Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“ቅ/ጊዮርጊስ ሻምፒዮና ይሆናል፤ እኛም ሁለተኛ ካልሆንን ሶስተኝነትን አናጣም” “ኳስ ይዞ በመጫወት ከእኛ የሚሻል ቡድን የለም” ይገዙ ቦጋለ /ሲዳማ ቡና/

 

በኢትዮጵያ  የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮና  ቅ/ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ሽንፈቱን  በፋሲል ከነማ ቢቀምስም አሁንም መሪነቱን እንደያዘ ነው።  ሌላኛው ቡድን ሲዳማ ቡና ደግሞ  ባህርዳር ከተማን  ማሸነፉን ተከትሎ የሶስተኛነቱን ደረጃ እንደያዘ ይገኛል።

የአሰልጣኝ ገ/መድህን ሀይሌው  ሲዳማ ቡና  በእዚህ የሊግ ውድድር  ጠንካራ  ተፎካካሪ ቢሆንም  በሊጉ ቀጣይ ቀሪ ጨዋታዎች  ለሁለተኝነት እንደሚጫወቱና  ያ የማይሳካ ከሆነም  የሶስተኛነት ደረጃን  እንደማያጡ የቡድኑና  የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ኮከብ ግብ አግቢ ይገዙ ቦጋለ  ከሊግ ስፖርት ጋዜጠኛው መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር ባደረገው ቆይታ ገልጿል።

ሊግ ስፖርት  እና   ይገዙ ቦጋለ  በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ ያደረጉት ቃለ-ምልልስ የሚከተለውን ይመስላል።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ እስካሁን ስለነበራቸው የውድድር ቆይታ

“የውድድሩ ጉዞአችን ሁለት መልክ ያለው ነው።  የሊጉ ጅማሬ ላይ መቀዛቀዝ ነበር።  አሁን ላይ ደግሞ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው የምንገኘው።  የተሻለም ነገር አለን። በጥሩ ሁኔታ  እየሄድንም ነው”።

ስለ ጥንካሬያቸው እና ክፍተታቸው

“የእኛ ቡድን  በአብዛኛው  ጠንካራ ነው፤ ጥንካሬውም ከበረኛ አንስቶ እስከ አጥቂው ክፍል  ላይ ያለው ጎኑ ነው።  ያለበት ክፍተቱ ደግሞ  በምንሰራቸው ጥቃቅን  ስህተቶች  በተለይም የመጀመሪያው ዙር ላይ  ዋጋ እየከፈልን የነበርንበት ሁኔታ ነው።  ከላይ ከጠቀስኩት ውጪ  ሌላ  ያለው ነገር  በተመሳሳይ ስህተት  ዋጋ እየከፈልን የምንገኝበትም ሁኔታ ነው”።

ባሳለፍነው ጨዋታ  ባህርዳር ከተማን በመርታት ባለድል ሆናችኋል፤ ጨዋታው ምን መልክ ነበረው?

“እነሱ በሜዳቸው እና  በደጋፊዎቻቸው ፊት ስለሚጫወቱ  አስቀድመን  ጨዋታው ከባድ እንደሚሆን ገምተን ነበር፤   እኛም ካለንበት ስፍራ ደረጃችንን ለማስጠበቅ እና ግጥሚያውንም ለማሸነፍ   ነበር ወደ ሜዳ በሚገባ ተዘጋጅተን  የገባነው።  በስተመጨረሻም ግጥሚያውን  ከፈጣሪ  ጋር አሳክተነዋል”።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ  ለቡድናችሁ አስቆጪ ጨዋታ የነበረው የቱ ነው?

“ከፋሲል ከነማ ጋር  ባህርዳር ላይ  ያደረግነው  ግጥሚያ  ነዋ!”።

የጨዋታው  አስቆጪነቱ ምን ላይ ነው?

“አስቆጪነቱ   እኛ   ከእነሱ  የተሻልን ስለነበርንና በመሸነፋችን  ነው። አሸንፈናቸው ቢሆን ኖሮ እኛም ተፎካካሪነታችን ይቀጥል ነበር። ባለቀ ሰዓትም ነው ጎል ገብቶብን ልንሸነፍና   ደረጃችንንም   ወረድ ያደረገብንና ነጥቡ እንዲሰፋብንም  ያደረገብን”።

በቤትኪንግ ፕሪምየር  ሊጉ  ከውድድሩም ሆነ  ከእናንተ ቡድን   ጎልቶ የወጣብህ ተጨዋች ማን ነው?

“ከእኛ ቡድን ከሆነ ጊት ካት ነው ጎልቶ የወጣው ተጨዋች።  ጥሩ ተጨዋች ነው ብዬም አስባለው።  በጣምም አስደምሞኛል።  ከአጠቃላዩ ውድድር  ከሆነ ደግሞ  ጥያቄው ለእኔ  ለመመለስ  ይከብደኛል”።

በቤትኪንጉ  ምርጡ   ቡድንስ….?

“ቅ/ጊዮርጊስ ነዋ!  ከምርጥነቱ ውጪ ሊጉንም በመምራት ላይ ይገኛል”።

ከቅ/ጊዮርጊስ  ያላችሁ  የነጥብ ልዩነት ሲታይ ሰፋ ያለ ነው፤ በእዚህ ዙሪያ ምን ትላለህ? ጠብቀኸስ ነበር?

“በእርግጥ ውድድሩን ስንጀምር  እኛም  ለዋንጫ ነበር ስንጫወት የነበረው።  ከመሪዎቹ ክለቦች ቅ/ጊዮርጊስ እና ተከታዩ ፋሲል ከነማ ጋር ስንጫወት ነው በመሸነፋችን በነጥብ ልንርቅ የቻልነውና ከጥንካሬያችንና አልመን ከተነሳንበት  ሁኔታዎች አንፃር  ይሄ ውጤት እኛን ይገጥመናል ብለን በፍፁም አልገመትንም ነበር”።

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ሁለተኛ ካልወጣችሁ ሶስተኛ ትወጣላችሁ?

“ይሄማ ግልፅ ነው ሶስተኛ እንደምንወጣ።  ብናጣ ብናጣ ሁለተኝነቱን እንጂ ሶስተኝነቱ ደረጃማ  የግድ የእኛ ነው”።

አሰልጣኛችሁ ገብረመድህን ሀይሌ እንዴት ይገለፃል?

“ስለ እሱ  ለመናገር  እና  ለመግለፅ   ቃላቶች ነው የሚያጥሩኝ።  እሱን የኢትዮጵያ  ህዝብ ሁሉ ያውቀዋል።  ለቡድናችንም የሚችለውን ሁሉ አድርጓል።  የሀገሪቱ ትልቁ አሰልጣኝ ስለሆነና ስለ እሱ ማንም ስለሚመሰክርም  እንዲህ ነው ብዬ ማውራት   አልችልም”።

ቤትኪንጉን ቅ/ጊዮርጊስ  ወይንስ ፋሲል ከነማ ያነሳዋል?

“ቅ/ጊዮርጊስ  ያነሳዋል ብዬ አስባለው።  ምክንያቱም እነሱ በጥሩ አቋም ላይ ነው የሚገኙት። ከእዚህ በኋላም ነጥብ ይጥላሉ ብዬ ስለማላስብ  እና ከሁለት ጨዋታ በኋላም ሁሉም ነገር ስለሚታወቅ ዋንጫው ወደ እነሱ የሚያመራ ይመስለኛል።”

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ  ተሳትፎ   ሲዳማ ቡና   እንዴት ይገለፃል?

“እንደ ቡድን ክለባችን ጠንካራ እንደሆነ ማንም ያውቃል።   ሲዳማ ቡና ከቅ/ጊዮርጊስም በላይ የቱም ቡድን  ነው ትኩረት ሰጥቶንም ወደ ሜዳ የሚገባው።  የውድድር ዓመቱም ጠንካራው ቡድን ነው። ማንምም ይመሰክራል”።

ሁሉም ቡድን ነው ለእናንተ ትኩረት ሰጥተው የሚገቡት? ለቅ/ጊዮርጊስ፣ ለፋሲል ከነማ እና  ለሌሎቹስ?

“አዎን፤  ለእኛም ለእነሱም  ትኩረት ይሰጣሉ።  ይበልጥ ግን የእኛ  ቡድን ኳስን ይዞ ስለሚጫወት  በእዛ ተሽለን ስለምንገኝ እና ጠንካራም ስለሆንን ነው”።

የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የኮከብ ግብ አግቢነቱን ከመምራትህ አኳያ በአንተ  አሸናፊነት የሚጠናቀቅ ይመስልሃል?

“ካለን የጎል ተቀራራቢነት አኳያ   ይሄን እርግጠኛ ሆኜ አዎ ብዬ አልነግርህም። ምክንያቱም  ውድድሩ ገና ነው። ያም ሆኖ ግን በእያንዳንዱ ጨዋታ ላይ ጎል ማግባት አለብኝ በሚል ትኩረት አድርጌ ወደ ሜዳ ስለምገባ እንደ ፈጣሪ ፈቃድ  ኮከብ ግብ አግቢ ሆኜ ብጨርስ ደስ ይለኛል። በየጌሙም ጎል ለማስቆጠር ስለምጥር  ኮከቡንም መጨረሻ ላይ የምናየው  ይሆናል”።

እስከ 30ኛው ሳምንት በሚኖረው ጨዋታ ምን ያህል ጎል ታስቆጥራለህ?

“ይህንን ያህል አገባለሁ አልልህም።  በየጨዋታው ግብ ለማስቆጠር ነው ወደ ሜዳ የምገባው”።

የእንግሊዝ  ፕሪምየር  ሊግ በማንቸስተር ሲቲ  አሸናፊነት ተጠኔቋል። ድሉ ይገባዋል?

“አዎ፤ ይገባዋል ብዬ ነው የማስበው።  ምክንያቱም  ዓመቱን ሙሉ ጥሩ ናቸው። በጣም ለፍተዋል። የልፋታቸውንም ዋጋ ነው ያገኙት። ጥሩ ባይሆኑ ለእዚህ ደረጃ አይደርሱም ነበር።  የተሻለ ነገር የሰራ የተሻለ ነገር ያገኛል።  ሁሉንም አሳምነውም ነው  ባለድል የሆኑት”።

ሊቨርፑልስ?

“በጣም ጠንካራ ተፎካካሪ ነበሩ። ለቻምፒየንስ ሊጉም ለፍፃሜ ደርሰዋል።  እንደ ሲቲ ሁሉ  ጥሩ ነበሩ”።

የአንተስ ቡድን?

“የማንቸስተር  ዩናይትድ ደጋፊ ነኝ። ሊቨርፑልን እወደዋለሁ።  የእኛ ቡድን ግን አልተሳካለትም”።

በዛሬው ቻምፒየንስ ሊግ ፋይናል  ዋንጫው ወደ ሊቨርፑል ወይንስ ወደ  ሪያል ማድሪድ?

“ሪያል ማድሪድን በጣም ስለምደግፈው እና ደስ ስለሚሉኝ ዋንጫውን እነሱ ቢበሉት ደስ ይለኛል”።

እስካሁን  ያስቆጠርካቸው ግቦች ለአንተ በቂ ናቸው?

“እንደ ጀማሪ ተጨዋችነቴ እና ከታች እንደ ማደጌ  እንደዚሁም ደግሞ  ለፕሪምየር ሊጉም ገና የሶስተኛ ዓመቴን እንደመያዜ ፈጣሪ ይመስገን የእስካሁኑ ጎሎቼ ጥሩ ናቸው። በፈጣሪ ፈቃድም ነው ይሄ ጎል የተገኘው።  በአምስቱ ቀሪ ጨዋታዎችም  ጥሩ ልምድ እያገኘው ስለምሄድ  ሌሎች ጎል የማስቆጠር እድሎች ይኖሩኛል”።

ወደ ዋናው ቡድን ካደግክ ጀምሮ ስንት ስንት ጎል እንዳስቆጠርክ?

“የዘንድሮ ያው ይታወቃል። 13 ጎሎች እስካሁን አለኝ።  ባደግኩበት 2011 ላይ ደግሞ በኮቪድ ውድድሩ እስከተቋረጠበት ሰዓት ድረስ  8  እንደዚሁም ባሳለፍነው ዓመት 6 ጎሎችን ለማስቆጠር በቅቻለሁ”።

በግል ባህርይ  እንዴት እንደሚገለፅ

“አስቸጋሪ ባህሪ  የለኝም።  ከሰዎች ጋር ቶሎ ተግባቢም ነኝ”።

በመጨረሻ…..

“እዚህ የደረስኩት በራሴ ሳይሆን  በፈጣሪ እርዳታ ስለሆነ እሱን  ማመስገን እፈልጋለሁ።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P