Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በሊጉ ከ1-5 ያለውን ደረጃ ይዘን እናጠናቅቃለን፤ አልሸነፍ ባይነታችን እና ተጋግዘን መጫወታችን ጠንካራ ጎናችን ነው” ግርማ ዲሳሳ /ባህር ዳር ከነማ/

በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ተሳትፎ ላይ የባህር ዳር ከተማው ሰባት ቁጥር ለባሽ ተጨዋች ግርማ ዲሳሳ በሊጉ ጥሩ እንቅስቃሴን ከሚያሳዩ ተጨዋቾች መካከል አንዱ ሲሆን ይህ ተጨዋች ክለባቸው በፕሪምየር ሊግ እያደረገ ባለው የውድድሩ ተሳትፎ ከ1-5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው እንደሚያጠናቅቁ ለሊግ ስፖርት ጋዜጣ ድረ-ገፅ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡
የባህር ዳር ከተማ ክለብ ዘንድሮ የሊጉን ውድድር በተቀላቀለበት የመጀመሪያው ዓመት ላይ ከወዲሁ እያስመዘገበ የሚገኘው ውጤት በአበረታችነት የሚጠቀስለት ሲሆን የሁለተኛው ዙር ላይም የተሻለ ውጤት ያመጣል ተብሎም ግምት ተሰጥቶታል፤ ስለ ክለቡ አጠቃላይ የሊጉ ተሳትፎ ፤ ስለ ጠንካራ እና ደካማ ጎናቸው እንደዚሁም ደግሞ ዘንድሮ ሊጉን በምን ውጤት ሊያጠናቅቁ እንደሚችሉና ሌላም ተጨማሪ ጥያቄን ለግርማ ዲሳሳ አቅርበንለት የሰጠን ምላሽ ይሄን ይመስላል፡፡
ሊግ፡- የባህር ዳር ከተማ የአንደኛው ዙር የእስካሁን ጉዞ ምን ይመስላል… ጠንካራ እና ክፍተት ጎኑስ ምንድነው ?
ግርማ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያው ዙር ተሳትፎአችንን ዘንድሮ ከታችኛው ሊግ እንደመምጣታችን ስንመለከተው እየሄድንበት ያለው ጉዞ አበረታች ነው፤ በውድድሩ ላይ ያለን ጠንካራ ጎንም በእያንዳንዱ ጨዋታዎቻችን ላይ ወደ ሜዳ ስንገባ አልሸነፍ ባይነታችን እና ተጋግዘን መጫወታችን ነው፤ በተቃራኒው ደግሞ እንደክፍተት የምንመለከተው በሜዳችን ላይ የምናደርጋቸውን ጨዋታዎች ነጥቦችን በእርግጠኝነት አንጥልም ብለን በትኩረት ማጣት ነጥብ የምንጥልበት አጋጣሚ አለና በእዚያ ላይ ያሉብንን ችግሮች ማስተካከል እና ማመጣጠን ይኖርብናል ብለን ነው እያሰብን የምንገኘው፡፡
ሊግ፡- የሁለተኛው ዙር ላይ ክለባችሁ ምን አይነት ቡድን ይኖረዋል?
ግርማ፡- ባህር ዳር ከተማ በሁለተኛው ዙር በሚኖረው የሊጉ የውድድር ተሳትፎው ብዙ ነገሮችን አስተካክሎ ለመቅረብ እንደሚችል ከወዲሁ እቅድን ነድፏል፤ በመጀመሪያው ዙር ላይም የእያንዳንዶቹን ተጋጣሚዎች አቋምም በሚገባ ተመልክቷልና በውድድሩ ጠንካራውን እና ከመጀመሪያው ዙር የተሻለውን ባህር ዳር ከተማን ጠብቁ ነው የምንለው፡፡
ሊግ፡- ባህር ዳር ከተማን ለመጥቀምስ በአንተስ በኩል ምን ይጠበቅ?
ግርማ፡- በባህር ዳር ከተማ ቆይታዬ እስካሁን ክለቤን በሚቻለኝ አቅም ሁሉ እያገለገልኩት ነው፤ ለቡድኑ ስጫወትም በእኔ ላይ የሚያምኑብኝን እና ብዙ ደጋፊዎችንም ለማትረፍ ችያለሁና፤ በቀጣዩ ጊዜም ይሄ ሳያዘናጋኝ ክለቤን ከአሁን በበለጠ መልኩ ለማገልገል ጠንክሬ እየሰራሁኝ ነው፤ ክለቤንም ከጓደኞቼ ጋር በጋራ ሆኜ ትልቅ ቦታም አደርሰዋለሁ፤ ለእዚህ ፈጣሪም ይርዳን ነው የምለው፡፡
ሊግ፡- የባህር ዳር ከተማ ደጋፊዎች በአንተ አንደበት ሲገለፁ?
ግርማ፡- የባህር ዳር ከተማ ደጋፊዎችን መግለፅ በጣም ነው የሚከብደው፤ እኛ የቡድኑ ተጨዋቾች ኳሱ ስራችን ስለሆነ ተከፍሎን ነው የምንጫወተው፤ ባይከፈለን ኖሮ አንጫወትም ነበር፤ ወደ ሌላም ስራ እናመራለን፤ ደጋፊዎቻችን ግን ምንም ነገር ሳይከፈላቸው ከኪሳቸው እያወጡ እና ተበድረውም በመምጣት ነው የትም ቢሆን መጥተው የሚደግፉን፤ ስለ እነሱ ምን ብዬ እንደምነግርህ አላውቅም፤ አለ አይደል እነሱ ከኋላችን አለንላችሁ እያሉን ስለሆነ ስለ እነሱ ለመናገር የምፈልገው፤ አይዟችሁ፤ አናሳፍራችሁም፤ የለፋችሁበትን ነገር ታገኛላችሁ በልልኝ፡፡
ሊግ፡- ባህር ዳር ከተማ ሊጉን በምን ውጤት ያጠናቅቃል?

ግርማ፡- የባህር ዳር ከተማ ክለብን በተመለከተ ከእዚህ በፊት እንደገለፅኩልህ የሊጉን ውድድር ከ1-5ኛ ባለው ደረጃ ያጠናቅቃል ብዬ ነበር፤ አሁንም ያንን ነው የምደግመው፤ የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች ለእኛ በጣም ነው የሚቀሉን፤ የገባነውን ቃላችንንም እንጠብቃለን፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ…..?

ግርማ፡- የእግር ኳስ ተጨዋችነት ህይወቴ ገና ጅማሬ ላይ ቢሆንም ለእስካሁኑ ለደረስኩበት ደረጃ ግን በዋናነት ለማመስገን የምፈልገው በቅድሚያ በብዙ ነገር የረዳኝን እግዚአብሄር ነው፤ በመቀጠል ቤተሰቦቼን እና ደጋፊዎቻችንን አመሰግናለሁ፤ አከብራችኋለሁም፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P