የሁለተኛው ዙር ላይ እኛን ለማጠናከር
ከመጡት ተጨዋቾች ጋር በፍጥነት ለመዋሃድ መቸገራችን ያ ሊጎዳን ችሏል፤ ለባንኮች መፍረስ ትክክለኛ ምክንያቱን እኔ
ላውቅ ባልችልም ይሄ ቡድን ግን ለሀገር እግር ኳስ ካበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ አንፃር መፍረስ አልነበረበትም”፡፡
በመቐለ 70 እንደርታ ክለብ ውስጥ ስለነበረው የተጨዋችነት ዘመን ቆይታው እና ቡድኑ በጊዜው ስላስመዘገበው ውጤት
“መቐለ 70 እንደርታ እኔ በነበርኩበት ሰዓት መቐለ ከተማ ነበር የሚባለው፤ አሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌም ነበር
ለኢትዮጵያ ታዳጊ ቡድን መርጦኝ በነበረበት ሰዓት ያውቀኝ ስለነበር ወደዚህ ቡድን ጠርቶኝ በማስገባት ሊያጫውተኝ
የቻለው፤ በመቐለ ቆይታዬ ጥሩ የኳስ ጊዜን ነው ያሳለፍኩት፤ ያኔ ቡድናችን ካደረጋቸው 30 ጨዋታዎች ውስጥም
በ29ኙ ልጫወት ችያለሁ፤ ከሲዳማ ቡና ጋር በነበረን ግጥሚያ አንዱን ያልተጫወትኩትም በጊዜው ደርሶብኝ በነበረው
የጡንቻ መሸማቀቅ ህመምም ነበር፤ መቐለ በፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዓመት የውድድር ተሳትፎው ያስመዘገበው
ውጤት ከታችኛው ሊግ ከመምጣቱ አንፃር በጣም ጥሩ የሚባል እና የሚያበረታታም ነው፤ አራተኛ ሆነን ነበር ሊጉን
ያጠናቀቅነው፤ ይሄ ውጤት እንዲመጣም የክለባችን ህብረት ጥሩ መሆኑ፣ የተጨዋቾቻችን ተነሳሽነት እንደዚሁም
ደግሞ አሰልጣኝ ዩሃንስ የሚለንን ነገር ሁሉ መስማታችን እና ሊጉንም በአሰልጣኙ አማካኝነት በእዚህ ደረጃ ላይ ሆነን
እናጠናቅቃለን ብለን ለማቀድ መቻላችን የምንፈልገውን ውጤት እንድናመጣ ጠቅሞናል”፡፡
በ29 የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች ስለመጫወት ሚስጥሩ
“ይሄ ሊሆን የቻለው ሁሌም ቢሆን ራሴን ጠብቄ እጫወት ስለነበርና ልምምዶቼንም ጠንክሬ እሰራ ስለነበር ነው፤
ሌላው ከስራ ውጪ መዝናናት ላይም አልነበርኩበትም፤ ከዛ ውጪም የቡድኑ አሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌም እኔ ጥሩ ደረጃ
ላይ እንድደርስም ይፈልግ ነበርና ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ስለሚነግረኝ ሌላው ደግሞ የቡድኔ አጋር ተጨዋች አሌክስ
ተሰማም ከአጠገቤ ሆኖ ይጫወት ስለነበርና ስለሚያበረታታኝ እነዚህ ነገሮች ናቸው ለእኔ ትልቅ ልምድ ሆነውኝ በበርካታ
የክለቡ ጨዋታዎች ላይ ተሰልፌ ለመጫወት የቻልኩት”፡፡
መቐለ ከተማን በጊዜው ለቅቆ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ስለማምራቱ
“ለድሬዳዋ ከተማ ያኔ የፈረምኩት ከመቐለ ከተማ ጋር ለመቀጠል አድርገነው በነበረው የገንዘብ ድርድር ልንስማማ
ስላልቻልን ነው፤ ከዛም ድሬዳዋ ገባሁና በውድድር ዓመቱ ጥሩ ጊዜን አሳለፍኩኝ፤ ድሬ ስገባ ጥሩ የተጨዋች አቀባበልም
ነበር የተደረገልኝ፤ በተለይ ደግሞ ከቡና ጋር በነበረው ጨዋታ ላይ ጥሩ መንቀሳቀሴን ተከትሎም ያገኘሁትን አድናቆት
የምረሳውም አይደለም”፡፡
የእግር ኳስን በሰፈር ደረጃ መጫወት ሲጀምር ለመጀመሪያ ጊዜ ስላደነቀው እና ተምሳሌቱስላደረገው ተጨዋች
“ለመጀመሪያ ጊዜ ኳስን ሲጫወት ተመልክቼው ያደነቅኩት ተጨዋች የቀድሞውን የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች የነበረውን ዮናታን ሀይለን ነው፤ በእግር ኳሱ እሱን እያየውም ነበር ያደግኩት፤ ዮናታን

ባጋጠመው ጉዳት በእግር ኳሱ መድረስ በሚፈልግበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ባይችልም ፈጣሪ ለእሱ ያዘጋጀለት ነገር አለና
አሁን ላይ ያን እየጠበቀ ነው የሚገኘው”፡፡
በፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ምልከታህ በጣም ያደነቅከው ተጨዋች
“ደጉ ደበበን ነዋ! የእሱ አጨዋወት ሁሌም ይመስጠኛል፤ እሱን ለመምሰልም ጭምር ነው በሜዳ ላይ ሁሌም
የምጫወትም የሚመስለኝ፤ የደጉ የአጨዋወት እርጋታው በተለይ ልዩ ስሜት ስለሚሰጠኝ አድናቂው ነኝ”፡፡
የእግር ኳስን በደንብ ተጫውቼ አሳልፍኩ ብለህ ታስባለህ
“መች ጀምሬ፤ በተለይ ደግሞ እነ ደጉ ደበበን፣ ሳላህዲን ሰይድን፣ አዳነ ግርማን ስታይን ስትመለከት ኳስን ተጫወትኩ
ማለት አትችልም፤ እነሱ ብዙ ነገሮችን ሰርተው አልፈዋል፤ ያኔ ብትል አይቆጭህም”፡፡
ከእግር ኳስ ውጪ መዝናኛው ስለሆነው ነገር
“ፊልም ማየት፣ ወክ ማድረግ እና መዝሙሮችን ማዳመጥ በጣም ደስ ይለኛል”
የግል ባህሪው
“ቀልደኛ ነኝ፤ ከሰዎች ጋርም ቶሎ እግባባለሁ”፡፡
ከተጨዋቾች የቅርብ ጓደኞቹ ስለነበሩት
“በወልዋሎ አዲግራት በነበርኩበት ሰዓት ለእኔ ቅርበት ኖራቸው እንግባባ የነበሩት ጓደኞቼ ካፒቴናችን የነበረው አይናለም
ሀይለ እና ራምኬል ነበሩ፤ በድሬዳዋ ከተማ ደግሞ ከገናናው ረጋሳ ጋር ነበርና እነዚህ ተጨዋቾች የቅርብ ጓደኞቼ
ናቸው”፡፡
ስለ ባለቤቱ እና ስለ ትዳር ህይወቱ
“ባለቤቴ ዕድላዊት ዘውዱ ትባላለች፤ የድሬዳዋም ልጅ ነች፤ ከተጋባን 4 ዓመትም ሆኖናል፤ የትዳር ህይወቴን በተመለከተ
በአሁን ሰዓት በጥሩ ሁኔታ ከምወዳት ባለቤቴ ጋር እየኖርን ይገኛል፤ ከአብራካችንም በዋና ስሙ አቤኔዘር በቤት ስሙ
ደግሞ ፍቅር ተብሎ የሚጠራ የሁለት ዓመት ከ6 ወር ዕድሜ ያለው ልጅን አፍርተናል፤ ከዛ ውጪም አሁን ላይ እሷም
ነፍሰ-ጡር ስለሆነች ሌላ ልጅን ከቀናቶች በኋላ ልታበረክትልኝ እያኮበኮበች ይገኛል”፡፡
ከባለቤቱ ጋር ስለነበራቸው የመጀመሪያ ቀን ትውውቅ
“የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ ተጨዋች በነበርኩበት ሰዓት ላይ ነው በማህበራዊ ድረ-ገፅ /ፌስ ቡክ/ ላይ
ለመጀመሪያ ጊዜ ተመልክቻት ልተዋወኳት የቻልኩት፤ ከዛም ከእሷ ጋር ስልክ ተለዋወጥንና ተደዋወልን፤
በስተመጨረሻም ከመግባባት ላይ ስለደረስን ለዛሬው የትዳር ጥምረታችን ልንበቃ ቻልን”፡፡
ባለቤቱ የእግር ኳስን ትወድ እንደሆነና ከኳሱ ጀርባ ስለምታደርግለት እገዛ
“አዎን፤ ባለቤቴ ኳስን በእኔ ምክንያት ልትወድ ችላለች፤ ከኳሱ ህይወቴ ጀርባም እሷ የምታደርግልኝ እገዛ በጣም ጥሩ
የሆነ ነው”፡፡
ከባህር ማዶ ስለሚደግፈው ቡድን እና ስለሚያደንቀው ተጨዋች
“ከውጪ ቡድኖች ብዙም ባልደግፍም አርሰናል ሲጫወት ግን በጣም ደስ ይለኛል፤ የማደንቀው ተጨዋች ደግሞ በራሴ
ቦታ ላይ የሚጫወተውን ሰርጂዬ ራሞስን ነው፤ ራሞስ ሲጫወት ታክሎቹ እንዲሁም ኳስን በግንባሩ የሚገጭበት ሁኔታ
ደስ ይለኛል”፡፡
ለብሔራዊ ቡድን ተመርጦ ስለመጫወት እና ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ዘንድሮ በምን መልኩ ለማሳለፍ እንደተዘጋጀ

“የድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብን በድጋሚ በተቀላቀልኩበት የአሁን ሰዓት ላይ ቡድኑን በጥሩ ብቃት ለመጥቀም
የክረምቱ ወራት ላይ ራሴን ከኮቪድ ወረርሽኝ በመጠበቅ በነበረኝ ጥሩ ማቴሬያሎች ልምምዴን ሰርቼ በግሌ በደንብ
ተዘጋጅቻለው፤ አሁን ደግሞ የፕሪ-ሲዝን ዝግጅታችንን ልንጀምር ስለሆንም ከክለብ አጋሮቼ ጋር የቅንጅት ስራን
የምሰራበት ሁኔታ አለና የእዚህ ዓመት ላይ ከመቼውም ጊዜ የተሻለ አቋም ይኖረኛል፤ ለብሔራዊ ቡድን ከመመረጥ ጋር
በተያያዘ ከእዚህ በፊት በአሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌ የኃላፊነት ዘመን ከእዚህ ቀደም ለተስፋ ቡድን በመመረጥ
የተጫወትኩበት ጊዜ ነበር፤ አሁን ደግሞ ለብሔራዊ ቡድን መመረጥ እና መጫወትን እፈልግ ነበርና ያን ምኞቴን
ለማሳካት ጠንክሬ በመስራት የምችለውን ሁሉ ጥረትን አደርጋለሁ”፡፡
በመጨረሻ…
“በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኔ አሁን ለደረስኩበት ስፍራ በቅድሚያ ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ፤ ከዛ በመቀጠል እናት እና
አባቴን በህይወት አጥቼ ነበርና እንደ እነሱ ሆኖ ያሳደገኝን ወንድሜን ተስፋዬ ደነቀን፣ አሰልጣኝ ሲሳይ ከበደን፣ አሰልጣኝ
ዩሃንስ ሳህሌን ጓደኞቼን በአስኮ ፕሮጀክት ያሰለጠኑኝን አሰልጣኞች እና ከዛም በተጨማሪ የእኔን ጨዋታ በመመልከት
ጠንካራና ደካማ ጎኔን ይነግሩኝ የነበሩትን የባለቤቴን አባት አቶ ዘውዱ ማሞን እና እናቷን ወ/ሮ ስንታየሁ ዘለቀን
ጭምር ላመሰግናቸው እፈልጋለው”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P