Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በሌለ እግር ኳስ ለተጨዋቾች መቶ ሃምሳና ሁለት መቶ ሺህ እየከፈሉ መቀጠል አንድ ቦታ ሊቆም ይገባዋል” ኮ/ል አወል አብዱራሂም /የኢት.እግር ኳስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት /

 

በተለይ ለሊግ ስፖርት
በአለም ሰገድ ሰይፉ

ቀለል ያለ ስብዕናው ብዙሃኑን በነፃነት እንዲቀርቡት አስችሏቸዋል፡፡ ዛሬ የፌዴሬሽኑን የሃላፊነት መንበር ሲጨብጥ ሳይሆን ከአነሳሱ
አንስቶ ደደቢትን ለዛሬው ትልቅ ደረጃ በማድረሱ ሚና ብዙሃኖች ጠንቅቀው ያውቁታል፤ የዛሬው እንግዳዬ ኮ/ል አወል አብዱራሂም፤
ዛሬ ዛሬ የኢትዮጵያ ፉትቦል ከሚያሳየው እድገቱ ይልቅ ከስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰቱ ጋር ተያይዞ እየተፈፀመ ያለው የደጋፊዎች ግጭት
አበይት አጀንዳ እየሆነ መጥቷል፤ እናም የፍም ያክል እየተፋጀ ያለው ሂደት እንዴት ሊገታ ይችላል? የሚለው ጥያቄ አሁን ድረስ
ምላሽ ማግኘት አልቻለም፤ ከላይ ባነሳኋቸው ስጋቶችና በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ኮ/ል አወል አብዱራሂም ከሊግ ስፖርት
ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር አለምሰገድ ሰይፉ ጋር የ30 ደቂቃ ቆይታ ነበራቸው፡፡

ሊግ፡- ማዕረግ አንሻፍፌ እንዳልጠራ ኮ/ል በሚለው ማዕረግ ልቀጥል?
ኮ/ል አወል፡- (…ሳቅ…) ሲቪል ከሆንኩ ስንት አመቴ፤ ከዚያ በኋላ ማዕረግ ከየት ይመጣል ብለህ ነው?
ሊግ፡- አዲሱን ሹመት እንዴት እያጣጣምከው ነው?
ኮ/ል አወል፡- ማጣጣም የምትለዋ ነገር እንዴት እየለመድከው ነው በምትለው ሃረግ ትስተካከልልኝ፡፡
ሊግ፡- እሺ እንዴት እየተላመድከው ነው?
ኮ/ል አወል፡- ያው አይለመድ ነገር የለም እየተላመድነው ነው፤ በዛ ላይ በተቻለ መጠን ህዝባችን የሚፈልገውን የኳስ ለውጥ
ማምጣት ካልቻልን የሰው ለውጥ ብቻ ማድረግ ትርጉም ያለው አይመስለኝም፤ በመሆኑም ያ እንዳይሆን እቅድ ተኮር ስራዎችን
እያከናወንን ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ጊዜ የማይሰጡ ስራዎች ላይ ትኩረት አድርገን እየሰራን ነው፡፡
በተለይ ደግሞ የምናከናውናቸው ስራዎች በአጠቃላይ ግልፅና ተጠያቂነት ባለው መልኩ ነው፤ ለምሳሌ ውድድሮችን ብትወስዳቸው
ጊዜ የማይሰጡ ናቸው፡፡ እናም ውድድሮች ሲታጠፉም ሆነ ሲቀየር ግልፅ በሆነ አሰራርና ማንንም ተጋጣሚ ቡድን በማያስከፋ
መልኩ እንዲሆን እየተሞከረ ነው፤ ሊግ ኮሚቴው ሰባት አባላት ያሉት ሲሆን ሁሉም በተሟላበት ሁኔታ ነው ውሳኔዎች
የሚተላለፉት፤ እናም ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት በአንድ በኩል ጊዜ የማይሰጡትንና በሌላ በኩል ደግሞ በረጅም ጊዜ ፕላን
ለእግር ኳሱ እድገት መሰረት መሆን የሚችሉ ተግባራትን እያከናወንን እንገኛለን፡፡
ሊግ፡- ብዙ ጊዜ ከውጪ ሲባል እንደምሰማው የፌዴሬሽኑ ወንበር ይቆረቁራል ይሉና ልቀቁ ሲባሉ ደግሞ የሞት ሽረት ትግል ነው፤
አንተስ ይሄን ወንበር እንዴት አገኘኸው?
ኮ/ል አወል፡- እኔ ወንበሩን የምገልፀው በህዝብ አመኔታ እንደተሰጠ ቦታ ነው፡፡ ይሄን አላማ ከግብ ለማድረስ ደግሞ ተደላድሎ
መቀመጥ ሳይሆን ያለ አንዳች ማንቀላፋት ሌት ተቀን መስራት ሲቻል ብቻ ነው፡፡ መለኪያው ደግሞ ተግባር፤ ፉትቦልን በከፍተኛ
ደረጃ ለተጠማው የስፖርት ቤተሰብ አጥጋቢ ምላሽ መስጠት ሳትችል ወንበር ላይ ብቻ መሰየም ዋጋ ስለሌለው ይቆረቁራል በሚለው
ምርጫ ብሰማማ ይሻለኛል፡፡
ሊግ፡- ፌዴሬሽኑ ብዙ ጊዜ ሮሮዎች የሚሰሙበት ቦታ ከመሆኑ አንፃር የአራት አመቱን የስልጣን ዘመን ለመጨረስ ትዕግስት
አይፈትንም?
ኮ/ል አወል፡- እንዳልከው ብዙ ሮሮዎች ወደ ፌዴሬሽናችን ሊመጡ ይችላሉ፤ ነገር ግን ሮሮዎች ስለመጡ ብቻ መደንገጥ የለብህም፤
ከዚያ ይልቅ የመጣው ሮሮ አልያም አቤቱታ ይዘቱ ምንድነው? የሚለውን ነጥብ በአግባቡ መፈተሽ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም
አንዳንዴ አንተ ያላስተዋልከው በአንፃሩ ሮሮ አቅራቢው ያየው ነገር ሊኖር ይችላል፡፡ በመሆኑም የመጣው ሮሮ ዝም ብሎ ፍላጎት ብቻ
ነው? አሊያስ ተጨባጭ እውነታ አለው የሚለው ነገር በጥሞና ታይቶ መፍትሄ ይፈለጋል፡፡
አንዳንዴ ደግሞ ከዚህ ባፈነገጠ ሁኔታና በቀጣይነት ከተያዙት እቅዶች መካከል ሊተገበር የታሰበን እቅድ አሁን እንዲፈፀምላቸው
የሚጠይቁ ይኖራሉ፤ ከዚህ አንፃር ሁሉን ነገር በጥንቃቄ በማየት ሂደቱ ራሱ መልስ የሚሰጥበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ በመሆኑም

በዚህ ረገድ ሆደ ሰፊና አስተዋይ ሆኖ መስራት የግድ ይላል፤ ነገር ግን ለሚቀርቡ ሮሮዎች ሁሉ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ መቀመጥ ተገቢ
አይደለም፡፡
ሊግ፡- ከእናንተ ቤት ሊፀዳ ያልቻለው ችግር የፕሮግራም መቆራረጥ አባዜው ይመስለኛል….?
ኮ/ል አወል፡- ብዙሃኖችም እንደዚሁ ሊያስቡ ይችላሉ፤ ነገር ግን ዋናው መታወቅ ያለበት ነገር እውነታ ፕሮግራሙ እንዲታጠፍ
የደረስንበት ተጨባጭ ሃቅን መረዳቱ ላይ ነው፡፡ ፌዴሬሽኑ በራሱ ፍላጎት ብቻ ተንተርሶ ፕሮግራም የሚለውጥበት ምክንያት የለም፤
ጨዋታ ሲቀየርም ምክንያቱም አብሮ ይገለፃል፡፡ ከዚህ በኋላ ይቀበለው አይቀበለው መልስ የተሠጠው አካል ነው፡፡ የበለጠ ጥሩ
ምላሽ የሚሆነው ግን በአመቱ መጨረሻ ላይ የሚኖረን የአፈፃፀም እውነታ ነው፡፡
ሊግ፡- አሁን አንተ እያልከኝ ያለኸው የ2011 ዓ/ም የውድድር ዘመን በሰኔ በጀት መዝጊያ ይጠናቀቃል ማለት ነው?
ኮ/ል አወል፡- አዎ! የ2011 ዓ/ም የፕሪምየር ሊጉ የውድድር ዘመን በተያዘለት ፕሮግራምና እቅድ ይጠናቀቃል፡፡ ይሄን ሂደት
ስኬታማ ለማድረግ ደግሞ በሆነ ባልሆነ ምክንያት ፕሮግራሞች እንዳይታጠፉ መከላከል ነው፡፡ እስካሁን ባለው ሁኔታ ከአቅም በላይ
በሆነ ችግር ካልሆነ በቀር የሚቀየር ፕሮግራም የለም፡፡
ሊግ፡- እኔ እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ማንሳት እፈልጋለሁ፤ በሁለተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ከወልዋሎ አዲግራት
ሊያደርጉ የነበረው ጨዋታ የተሰረዘበት ምክንያት አጥጋቢ ነው ማለት ይቻላል?
ኮ/ል አወል፡- አሁን አንተ ኢትዮጵያ ቡናን በተመለከተ ላነሳከው ጥያቄ ሁለት አይነት መልስ ልስጥህ፤ እንደ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
አመራር ሆኜ ሳየው መቋረጡ ትክክል ነው እላለሁ፤ ምክንያቱም በጣም ለተቀደሰ አላማ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ህዝብ
ለህዝብ ለማገናኘትና ሰላም ለመፍጠር ወደሶስት መቶ የሚጠጉ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ይዘው ወደ ባህርዳር የሚሄዱበት ጊዜ
ነበር፤ እናም በማንኛውም መልኩ ይሄን አካሄድ የሚደግፍ ውሳኔ ከፌዴሬሽኑ የሚጠበቅ ነው፤ በዛ ላይ ወደባህር ዳር ይዘዋቸው
ከሚሄዱት ወጣቶች መካከል 150ዎቹ የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ደጋፊዎች ናቸው፡፡
ሊግ፡- ኢትዮጵያ ቡና ያለው ደጋፊ 150 ብቻ ነው እንዴ? በዛ ላይ ተጨዋቾቹ አብረው አልተጓዙም፤ እናም ለፕሮግራሙ መታጠፍ
የቀረበው ምላሽ አጥጋቢ ነው ማለት ይቻላል?
ኮ/ል አወል፡- እርግጥ ነው አሁን አንተ ያልከው ነገር ሊያስኬድ ይችላል፡፡ ሆኖም ወደዛ የሚጓዙት ደጋፊዎች ክለባቸውን የሚወዱ
ከመሆናቸው አንፃር ደስ ብሏቸው ወደስፍራው ሊሄዱ የሚችሉት ጨዋታው ሲራዘምላቸው ነው፤ እናም እንደ ፌዴሬሽኑ አመራር
ስታየው የታየዘላቸው አላማ በጎ ከመሆኑ አንፃር ሂደቱን የማያደናቅፍ ውሳኔ ማስተላለፍ ስለነበረብንና ወጣቶቹም ደስ ብሏቸው
እንዲሄዱ ለማስቻል ፕሮግራሙ መታጠፉ ትክክል ነው፡፡ ከዛ በኋላ ባለው ሁኔታ በሳምንቱ አጋማሽ ላይ እንዳይካሄድ የሚወጣው
ፕሮግራም ከተጋጣሚያቸው ቡድን ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ ነው እንጂ እንደዛ ማድረግ ይቻል ነበር፤ በመሆኑም በክብር
ከንቲባው የተያዘው ፕሮግራም እንዲሳካ ጨዋታው እንዲታጠፍ ተደርጓል፡፡
በሌላ በኩል እንደፌዴሬሽኑ አመራር ሳይሆን እንደ አንድ የስፖርት ቤተሰብ በግሌ ብትጠይቀኝ ክለቡ ደጋፊዎቹን አሳምኖ ጨዋታውን
ማድረግ ይችል ነበር፤ “ምንም እንኳን ፌዴሬሽኑ ጨዋታው ለሌላ ጊዜ ይራዘም ቢልም እኔ ማከናወን እችላለሁ” በሚል መወሰን
ደግሞ የክለቡ ሃላፊነት ነው፡፡
ሊግ፡- ግን እናንተ ይሄንን ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ስታስተላልፉት ከክለቡ ጋር ተመካክራችሁ ነው?
ኮ/ል አወል፡- አዎ! በዚህ በዚህ ምክንያት ጨዋታውን ልናራዝምላችሁ ነው አልናቸው፡፡ እነርሱም እሺታቸውን ገለፁልን፤ እርግጥ
ጥያቄው ከክለቡ የመጣ ባይሆንም እኛ የሚራዘምበትን ምክንያት ስንገልፅላቸው እነርሱም እሺ ጥሩ ነው ይራዘም የሚል ምላሽ
ሰጥተውናል፡፡ እናም ቀደም ብዬ እንደገለፅኩልህ በግሌ ብትጠይቀኝ እኔ ብሆን ጨዋታው እንዲራዘም አልፈቅድም፤ ምክንያቱም
ወደዛ የተጓዙት ደጋፊዎች ለተቀደሰ ዓላማ ሄደዋል፡፡ እዚህ ጋር ግን እኔ የክለቤን ጨዋታ እንዳላደርግ የሚከለክለኝ ነገር የለም ብለህ
ጨዋታውን ማስቀጠል የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ነው የሚታየኝ፡፡
ሊግ፡- ብዙሃኖች የእናንተን ተቋም የሚገልፁት ዝርክርክ በሚለው አነጋገር ነው፤ ይሄን አባባል አንተም ትጋራዋለህ?
ኮ/ል አወል፡- ፌዴሬሽኑን እነ አቶ እገሌ ናቸው እንደዚህ ያደረጉት ብሎ ማስቀመጥ ተገቢ አይሆንም እንጂ ረጅም አመት
እንዳስቆጠረ ተቋም በማይሆን ደረጃ ወርዶ ነው ያገኘሁት፡፡ እጅግ በጣም በሚገርም ሁኔታ ውስጡ የስራ መናበብ የሌለበት፣ የጊዜ
አስፈላጊነት የወረደበት ተቋም ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ የጊዜ አስፈላጊነትን ብትወስድ በጊዜ ምላሽ ለሚፈልጉ ጥያቄዎች
ውሳኔ አለመስጠትና በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰርተው ውጤት ለማምጣት ያለው ተነሳሽነት ደካማ ነው፡፡

በዛ ላይ የሙያተኛ እጥረት ይታያል፡፡ የአይቲና የህዝብ ግንኙነት ዲፓርትመንትን ብትወስድ በጣም ደካማ የሆነ ነው፡፡ በፋይናንስ
ረገድ ያን ያህል የተጋነነ ነገር ባይታይም ሂደቱ ግን በጣም የተንዛዛ ነው፡፡ ለምሳሌ ዳኛና ኮሚሽነርን ብትወስድ አበል ለመውሰድ
ጠዋት መጥቶ እዛው ይውላል፤ አንዳንዱ ደግሞ በተንዛዛው ስርአት ምክንያት አበልና ትራንስፖርት ሳይዝ ወደ ክፍለ ሃገር
ይመለሳል፡፡ በአጠቃላይ ካየከው ተቋሙ እንደተቋም ቁመና የሌለውና በደንብ ያልተፈተሸ መሆኑን ያሳይሃል፤ በመሆኑም የዚህ
አይነቱን የተዝረከረከረ አካሄድ መስመር ለማስያዝ ይቻል ዘንድ ከፅህፈት ቤቱ አንስቶ ብዙ መለወጥ ያለባቸው ነገሮች አሉ፤
በቅርቡም ይሄን የተንጋደደ አካሄድ ለማስተካከል በትጋት እየሰራን ነው፡፡
ሊግ፡- አንተ ደደቢትን በሃላፊነት ትመራ በነበረበት ወቅት አጥብቀህ የምትቃወመው የውድድሮችን መቋረጥ ነበር፤ አሁንስ አንተ
ወደዚህ ሃላፊነት ስትመጣ ችግሮቹን ለማቅለል ምን ያህል ዝግጁ ነህ?
ኮ/ል አወል፡- እርግጥ ነው በክለብ አመራርነት ለበርካታ አመታት ቆይቻለሁ፤ እኔ እመራው የነበረው ደደቢት ዝም ብሎ የተንሳፈፈ
አካሄድ ያለው ሳይሆን በተግባር ጥንካሬውን ማሳየት የቻለ ክለብ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በፌዴሬሽኑ ውስጥ የሊግ ውድድሮች መሪ
መሆኔ በፊት ያሳለፍኳቸው ልምዶች በእጅጉ ጠቅሞኛል፤ ይሄን እውነታ ለማረጋገጥ ደግሞ አንድ ቀን ሲመችህ የሊጉ ኮሚቴ
አባላትን መጠየቅ ትችላለህ፤ ከዚህ አንፃር እኛ የምንሰጣቸው ውሳኔዎች በሳልና ለውዝግብ የማይዳርግ ነው፤ ከምንም በላይ
መጠንቀቅ ያለብህ ነጥብ እዚህ ላይ ነው፤ የሚሰጡት ውሳኔዎች ለውዝግብ የሚዳርግ ከሆነ አደጋ አለው፤ ለምሳሌ ትላንት ማታ
የወሰንነውን ውሳኔ ልንገርህ (ያናገርኩት ረቡዕ ጠዋት ነው) በ5ተኛው ሳምንት የሊግ ጨዋታ የመቀሌ 70 እንደርታና የባህርዳር
ከነማ ጨዋታ ይገኝበታል፤ ይህን ውድድር ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ አድርገናል፡፡
ሊግ፡- ግን እኮ ቀደም ብላችሁ ይሄ ጨዋታ ፈፅሞ እንደማይሻር ተናግራችሁ ነበር?
ኮ/ል አወል፡- ርግጥ ነው እንደዛ ብለን ነበር፤ ነገር ግን የዚህ አይነቱ ጨዋታ ከፍተኛ ጥንቃቄና በሳል ውሳኔ የሚፈልግ ነው፤
በዚህ ረገድ እኔ ይዤ በቀረብኩት ፕሮፖዛል ላይ ከሊግ ኮሚቴው ጋር በሚገባ ተወያይተን በሙሉ ድምፅ ነው ያፀደቅነው፤ ይሄን
ፕሮፖዛል ያዘጋጀሁት ከመሬት ተነስቼ ሳይሆን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ነው፤ ለምሳሌ በሁለቱ ክልል ክለቦች
መካከል ያለው ግንኙነት እንዲሻሻል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው ያለው፤ በክልሉ ሃላፊዎችና በስፖርት ኮሚሽን አማካይነት ጥሩ
የሚባል ገንቢ ውይይት እየተደረገ ነው፤ ቀደም ብዬ እንደገለፅኩልህ የተጀመረው ጤናማ የሆነ የጋራ ምክክር ወደመሬት እስኪወርድ
ድረስ ጊዜ ይፈልጋል፡፡
እነዚህ ነገሮች ወደ ስፖርት ቤተሰቡና ደጋፊው ዘንድ ደርሰው በደንብ ከበሰለ በኋላ ሁለቱ ቡድኖች መገናኛታቸው የማይቀር ይሆናል፤
እስከዛ ጊዜ ግን ተቻኩለህ የምታደርገው ነገር የሚያስከትለው ጉዳት የላቀ ሊሆን ስለሚችል ጨዋታውን ለሌላ ጊዜ ማራዘሙ
ተገቢ ይሆናል፡፡ ቀደም ብዬ ለመናገር እንደሞከርኩት የሚተላለፉ ውሳኔዎች ማወዛገብ የለባቸውም፤ ከዚህ አንፃር የሁለቱን
ቡድኖች ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ያስተላለፍንበት ውሳኔ በምንም መልኩ ሊያወዛግብ አይችልም፡፡
ሊግ፡- ግን እንደ ፌዴሬሽን በየጊዜው የሁለቱን ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ከማራዘም ውጭ ፕላን ቢ ብላችሁ ያስቀመጣችሁት እቅድ የለም
ማለት ነው?
ኮ/ል አወል፡- እውነት ለመናገር መጀመርያ ላይ የአመቱን የውድድር ፕሮግራም ስናቅድ ሁሉም ቡድ ኖች በሜዳቸው ላይ
እንዲጫወቱ ተማምነን ነበር፤ በዚህን ወቅትም ጋዜጣዊ መግለጫ በምንሰጥበት ጊዜ ከጋዜጠኞች ከቀረበልን ጥያቄ መካከል
አንዱ ያነሳው ሃሳብ በጣም ጥሩ ሊባል የሚችል ነው፤ ልክ አሁን አንተ እንዳነሳከው እሱም ፌዴሬሽኑ ፕላን ቢ የለውም ወይ
ለምሳሌ በዝግ ስቴድየም ቢጫወቱ የሚል ነበር፡፡ ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው የእርሱ ምልከታ ጥሩ ነበር፤ እኛ ደግሞ ያሰብነው በወቅቱ
በሁለቱ ክልሎች ጥሩ ሊባል የሚችል ውይይት ተጀምሮ ስለነበር እነዚህ ሃሳቦች በፍጥነት ወደ መሬት ወርዶ ሁለቱም ቡድኖች
በየሜዳቸው ይጫወታሉ የሚል እምነት ስለነበረን እውነቱን ለመናገር ፕላን ቢ አልያዝንም፤ አሁን ግን የሁለቱ ክለቦች ግጥሚያ
በተስተካካይነት ከሚደረጉ ጨዋታዎች ጋር እየተመደቡ ነው፡፡
አሁን ለማድረግ ያሰብነው ሌላው ነገር ስድስቱን ክለቦች ጠርተን እናናግራቸዋለን፡፡ ይህም ማለት ተስተካካይ ጨዋታው በምን
መልኩ ይካሄድ የሚለው ነው፤ በዝግ ስቴድየም፣ በየሜዳችሁ አልያስ አዲስ አበባ የሚሉትን አማራጭ እናቀርብላቸዋለን፡፡
ሊግ፡- አዲስ አበባን ቢመርጡ ደጋፊዎቻቸውን ይዘው እንዲመጡ ትፈቅዳላችሁ?
ኮ/ል አወል፡- ኖ…. አዲስ አበባንም ቢመርጡ ጨዋታውን የምናካሂደው በዝግ ስቴድየም ነው፤ ይህ የሊግ ኮሚቴው ሃሳብ ነው፤
ይህ የሚሆነው ግን አሁን የተጀመሩት ውይይቶች አጥጋቢ በሆነ መልኩ ካልተጠናቀቁ ነው፤ በጣም የሚገርምህ እውነት በሁለቱም
ክለቦች መካከል ያለው ስሜት ጥሩ ሊባል የሚችል ነው “አብረን እንጫወት” የሚል ጥያቄ እያቀረቡልን ነው፤ ስለዚህ በዚህ
መልኩ ያለው የሁለቱ ቡድኖች ጉጉት እንዳይጎዳ እየጠበቅን በሌላ አንፃር ደግሞ ጉዳቶች እንዳይከተሉ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ
መጓዝ ተገቢ ነው የሚሆነው፡፡

ሊግ፡- ከላይ ሁለታችንም የተጋራናቸውን ስጋቶች ተከትሎ ብዙሃኖች የዘንድሮው ውድድር በሠላም ስለመጠናቀቁ ስጋት አላቸው፤
አንተስ?
ኮ/ል አወል፡- ምንም አይነት ስጋት የለም፤ የዘንድሮው የ2011 ዓ/ም ውድድር በሰላም ተጀምሮ በሰላም ይጠናቀቃል፤ ይህ
የሚሆነው ግን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስለተንቀሳቀሰ ብቻ አይደለም፤ እኛ በተቻለ አቅም የምንሰጣቸው ውሳኔዎች
ፍትሃዊና ውዝግብ እንዳያስነሱ ለማድረግ በጥንቃቄ መስራቱ ላይ ነው፤ በተረፈ ውድድሩን በሰላም ለማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ ትልቁ
ሃላፊነት ያለው በክለቦች፣ በደጋፊዎችና የየክልሉ ፌደሬሽን ነው፡፡ እኛ ማድረግ ያለብን ብቃት ያላቸው ሙያተኞችንና ኮሚሽነሮችን
መመደብ ነው፤ ከዚህ በተረፈ ችግር ሲፈጠር የማስተካከል ርምጃ እንወስዳለን፡፡ ለምሳሌ በዘንድሮው ውድድር በሁለት ጨዋታዎች
ላይ ለተፈጠረ ችግር ርምጃ ወስደናል፡፡ ዳኛም ኮሚሽነርም ተቀጥቷል፡፡ የስፖርቱን የእድገት አቅጣጫ መስመር ለማስያዝ ሁሉን
ነገር ለፌዴሬሽኑ ብቻ መተው ሳይሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት መተጋገዝ አለበት፡፡
ሚዲያውም ቢሆን የዘገባ ሽፋን ቅኝቱ መስተካከል ያለበት ይመስለኛል፤ በእኛ በኩል የሚሰጡትን ውሳኔዎች ተንተርሶ ያሉትን
ተጨባጭ እውነታዎች በመፈተሽ በመሰለው መንገድ መዘገብ ይችላል፡፡ ነገር ግን መናበበ መቻል አለብን፡፡ አንዳንዴ በችኮላና
በስሜታዊነት የሚቀርቡ ዘገባዎችን አስተውላለሁ፡፡ ፕሮግራም ስለታጠፈ ብቻ እግር ኳሳችን እየቀጨጨ ነው የሚል ጋዜጠኛ ካለ
አልገባውም ማለት ነው፤ ጨዋታ መቀየር ማለት እኮ የአለም ፍፃሜ አይደለም፤ ደግሞም አንድ ክለብ በጀት የሚይዘው ለአንድ
የውድድር ዘመን ነው እንጂ ለየእለቱ አይደለም፡፡ ርግጥ ነው ሰኔ 30 ካለፈ በጀት ተቃውሷል ይባላል፤ በተረፈ እኛ በያዝነው
ፕሮግራም መሰረት ምንም አይነት የበጀት መቃወስ አይኖርም፤ ፕሮግራሙም ከተያዘለት ቀን የሚያልፍበት ምክንያት አይኖርም፡፡
ሊግ፡- ፌዴሬሽናችሁ ያለበትን እዳ መክፈል ስላቃተው የፊፋን እገዛ ጠይቃችሁ ነበር፤ ይህ ሁኔታ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
ኮ/ል አወል፡- ይሄን ጉዳይ በተመለከተ በቀጥታና በቅርበት ጉዳዩን እየተከታተለ የሚገኘው ፕሬዝዳንታችን አቶ ኢሳያስ ጅራ በመሆኑ
እሱ ቢያብራራልህ የሚሻል ይሆናል፡፡
ሊግ፡- የልጅህ ያህል ተንከባክበህ ያሳደግከው የደደቢት ክለብ በአሁን ሰአት በፋይናንስ እጥረት እየተንገዳገደ ስታየው ምን ተሰማህ?
ኮ/ል አወል፡- (..ተከዘ..) እኔ ዛሬ ሳይሆን የተሰማኝ ከ5 አመት በፊት ክለቡን ያለ በቂ ምክንያት የወሰዱት ጊዜ ነው፡፡
በወቅቱ ክለቡን ከተረከበው አካል ቢያንስ ለአንድ አመት ያህል ስለክለቡ ምንም አይነት ኢንፎርሜሽን አልነበረኝም፤ ክለቡ
በወቅቱ ከእኔ ከተወሰደ በኋላ ስሜቴ ክፉኛ ተጎድቶ ነበር፡፡ ርግጥ ክለቡ ትልቅ ደረጃ እንዲደርስ ከተፈለገ ማንኛውም አካል ተረክቦ
ቢያስተዳድረው የእኔም ፍላጎት ነው፡፡
እኔ እጠብቅ የነበረው ክለቡ የያዘውን እቅድና ስትራቴጂ የበለጠ የሚያስቀጥል አካል ነበር፡፡ እኛ በወቅቱ ይሄን ክለብ በሁለት እግሩ
ለማስቆም ይቻል ዘንድ በልመናም ሆነ በተለያየ መንገድ ብዙ ርቀት ተጉዘናል፤ ከዚህ አንፃር ክለቡን ከእኛ ሲወስዱ የተሻለ ነገር
ሊፈጥሩለት ይችላል የሚል እምነት ይዤ ነበር፤ የነበረው ሁኔታ ሞራሌን በከፍተኛ ደረጃ የሚረብሽ ስለነበር ለአንድ አመት ያህል
ከአካባቢው መራቅና ስቴድየም ራሱ በዚያን ጊዜ ብሄራዊ ቡድኑ ሲጫወት ብቻ ነበር የገባሁት፡፡
ሊግ፡- ይሄን ያህል ውስጥህ ተጎድቶ ነበር ማለት ነው?
ኮ/ል አወል፡- አዎ! ተጎድቶ ነበር፡፡ ለዛም ነው በወቅቱ ለአንድ አመት ያህል ከሁሉ ነገር ርቄ መቆየትን የመረጥኩት፡፡ ከዚያ
በኋላ ግን አንዳንድ መረጃዎችን ስሰማ የክለቡ አደረጃጀትና የማኔጅመንት አካሄድ ትክክል እንዳልሆነና ከአመራርነት ይልቅ
በግለሰቦች ጫንቃ ላይ የተንጠለጠለ እንደሆነ ስሰማ ዛሬ ሳይሆን ያኔ ደደቢት አደጋ ሊገጥመው እንደሚችል ገምቻለሁ፤ ምክንያቱም
አንድ ስፖርት ክለብ ሲመሰረት እንዴት መመራት አለበት የሚለው ጥያቄ በአግባቡ መመለስ መቻል አለበት፤ ቀደም ሲል የነበረው
የደደቢት ክለብ ለውጥ ያመጣው በደመ-ነፍስ ሳይሆን አመራሩ ይከተለው በነበረው ዘይቤ ነው፤ ክለቡ በወቅቱ ምንም አይነት
የራሱ ገቢና ቋሚ ንብረት ሳይኖረው ለሌሎች የሃገራችን ክለቦች አርአያ መሆን የሚችል ተግባር መፈፀም የቻለው በአመራሩ
ብስለት ነው፡፡
በ2004 ዓ/ም በፊፋ መስፈርት በሃገራችን ካሉት ክለቦች መካከል በውጤት ሳይሆን በክለብ አደረጃጀት መስፈርት ደደቢት አንደኛ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ሁለተኛ ነው የወጡት፤ እናም ይሄን ያህል ርቀት ወደፊት የሄደን ክለብ ስትረከበው ዝም ብሎ መውሰድ
ሳይሆን በዛ አጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ሊሆን የቻለበትን ሚስጢር መፈተሽ ያስፈልጋል፡፡ በጣም የሚገርምህ ነገር ሐምሌ
05/2005 ዓ/ም ክለቡን ተረከቡኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ባለው ጊዜ ውስጥ የውጤት ሚስጥሩ ምንድን ነው? ብሎ ያናገረኝም ሆነ
የጠየቀኝ ሰው የለም፡፡
የክለቡ ባህል፣ እሴትና እንቅስቃሴ ምን ይመስላል? ብለው ለመጠየቅ አልደፈሩም፤ በዚህ ሁኔታ አንድ ሁለት ወር ግራ ተጋባሁና
ከሁለት ወር በኋላ ደውዬ ከእኔ ምንም የምትፈልጉት ነገር የለም እንዴ? ብዬ ስጠይቃቸው የደወልኩላቸው ሰው አይ የምንፈልገው
ነገር ካለ እንደውልልሃለን ለጊዜው ግን የምንፈልገው ነገር የለም ብሎ ዘጋኝ፡፡ እኔም ስሜቴ በጣም ተጎዳ፤ ከዚያ በኋላም አንድ
አመት ሙሉ ስለክለቡ ምንም አይነት መረጃ አልነበረኝም፤ ያለው ሁኔታ ክለቡን ወደፊት ብዙም ሊያስኬደው እንደማይችል

አነበብኩ፤ በዚህ ረገድ ደደቢት ብቻ ስለሆነ ሳይሆን ስለማያስፈልገኝና ስለማያገባኝ እንጂ እያንዳንዱ ክለብ የትኛው ላይ ነው
ጥንካሬው? ምን ላይ ነው ድክመቱ? የሚለውን ነገር ጠንቅቄ አውቀዋለሁ፡፡
በድምር ስናየው የኢትዮጵያ ክለቦች ትልቁ ችግራቸው ከፍተኛ የሆነ የእቅድና የማኔጅመንት ችግር ያለባቸው ናቸው፤ ሲነፃፀሩ አንድ
አሊያም ሁለቱ ሊሻሉ ይችሉ ይሆናል እንጂ ሁሉም የሀገራችን ክለቦች ከፍተኛ ሊባል የሚችል ችግር አለባቸው፤ እግር ኳሳችን
እንዲያድግ ከተፈለገ እቅድና ማኔጅመንቱ መስተካከል መቻል አለበት፤ በጀት መዳቢ አካላትም ይህ ችግር መስመር ሳይዝ በጀት
ለክለቦቹ ባይፈቅዱ ጥሩ ነው እላለሁ፤ እኔ እንደ ፌዴሬሽን አመራርነቴ ሳይሆን በግሌ በጀት መዳቢ አካላትን የምመክራቸው ምንም
ሳይኖር 30 እና 40 ሚሊዮን ብር ዝም ብሎ እንዴት ይመደባል? የክለቡ አላማ እቅድና ጉዞ ምን ይመስላል? የሚለው ነገር
በሚገባ ሊጤን ይገባል፤ አንድ ክለብ ቢያንስ በትንሹ የ5 አመት እቅድና ስትራቴጂ ሰርቶ ሊያቀርብ ይገባል፤ ይህ ሲሆን እንዴት
ወድቀህ እንደምትነሳ ታውቀዋለህ፡፡ ለምሳሌ ደደቢት የ11 አመት እቅድ ነው የነበረው፤ ይህ አሃዝ ለሶስት የተከፈለ ነበር፤
የፕሮጀክት፣ የዲቪዝዮንና የፕሪምየር ሊግ የሚሉት ናቸው፡፡ በ2002 ዓ/ም የፕሪምየር ሊጉን እየተካፈልን ከ2003 ዓ/ም
ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ ደግሞ የ5 አመት ስትራቴጂ ፕላን ነበረን፤ በወቅቱ አቶ ጌታቸው የሚባሉ ከፍተኛ የስፖርት ኤክስፐርትን
በመያዝ እሳቸው የሚመሩት አንድ አብይ ኮሚቴ ተቋቁሞ የ5 አመት ስትራቴጂ እቅድ ተቀርፆ ፀድቋል፡፡ በዚህ ፕላን መሰረትም
ደደቢት በቀጣዩ አምስት አመት ውስጥ የራሱ ስቴድየም ባለቤት መሆን አለበት የሚል ነው፤ በ2005 ዓ/ም 125 ሺህ ካሬ
ሜትር መሬት ከአዲስ አበባ መስተዳደር ተፈቀደ፤ ይህ ስቴድየም አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ 50ሺህ ተመልካች የሚይዝና
ግዙፍ የሆነ የቢዝነስ ማዕከላትን ያካተተ እንዲሆን ታስቦ የታቀደ ሲሆን ሁሉ ነገር ተጠናቅቆ የቀረን ርክክብ ብቻ ነበር፡፡ በመሆኑም
ይህን ርክክብ እንዲፈፅም ክለቡን ለተረካቢው አካል ዶክመንቱን ሰጠሁት፡፡ በኋላ ላይ ግን ይህ ብዙ የተደከመበት እንቅስቃሴ
ከግብ አለመድረሱን ነው የሰማሁት፡፡
ስለዚህ እቅድ ሊኖር ይገባል፡፡ ነገር ግን በአሁን ሰአት ክለቦቻችንም እያደረጉ የሚገኘው ካለ አንዳች እቅድ 30ም ትሁን 40
ሚሊየን ብር ታመጣና ታጠፋለህ፡፡ እንደገና በአመቱ ደግሞ ሌላ የሚጠፋ ገንዘብ ነው የሚፈለገው፡፡ ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ፉትቦል
ያለው ፋይዳ አናሳ ስለሆነ ነው በብሄራዊ ቡድን ደረጃ ውጤት አጥተን በዝረራ እየወጣን ያለነው፤ በዚሁ አጋጣሚ በጣም በፍጥነት
በፌዴሬሽኑ በኩል መስተካከል ያለበት ርምጃ ለክለቦቻችን የውጤት ድክመት ዋናው መንስኤ ክለቦች በየወሩ ለተጨዋቾች
የሚከፍሏቸው ገንዘብ ነው፤ ለሌለ እግር ኳስ 200 ሺህ ብር ለተጨዋቾች እየከፈሉ የመቀጠሉ ሂደት አንድ ቦታ ሊቆም ይገባዋል፤
እናም ይሄን ሂደት ለማስተካከል ፌዴሬሽኑ የመነሻ ሃሳብ በማዘጋጀት ከክለቦች፣ ከሚመለከታቸው ወገኖችና ከባለድርሻ አካላት
ጋር ተነጋግረን አሁን እየተኬደበት ያለውን አሰራር በፍጥነት እንቀይረዋለን፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P