ቅዱስጊዮርጊስ ከሀብቴ ጋርመንትና ህትመት ስራ ጋር በመተባበር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር የጥራት ደረጃ መስፈርት መሰረት በክለባችን አርማና መለያ ያሰራቸውን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን አቅርቧል ፡፡
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎቹ ከፍተኛ የጥራት ደረጃን ጠብቀው የተመረቱ ከመሆናቸውም ባሻገር እየታጠቡ ዳግም ጥቅም ላይ መዋል የሚችሉ ናቸው፡፡
ዋጋቸውም የአንዱ ጭምብል ዋጋ 30 ብር መሆኑን ክለቡ ተገልጿል

የፊት እና የአፍንጫ ጭንብሉን ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በቅሎ ቤት ዳሽን ባንክ ጎን ኖክ ማድያ አንደኛ ፎቅ ያለው ቢሮ በመገኘት ደጋፊዎቹ መግዛት እንደሚችሉ ክለቡ በይፋዊ ገፁ አስታውቋል ፡፡