Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ቅ/ጊዮርጊስ ለየት ብሎ ቢመጣም ወጥ አቋም ያሳየ ቡድን እስካሁን አልተመለከትኩም” “ፋሲል ከነማ እያለውኝ ወደ ሌላ ቡድን ከምትሄድ ተጨማሪ ገንዘብ አዋጥተንና ለምነን እንሰጥሃለን ያለኝ ደጋፊ ነበር” አብዱራህማን ሙባረክ /ግሪዳው/ /ድሬዳዋ ከተማ/

በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና ድሬዳዋ ከተማ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት መከላከያን ገጥሞ አብዱራህማን ሙባረክ /ግሪዳው/ ባስቆጠረው ብቸኛ ግብ 1-0 አሸንፏል፤ ድሬዳዋ ከተማ ባለድል መሆኑን ተከትሎም ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 9ኛ ሊያመራም ችሏል፤ ድሬዳዋ ከተማ በሊጉ የውድድር ዘመን ጉዞው ጠንካራ ተፎካካሪ መሆንን እንደ እቅድ ያስቀመጠ ሲሆን በሜዳው ላይ በሚኖረው የአሁኑ ተሳትፎም በርካታ ነጥቦችን እንደሚሰበስብም ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አስተያየቱን ሰጥቶታል፤ ሊግ ስፖርትና የድሬዳዋ ከተማው አጥቂ አብዱራህማን ሙባረክ በክለባቸው ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎ ዙሪያና ስለ ራሱ እንደዚሁም ደግሞ ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ጥያቄን አቅርበንለት የሚከተሉትን ምላሾች ሰጥቷል፡፡

ሊግ፡- በ10ኛው ሳምንት የጨዋታ መርሃግብር መከላከያን በሜዳችሁና በደጋፊያችሁ ፊት አሸንፋችኋል፤ ስለ ጨዋታው እና ስለ ውጤቱ አንድ ነገር ብትለን?

አብዱራህማን፡- ከመከላከያ ጋር ያደርግነው ጨዋታ ግጥሚያውን በሜዳችንና በደጋፊያችን ፊት እንደ መጫወታችን ውጤቱ በጣም ያስፈልገን ነበር፤ በደረጃው ሰንጠረዥም 12ኛ ስፍራ ላይ ከመቀመጣችን አኳያም ለጨዋታው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተንና በጥሩም መነሳሳት ወደ ሜዳ ስለገባን ግጥሚያውን ልናሸንፍ ችለናል፡፡

ሊግ፡- የድሉ ውጤት ለእናንተ ይገባችኋል?

አብዱራህማን፡- አዎን፤ እኛ የተሻልን ስለነበርን ማሸነፋችን ተገቢ ነው፤ እንደውም ወደ መጨረሻዎቹ ሰዓታቶች አካባቢ ከአጨራረስ ችግር ግቦችን ሳትን እንጂ በተጨማሪ ግብም ማሸነፍ እንችል ነበር፡፡

ሊግ፡- ተጋጣሚያችሁን መከላከያ እንዴት ተመለከታችሁት?

አብዱራህማን፡- ጥሩ ቡድን ነው፤ የመልሶ ማጥቃት አጨዋወትን ይጠቀማል፤ ያም ሆኖ ግን መሀል ላይ የእኛ ቡድን ከእነሱ ተሸሎ ተገኝቶ ስለነበር ልናሸንፋቸው ችለናል፡፡

ሊግ፡- ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ እንደተጀመረ ምን ውጤትን ለማምጣት ነበር እንደ እቅድ ይዛችሁ የነበረው?

አብዱራህማን፡- የእዚህ ዓመት ዋንኛው ተሳትፎአችን በሊጉ ላይ ጠንካራና ጥሩ ተፎካካሪ ሆኖ መቅረብ ነው፤ አሁን ያለንበትን ውጤት ስናየሁም መጥፎ የሚባል አይደለምም፡፡

ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሐዋሳ ከተማ ላይ ቆይታ አድርጋችሁ ነበር፤ ያን በምን መልኩ ነው የምትገልፀው?

አብዱራህማን፡- ወደ ውድድሩ ስፍራ ስናመራ ቡድናችንን በአንዴ አዋቅረን የነበረው በአብዛኛው በአዳዲስ ተጨዋቾች ስለነበር ወደሪትም ለመግባት ተቸግረን ነበር፤ ቀስ እያልን ስንሄድ ግን ለውጦችን በሂደት ተመልክተናልና ቡድናችንን እንደ አዲስነቱ ስመለከተው የተሻለ ጊዜን እያሳለፈ ነው፡፡

ሊግ፡- በድሬዳዋ ከተማ ክለብ ውስጥ ባለህ የቡድኑ ቆይታህ ራስህን አግኝተከዋል?

አብዱራህማን፡- በፍፁም፤ እያሳየሁት ያለው አቋም እኔነቴን አይገልፀውም፤ በጉዳት ላይ ስለነበርኩ ከሁለት ዓመት ቆይታ በኋላ ነው ቡድኑን የተቀላቀልኩት፤ ኳሱን በእዛን የጉዳቴ ወቅት ብዙም ባልጫወትም አሁን ላይ ግን እኔነቴን ስመለከተው ለጨዋታዎች ጥሩ መነሳሳት እየታየብኝ ነው፤ እንደ በፊቱ ለመሆንም እየተንገዳገድኩም ነው ወደ በፊቱ ብቃቴና አቅሜም ዳግም እንደምመለስም እርግጠኛ ነኝ፡፡

ሊግ፡- በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ለየት ብሎ የቀረበብህ ቡድን ማን ነው?

አብዱራህማን፡- ቅ/ጊዮርጊሶች በውድድሩ ላይ ከሌሎች አኳያ በንፅፅር ለየት ብለው ቢቀርቡም ወጥ አቋም ያሳየ ቡድንን ግን ፈፅሞ አልተመለከትኩም፤ አብዛኛዎቹን ቡድኖች ማለት ይቻላል በተመሳሳይ አቋም ላይ ነው የሚገኙት፡፡

ሊግ፡- ድሬዳዋ ከተማ ካደረጋቸው ግጥሚያዎች በጣም የሚቆጭህ የቱ ነው…ያስደሰተክስ ግጥሚያ?

አብዱራህማን፡- የሚያስቆጨኝ ጨዋታ ከወላይታ ድቻ ጋር ያደረግነውን ነው፤ ለቡድኔ ምንም ነገር ሳልሰራ የወጣሁበት ስለነበር ያን ግጥሚያ አልረሳውም፤ ያስደሰተኝ ጨዋታ ደግሞ መከላከያን በሜዳችንና በደጋፊያችን ፊት ከማሸነፋችን በተጨማሪ የድሉንም ግብ ያገባሁት እኔ ስለሆንኩ ይሄ መሆን መቻሉ ለየት ያለ የደስታ ስሜት እንዲሰማኝ አድርጎኛል፡፡

ሊግ፡-?

አብዱራህማን፡-

ሊግ፡- በእግር ኳስ ተጨዋችነት በተለያዩ ክለቦች ውስጥ ተጫውተህ አሳልፈሃል፤ ለአንተ ምርጡ ጊዜ የት እያለ የነበረው ነው?

አብዱራህማን፡- በፋሲል ከነማ ያሳለፍኩት ነዋ! እዛ እያለው ከምርጥ ጊዜው በተጨማሪ ከባድ ወቅትንም ላሳልፍ ችያለው፡፡

ሊግ፡- ከባዱ ወቅት ምን ነበር?

አብዱራህማን፡- ጉዳት ነዋ! በተለይ 2010/2011 ከሜዳ እንድርቅ አድርጎኝ ስለነበር ያ ለእኔ መጥፎ ወቅት ነበር፡፡

ሊግ፡- በፋሲል ከነማ ክለብ ውስጥ እያለህ ክለቡን እንዳትለቅ በመፈለግ አንድ ደጋፊ ያለ ነገር እንደነበር ሰማን፤ እሱ ምንድን ነው?

አብዱራህማን፡- አዎን፤ በወቅቱ የውል ጊዜዬን ጨርሼ በሌሎች ቡድኖች እየተፈለግኩኝ ነበር፤ ያኔ ታዲያ ከቡድኑ እንዳልወጣ የሚፈልግ ደጋፊ ስለነበር ግሪዳው ከእዚህ ቡድን መውጣት የለበትም ሌሎች ቡድኖች ሊሰጡት ካሳቡት ተጨማሪ ገንዘብ አዋጥተንና ለምነን እዚሁ እናስቀረዋለን ነበር ያለኝ፡፡

ሊግ፡- ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ ወደየትኛው ቤት የሚያመራ ይመስልሃል?

አብዱራህማን፡- የእዚህን ጥያቄ መልስ መመለስ ይቅርብኝ፡፡

ሊግ፡- ወደ ዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ እናምራ እነሱን በምን መልኩ ተመለከትካቸው?

አብዱራህማን፡- ውጤቱ ብዙም አስደሳች ባይሆንም ከሜዳ ላይ እንቅስቃሴ አንፃር ጥሩ ጊዜን ነበር ያሳለፍነው፤ ቡድናችን በጨዋታው ተስፋ ሰጪና አዲስ ነገርን ለማሳየት ሞክረዋል፤ እንደዛም ሆኖ በስራ ሊስተካከልና ሊሻሻል የሚችልን ነገርም አይተንበታልና ይሄን ነው ለማየት የቻልኩት፡፡

ሊግ፡- በአፍሪካ ዋንጫው ለአንተ ምርጡ ብሔራዊ ቡድን ማን ነው?

አብዱራህማን፡- ከውድድሩ ብትሰናበትም ለእኔ ምርጧ የነበረችው ሀገር ኮትዲቯር ናት፡፡

ሊግ፡- ምርጡ ተጨዋችስ ማን ነበር?

አብዱራህማን፡- ለእኔ የካሜሮኑ ዛምቦ አንጉኢሳ ለየት ብሎብኛል፡፡

ሊግ፡- የአፍሪካ ዋንጫውን ማን የሚያነሳ ይመስልሃል /ጥያቄው የቀረበለት ረቡዕ ዕለት ነበር?

አብዱራህማን፡- አዘጋጇ ካሜሮን የምታነሳ ይመስለኛል፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P