Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ሰዎች ቢጥሉኝም ፈጣሪ አልጣለኝም”“ለካሳዬ አጨዋወት አትሆንም ተብዬ ቡናን እንድለቅ ስደረግ ስቅስቅ ብዬ አልቅሻለው”ፍፁም ጥላሁን /ጅማ አባጅፋር/

ወጣቱ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ፍፁም ጥላሁን በኢትዮጵያ ከፍተኛው ሊግ የዘንድሮ የውድድር ዘመን ተሳትፎው ላይ በአሰልጣኝ እስማኤል አቡበከር የሚመራውን የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብን ወደ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ እንዲያልፍ ካስቻሉት ግምባር ቀደም ተጨዋቾች መካከል ስሙ በጉልህ የሚጠቀስ ሲሆን በእግር ኳስ ጨዋታ ዘመኑ የአጭር ዓመታት ጊዜ ውስጥምየቅ/ጊዮርጊስ የታዳጊ ቡድንን፣ የኢትዮጵያ ቡና የወጣት እና የዋናው ቡድንን እንደዚሁም ደግሞ የከፋ ቡናንና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቡድኖችን መለያ ካጠለቀ በኋላ በዘንድሮው የክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ጅማ አባጅፋርን በይፋ ሊቀላቀል ችሏል፡፡

በአሰልጣኝ እስማሄል አቡበከር በሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ቡድን ውስጥ ቁልፍ ሚና የነበረው ፍፁም ክለባቸው ወደ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ለማለፉ በክለቡ ውስጥ የነበረው አንድነት ፍቅርና በተለይም ደግሞ የአሰልጣኝ እስማሄልና የእኛ ተጨዋቾች የእርስ በርስ መግባባትና እሱ የሚሰጠንንም ታክቲክ በመተግበሩ ላይ ንቁ ተሳትፎ እናደርግ ስለነበር ይሄ ለውጤታችን አግዞናል፤ የአዲስ አበባ ከተማ ክለብ ቤትኪንጉን መቀላቀሉም በጣም ይገባዋል በማለት አስተያየቱን ከሊግ ስፖርት ጋዜጠኛው መሸሻ ወልዴ ጋር በነበረው ቆይታ ሰጥቷል፡፡

ፍፁም ጥላሁን በኳስ ጨዋታ ዘመኑ ኢትዮጵያ ቡና በነበረበት ሰዓት ለክለቡ ጥልቅ ፍቅር እንደነበረው እና አሁንም ክለቡን እንደሚወደው የተናገረ ሲሆን በዚሁ ቡድን ቆይታውም የሁለት ዓመት የውል ጊዜ እየቀረው ለካሳዬ አራጌ አጨዋወት አትሆንም ተብሎ ከክለቡ ጋር እንዲለያይ በተደረገበት ጊዜ ወደ ቤቱ በማምራት ስቅስቅ ብሎ ማልቀሱንና የውል ማፍረሻውንም ቡድኑ መክፈል ሲገባው ራሱ መክፈሉንም ይናገራል፤ ሊግ ስፖርት ከፍፁም ጥላሁን ጋር በኳስ ህይወቱ እና በሌሎች ጥያቄዎች ዙሪያ አናግራው ተጨዋቹ የሰጣት ምላሽ ይመስላል፤ ተከታተሉት፤ መልካም ንባብ፡፡

ስለ ውልደቱ፣ እድገቱ እና የኳስ ጨዋታ አጀማመሩ

“ተወልጄ ያደግኩት ቄራ በሚገኘው የአልማዝዬ ሜዳ አካባቢ ነው፤ እግር ኳሱን መጫወት የጀመርኩትደግሞ ከህፃንነት ዕድሜዬ አንስቶ በእዛው አቅራቢያ በሚገኘውና አሁን ላይ ትምህርት ቤት በተሰራበት የአሸዋ ሜዳ ላይ ነው፤ ያኔ ኳሱን የአምስት እና የስድስት ዓመት ልጅ ሆኜም ነበር ስጫወት የነበርኩት”፡፡

በሕፃንነትህ ዕድሜህ ላይ ስለነበረህ የኳስ ፍቅር

“በወቅቱ የነበረኝን የኳስ ፍቅር ፈፅሞ አልረሳውም፤ በህይወት ሳልፈጠር ራሱ እግር ኳስ ለእኔ የተፈጠረች ያህል ስሜትም ኖሮኝ ነበር ኳሱን ወድጄው እና አፍቅሬው ስጫወተው የነበርኩት”፡፡

ኳስን መጫወት ሲጀምር አርአያው /ተምሳሌቱ/ አድርጎት ስለነበረው ተጨዋች

“በሕፃንነት ዕድሜዬ መጀመሪያ ላይ ምኞቴ ታላቅ ነበርና ብራዚላዊውን የባርሴሎና ኮከብ ተጨዋች ሮናልዲኒኦ ጎቾን ነበር ሞዴሌና አርኸያዬ አድርጌው ስጫወት የነበረው፤ ወደ አገራችን ተጨዋቾች ስመጣ ደግሞ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና በተለያዩ ክለቦች ውስጥ ተጫውቶ ያሳለፈውን እነ አስራት መገርሳን የመሳሰሉት ተጨዋቾችን ነበር የማደንቀውና እንደ እነሱ ለመሆን በመመኘትና በጣምም እወደውና አደንቀውም ስለነበር ነው እሱን ጭምር ተምሳሌቴ ላደርገው የቻልኩት”፡፡

በልጅነት ዕድሜህ የእግር ኳስ ተጨዋች እሆናለው ብለህ አቅደህ ነበር የተነሳከው

“በፍፁም፤ ያኔ ኳስን እጫወት የነበረው ለስሜቴ ስልና ኳስንም በጣም ስለምወደው ነው፤ ከ10 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናቶችንም ቸሬ ባቋቋመው የፕሮጀክት ቡድን ውስጥ ቤተሰቦቻችንን አስፈቅዶ በመውሰድ እንድንጫወት ያደርገን ስለነበር ስለ ክለብ መግባት ፈፅሞ አላሰብኩም ነበር፤ በኋላ ላይ ግን ትንሽ አደግ እያልኩ ስመጣና ወደ ማርቆስ ዕድሜያቸው ከ12 እና ከ15 ዓመት በታች የሆናቸው ፕሮጀክት ቡድኖች ውስጥ ገብቼ ስጫወት በክለብ ደረጃ መግባት አለብኝ ወደሚል ስሜት ስለተሸጋገርኩ ከዛ በኋላ ነው መጀመሪያ ላይ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ የታዳጊ ቡድን አምርቼ ልጫወት የቻልኩት”፡፡

ስለ መጀመሪያ ክለቡ እና አገባቡ

“የመጀመሪያ ክለቤ የቅ/ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን ነው፤ ወደዛም ላመራ የቻልኩት ቄራ አንበሳ የታዳጊዎችን እግር ኳስ ውድድር አዘጋጅቶ ነበርና በወቅቱ የቅ/ጊዮርጊስ የታዳጊ ቡድን አሰልጣኝ በነበረው ደረጄ ተስፋዬ /አንገቴ/ አማካኝነት ነው ተመልምዬና የሙከራ ዕድሉም ተሰጥቶኝ ያን በማለፍ ክለቡን በ2009 ዓ/ም ላይ የተቀላቀልኩት”

በቅ/ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን ውስጥ ስለነበረው ቆይታ

“ቅ/ጊዮርጊስን ስቀላቀል ጥሩ ጊዜን ነበር ያሳለፍኩት፤ ጥሩ አሰልጣኝና ጥሩ ቡድንም ነበረን፤ በጣም ለፍተን በመጫወትም ነው ያኔ በነበረው የምድባችን ውድድር ላይም ለአንድም ጊዜ ሳንሸነፍ ዋንጫውን ልናነሳ የቻልነው፤ ባገኘነው ውጤትም በጣም ነበር የተደሰትኩት፤ በአጠቃላዩ ውድድራችን ላይ ግንለአንድም ጊዜ ተሸንፎ የማያውቀው ክለባችን ከተጋጣሚው የሐዋሳ ከተማ ክለብ ጋር ተጫውቶና በጨዋታውም ተሽሎና የግብ አጋጣሚዎችንም በማግኘቱ ረገድ ልቆ እያለ ግጥሚያውን በድል ሊወጣ ከጫፍ በደረሰበት ሰዓት ላይ እነሱ ከእኛ በአካል ብቃቱ ረገድ ትላልቅና ጉልበተኞችም ስለነበሩ ከማዕዘን በተመታ ኳስ በግንባር ተገጭቶ በተቆጠረብን ግብ አቻ ሆነንበፍፁም ቅጣት ምት በመሸነፍ ውድድራችንንአንገት በሚያስደፋና አሳዛኝ በሆነ መልኩ የተሸነፍንበት ጨዋታ ፈፅሞ አይረሳኝምና ያ ሁሌም ቢሆን ከውስጤ አይወጣም”፡፡

ለቅ/ጊዮርጊስ እስከዋናው ቡድን ዘልቆ ስላለመጫወቱና ከቡድኑ ጋር ስለመለያየቱ

“ከቅ/ጊዮርጊስ መለያየቱን በፍፁም አልፈልግም ነበር፤ ቡድኑን ከራሴ በላይም ወድጄው ነበር፤ አሰልጣኝ ደረጄ ተስፋዬም ወደ ተስፋው ቡድን ልታሳድገኝ ስትል በጊዜው የነበረው የተስፋው ቡድን አሰልጣኝ እኔን ከሰውነት ብቃቴ ጋር በተያያዘ ሊያየኝ ባለመቻሉ ከክለቡ ጋር በመለያየትና መልቀቂያዬንም በመቀበል ወደ ኢትዮጵያ ቡና ወጣት ቡድን ላመራ ቻልኩ”፡፡

ኢትዮጵያ ቡናን ስለተቀላቀለበት መንገድና በቡድኑ ውስጥ ስለነበረው ቆይታ

“ኢትዮጵያ ቡናን መጀመሪያ ለመቀላቀል የቻልኩት በወጣት የተስፋው ቡድን ላይ ለመጫወት ነበር፤ ወደ ቡድኑ ያመራሁበት ሁኔታም ቅ/ጊዮርጊሶች በድጋሚ እናሳድግሃለን የሚል ተስፋን ሰጥተውኝ ነበርና ያን እየተጠባበቅኩኝ በነበረበት ሰዓት ላይ ነው ጊዜው ወደ ሶስተኛው ወር ላይ በመሄዱና የህዳር ወርም በመግባቱ ክለቦች ወደ ዝግጅት የሚገቡበት ወቅት ደረሰና መስዑድ መሐመድ ሰፈር ውስጥ ሲመለከተኝና አንተ ልምምድ አልጀመርክም እንዴ? ባለኝ ሰዓት እስካሁን ጥሪ አልተደረገልኝም ስለው በቃ በቡና የሙከራ እድል እንዲሰጥህ አደርግሃለው ብሎኝና ወደ ቡድኑ ሲልከኝ በወቅቱ በነበረውና አሁንም ክለቡን እያሰለጠነ ባለው አሰልጣኝ ዮሴፍ ተስፋዬ ልወደድ ስለቻልኩ የቡና ወጣት ቡድንን ተቀላቀልኩ፤ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥም ተወዳጅነቴ ጨምሮም የዋናውን ቡድን ለመቀላቀልና በአንድ አንድ ጨዋታዎች ላይም ለመጫወት ቻልኩኝ፤ ይህ ሆኖ ሳለ ግን በቡና የነበረኝ የዋናው ቡድን ቆይታዬ ዘላቂ ይሆናል ብዬ ባስብም እንደጠበቅኩት አልሆነምና አሰልጣኛችን ዲዲየር ጎሜዝ ከውጤት ማጣት ጋር ተባሮ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ወደ ቡድኑ በመጣበት ሰዓት እኔም ከክለቡ ጋር የሁለት ዓመት የውል ጊዜ እያለኝ ከምወደው ቡድን ጋር ልለያይ ቻልኩ”፡፡

ከቡና ጋር ስለተለያየበት ሁኔታ

“በቡና ቆይታዬ አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ወደ ቡድኑ ሲመጣ ከክለቡ ጋር እንድቀጥል ያልተደረግኩበትን ምክንያት እኔ ፈፅሞ አላውቀውም፤ ዲዲየር ጎሜዝ ቡድኑን ለቅቆ ካሳዬ አራጌ ሲመጣበክለቡ አካባቢ በሚገኙ አንድአንድ ሰዎች ነው የሙከራ ዕድሉ ይሰጥሃል ከተባልኩ በኋላ ሜዳ ብገባም ብዙም ሊያዩኝ ስላልቻሉና የእነሱ ትኩረት ሁሉ በሌሎች ተጨዋቾች ላይም ስለነበር እኔን ለእሱ አጨዋወት እንደማልሆን በሚል ተነግሮኝ ቡናን እንድለቅ በተደረገ ጊዜ በጣም አዝኜ ነው ወደ ቤት በመሄድ ስቅስቅ ብዬ ያለቀስኩት፤ ምክንያቱም ቡናን በጣም ወድጄው ነበር፤ አሁንም ጭምር ክለቡን እወደዋለው፤ በዚህ ቡድን ቆይታዬም ሰዎች ያኔ እኔን ቢጥሉኝም ከዛ በኋላ በነበረኝ የኳስ ህይወት ለከፋ ቡናም ሆነ ለአዲስ አበባ ከተማ ቡድኖች ውስጥ ገብቼ ስጫወት በስኬታማነት የውድድሩን ጊዜያቶች እንዳጠናቅቅ ስላደረገኝና ፈጣሪም ስላልጣለኝ በቀጣይነትም ጥሩ ነገር እንደሚገጥመኝ አስባለው”፡፡

ለካሳዬ አጨዋወት አትሆንም ያለህ ማነው?….እሱ ራሱ ነው?

“በቀጥታ እንዲህ ያለኝ ማንም የለም፤ እኔ ከክለቡ ጋር እንደምቀጥልም ነበር የማውቀው፤ ከዛ ከቢሮ ዘሪሁን ለእኔና ለሁለት የቡድኑ ተጨዋቾች ይደውልና ለዝግጅት እንደምንፈለግ ነው የተነገረን፤ እዛ ስንደርስ ካሳዬ እኛን ለሙከራ እንደሚፈልገን ተነገረንና ሶስት ቀን ያህል ተመላልሰን ለ10 ደቂቃ ለሚደርስ ጊዜም ነበር ሳንታይ ካሳዬ እንደማይፈልገን በክለቡ በኩል ተነግሮን ከቡና ልንለያይ የቻልነው፤ በቡና ቆይታዬ ሌሎች ተጨዋቾች እስከ 40 ሺ እየተከፈላቸው እኔ ስለሚከፈለኝ 3 ሺብር ለአንድም ቀን አስቤ አላውቅም ነበር፤ እኔ ከቡና ጋር ቀጥዬ ክለቡን ማገልገል ነበር የምፈልገው፤ ይሄ ግን እንዳይሆን ሆነ፤ ለቡና እንደማልመጥንና ለካሳዬ አጨዋወትም እንደማልሆን ተደርጌም ነው በአንድ አንድ ሰዎች አማካኝነት ክለቡን እንድለቅም የተደረግኩትና ያ መፈጠሩ በጣም አሳዝኖኛል፤ ይባስ ብሎ ደግሞ ለእኔ 3 ሺብር ደመወዝ እየተከፈለኝና የሁለት ዓመት ኮንትራትም እየቀረኝ የውል ማፍረሻን ራሴ ከፍዬም ከቡድኑ እንድለያይ የተደረገበት ሁኔታም የሚያስገርመኝ ነው”፡፡

ከቡና ጋር አለመቀጠልህ ይቆጭሃል….?

“አዎን፤ በሰዓቱ ያኔ የገባሁበትን ሁኔታ እንዳማርር አድርጎኝ ነበር፤ ከዛ በኋላ ሳስበው ግን ያለኝን አቅም አውቀው ስለነበር ቡና ለዛሬ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሴ ትልቁን አስተዋፅኦ አበርክቶልኛልና በዚህ አጋጣሚ ክለቡንሳላመሰግን አላልፍም”፡፡

በቀጣይነት ስለተዘዋወረበት ቡድን

“በወቅቱ በበርካታ የከፍተኛ ሊግ ክለቦች እየተፈለግኩኝ ካናገሩኝ በኋላ በማላውቃቸው ምክንያቶች ስልካቸውን እያጠፉብኝ ፊታቸውን ዞር ቢያደርጉብኝም የመጨረሻ  አማራጬ በሆነው ከፋ ቡና ክለብ ውስጥ ደመወዛቸው ትንሽ ቢሆንም ለእግር ኳሱ ካለኝ ፍቅር ወደ እነሱ አመራውና እዛ ልጫወት ቻልኩ፤ ከዚህ ቡድን በፊት አሰልጣኝ አስማሄል እኔን ለአዲስ አበባ ከተማ ቡድን ይፈልገኝ ነበር፤ ግን የክለቡ ቀጣይነት ላይ ጥያቄ ስለነበር ነው ከፋ ቡና አምርቼ በመጫወት ጥሩ የውድድር ጊዜን ያሳለፍኩት፤ ከፋ ቡናም በታሪኩ ሶስተኛ ወጥቶ አያውቅምም ነበርና ይሄን ውጤት በማሳካታችን በጣም ነው ደስ ያለኝ”፡፡

ወደ አዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በመዘዋወር ክለቡን ወደ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያልፍ ካስቻሉት ተጨዋቾች መካከል አንዱ ሆንክ…..

“ለእዚህ ውጤታማነት የመጀመሪያው ተጠቃሽ ሰው ሊሆን የሚገባው አሰልጣኛችን እስማሄል አቡበከር ነው፤ እዚህ ሀገር ላይ እውነትና ትክክለኛ ነገርን የሚሰራ ሰው ስሙ እንዲደበቅ ይደረጋል፤ እስማሄል ይሄን ቡድን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማሳለፍ ብዙ ለፍቷል፤ ጎበዝ አሰልጣኝም ነው፤ ከተጨዋቾች ጋር ያለው የስራ ቀረቤታም አንተን በሚያሳድግ ነገር ላይ ስለሆነ በሁሉም ተጨዋቾች ዘንድ ተወዶም ነው የውድድር ዘመኑን በስኬታማነት ያጠናቀቅነው፤ ለውጤቱ መገኘት እሱና ሌሎቹ የኮቺንግ ስታፉ አባላቶችም ለክለቡ መደረግ በሚገባው ነገር ላይ አመራሮቹ ጋር በድፍረት ሄደው ስለሚጠይቁም ያ ጭምር ጠቅሞንም ነው ባለድል የሆነው፤ ሌላው እኛ ተጨዋቾችም እርስበርስ ባለን ፍቅርና አንድነት እንደዚሁም ለአሰልጣኛችን ታክቲክም ተገዢ በመሆንም ስራችንን በአግባቡ እንሰራም ነበርና ይሄ ጠቅሞን ውጤታማ አድርጎናል፤ እኔም እንደ ግል ለዚህ ቡድን 11 የሚደርሱ ግቦችንም በማስቆጠር የክለባችንና የምድባችን ኮከብ ግብ አግቢና ተጨዋች በሚያስብለኝ ደረጃና በአጠቃላዩ የውድድር ደረጃም ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ኮከብ ግብ አግቢ ሆኜ ሊጉን ያጠናቀቅኩበት ሁኔታም ስላለ በሁሉም ነገር ደስተኛ ሆኜ ነው ዘመኑን ያጠናቀቅኩት”፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ወደ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ማለፉ ይገባው እንደሆነ

“አዎን፤ በጣም ነው የሚገባን፤ ከዛ ሊግ በላይ ቢኖር ራሱ ይገባናል፤ ይህን ስል ያለ ምክንያት አይደለም፤ የቡድኑ አንድነት አስፈሪ ነበር፤ ክለቦች እኛን ለማሸነፍ ሳይሆን ብዙ ጎል እንዳይገባባቸውም ነበር የሚመጡት፤ ባይገርምህ አራት የመሀል ተጨዋቾች ይዘው የሚገቡ ቡድኖችም ነበሩ፤ ይህ ማለት ምንድን ነው? እኛ ላይ ጎል አግብተው ለማሸነፍ ሳይሆን እነሱ ላይ የሚገባባቸውን ጎሎች ለመቀነስ ነበር፤ የሚገቡት እኛ በአንደኛው ዙር 11 ጨዋታ ተጫውተን 9ኙን ነው ያሸነፍነው፤ አንዱን አቻ ተለያየን፤ በ1ዱ ተሸነፍን ሁለተኛው ዙር ላይ ደግሞ ዋንጫ ከበላን በኋላ ትንሽ ደከም አልን እንጂ ሀይለኛ የሚባለው ቡድን ላይ ራሱ አላገባን ከተባለ ሶስት ግብ በትንሹ ነው የምናገባው፤ አንድነታችን ፍቅራችን፤ ከዛ ውጪም በሁሉም ስፍራ ጠንካራ ግብ ጠባቂ፣ አማካይና አጥቂዎች ስላሉንና በጭንቅላት የታገዘም ምርጥ ኮች ስለነበረን የእኛ ወደ ፕሪምየር ሊግ መግባት ጥያቄ የሚያስነሳ አይደለምና በእዚህ አጋጣሚ ለአሰልጣኝ እስማሄል አቡበከር ያለኝን አድናቆትና ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለው፤ አዲስ አበባ ከተማምየእኔ ቡድኔ ባይሆን ራሱ ወደ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ማለፉ በጣሙን ይገባዋልም ነው የምለው”፡፡

ወደ ጅማ አባጅፋር ስላደረገው ዝውውርና ስለቀጣይ ጊዜ የኳስ ህይወቱ

 

“የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የከፍተኛ ሊግ ውድድሩን ካጠናቀቀ በኋላ ሌሎች ሊጉን የተቀላቀሉት ቡድኖች አንድአንዶቹ ለተጨዋቾቻው ሽልማትን ከመስጠት ባለፈ አንድአንዶቹም ተጨዋቾችን እያስፈረሙ ያለበት ሁኔታን በማየቴና የእኛ ቡድን ጋር ደግሞ ስለቀጣይ ጊዜ ጉዞው ዝም ሲባልና ምንም አይነት እንቅስቃሴን ልመለከትም ስላልቻልኩ ሁኔታው ሲያስጨንቀኝና ሲያስፈራኝ ጊዜ እኔ የነገውን ሁኔታዬን ነው የማስበውና ከሚፈልጉኝ ክለቦች ውስጥ አንዱ ለሆነውና ለወጣት ተጨዋቾችም የመጫወት ዕድልን ይሰጣል ወደተባለው የአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ቡድን ውስጥ በማምራት ፊርማዬን ለማኖር ችያለው፤ ወደ ጅማ ከማምራቴም በፊት ወደ ኢትዮጵያ ቡናም ክለቡን እወደው ስለነበር በራሴ ጥያቄ ወደ እነሱ በማምራት ዘንድሮ ስለነበረኝ ጉዞ ሁኔታዎችን ያሳወቅኩበት ሁኔታም ነበር፤ ያ ሳይሆን ሲቀር ነው ከሌሎች ቡድኖች ጅማን አስቀድሜ ወደ ቡድኑ የገባሁት፡፡ በጅማ አባጅፋር በሚኖረኝ የጨዋታ ቆይታዬ ራሴን በጥሩ ሁኔታ በማዘጋጀት ስኬታማ ተጨዋች መሆንን፤ አልማለው፤ ይህንን እልሜንም አሳካለው”፡፡

በመጨረሻ….

“በእግር ኳስ ተጨዋችነት ዛሬ የመጣሁበት መንገድ ብዙ ችግሮችን ተቋቁሜ ነው፤ አንድአንዶቹ ኳሹን በማቆም ወደ ሌላ ስራ እንዳመራም ሊያደርጉኝ የሚችሉም ነበሩ፤ ያም ሆኖ ግን በፈጣሪ ፀጋና ቸርነት እነዛን ነገሮች ሁሉ ተቋቁሜ አሁን ላይ ወደምፈልግበት ስፍራ ላይ እየመጣሁኝ ስለሆነ ለእዚህ አምላኬን ለማመስገን እፈልጋለው፤ ከእዛ ውጪም በኳሱ ዛሬ ላይ እዚህ ለመድረሴ ወላጅ እናቴ ብዙ ነገሮችን አድርጋ ማለትም እንጀራ ሸጣና አባቴም ቢሆን አስቀድሞ ወደ ትምህርት እንዳመራ ቢፈልግም ከእኔ የኳስ ፍቅር በኋላ እሱም በፍላጎቴ ተሸንፎ ውጪ እያደረ መኪና በመጠበቅ ብሎም ደግሞ ከእጦት ጋር በተያያዘም እኔን ልጁን ለማሳደግ ሲል አላስፈላጊ ነገር ውስጥ በመግባት እስከመታሰር ደረጃም ላይ በመድረስ ብዙ ነገሮችን አድርጎልኝ የእኔን ህይወት ወደተስተካከል ሁኔታ እንዲያመራ ያደረገበት አጋጣሚ አለና እነዚህን ወላጆቼንና ሌላው በቅዱስ ጊዮርጊስ ተስፋ ቡድን ውስጥ ይጫወት የነበረው አምደፅዮን የተለያዩ የስፖርት ትጥቆችን እየሰጠኝና እያበረታታኝ እዚህ ደረጃ ላይ እንድደርስ ስላደረገኝ እሱንና በአሰልጣኝነት ሙያው እኔ ላይ ሰርተው ላለፉት አሰልጣኞች ቸሬ፣ ማርቆስ ደረጄ ተስፋዬና እስማሄል አቡበከርን ከልብ ለማመስገን እፈልጋለውኝ”፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P