Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በምርጥ ቡድናችንና ደጋፊዎቻችን ታጅበን የሊጉን ዋንጫ የምናነሳበት ዕድሉ አለን” ሀብታሙ ተከስተ

በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/

የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብን በፕሪምየር ሊጉ የውድድር ተሳትፎው በመጥቀምና በመሀል ሜዳውም ላይ ቡድኑ ጥሩ እንቅስቃሴ እንዲያሳይ ብሎም ደግሞ በውጤት ደረጃም ክለቡን በስኬታማነት እንዲጓዝ እያደረጉት ካሉት ተጨዋቾች መካከል አንዱ ወጣቱ ተጨዋች ሀብታሙ ተከስተ ነው፤ የፋሲል ከነማ ክለብ ውስጥ በሜዳ ላይ በሚያሳየው ጥሩ ብቃት ብዙዎቹ የስፖርት አፍቃሪዎች እያደነቁት ያለው ይኸው ተጨዋች በተለይ በፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ዘንድ “ጎላ” በሚል ተቀፅላ ስም እየጠሩት አድናቆታቸውን የሚገልፁለት ሲሆን ይህን ተጨዋች ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ በክለቡ ወቅታዊ አቋም ዙሪያና በኳስ ህይወቱ አጠር ያሉ ጥያቄዎችን አቅርቦለት ተጨዋቹ ምላሹን እንደሚከተለው ሰጥቶናል፡፡

ሊግ፡- የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ለአንተ ከፍተኛ አድናቆት አላቸው፤ አድናቆታቸውንም ሲገልፁልህ “ጎላ” እያሉም ነው፤ “ጎላ ምን ማለት ነው?
ሀብታሙ፡- ፋሲሎች ለእኔ ስለሚሰጡኝ አድናቆት በሚገባ አውቃለው፤ “ጎላ” የሚል ስምም አውጥተውልኝ ስለሚሰጡኝም አድናቆት ምስጋናዬ ከፍ ያለ እና ከፍተኛም ነው፡፡
“ጎላ” ማለት በእኛ ክልል አተረጓጎም ትልቅ ድስት እንደማለት ሲሆን የእኔ ጭንቅላት ትልቅ መሆኑን ተመልክተው ደጋፊዎቻችን ያወጡልኝ ስም ነውና ይህንን ተቀብዬ እና አድናቆታቸውንም አክብሬ ክለቤን በሚገባ በማገልገል ላይ ነው የምገኘው፡፡
ሊግ፡- የፋሲል ከነማን ወቅታዊ አቋም ብትገልፅልን? ጠንካራ እና ደካማ ጎኑስ ምንድን ነው?
ሀብታሙ፡- የፋሲል ከነማ ወቅታዊ አቋም ጥሩ ሲሆን ቡድናችን ኳስን ተቆጣጥሮ በመጫወትም በብዙዎች ዘንድ የሚታወቅና የሚደነቅም ነው፤ የሊጉ ተሳትፎአችን ላይ እኛ ያለን ጠንካራ ጎን ሁሌም ኳስን በሜዳችንም ሆነ ከሜዳችን ውጪ ስንጫወት ያሉንን ጨዋታዎች በጋራ እና እንደ ቡድን የምንንቀሳቀስ መሆናችን ነው፤ በደካማ ጎንነት የማነሳው ደግሞ በፊት የግብ አጨራረስ ችግር ነበረንና አሁን ይህን ችግር በመከላከያው ጨዋታ በርካታ ግቦች በማስቆጠር ቀርፈነዋልና፤ በዚህ በኩል ተሻሸለናል፡፡
ሊግ፡- መከላከያን በሰፊ ግብ ስላሸነፋችሁበት ጨዋታ ምን ትላለህ?
ሀብታሙ፡- የመከላከያ ክለብ ላይ አራት የሚደርስ ግብ አስቆጥረንበት ያሸነፍንበት ጨዋታ የእኛን ክለብ ጥንካሬ ያሳየ ነው፤ ምክንያቱም መከላከያ ምንም እንኳን የወራጅ ቀጠናው ላይ የሚገኝ ቡድን ቢሆንም ቡድኑ የሀገሪቱ ትልቅ ቡድን ነው፤ ከዛ ውጪ የያዛቸው የተጨዋቾች ስብስብም ጥሩ ስለሆነ እነሱን ማሸነፍ መቻላችን በጣም ነው ያስደሰተኝ፡፡
የመከላከያን ክለብ በእሁዱ ጨዋታ ለማሸነፍ የቻልነውም በኳስ ቁጥጥሩም ሆነ የግብ ዕድሎችን በመፍጠር እኛ የተሻልንም ስለነበርን ነውና ውጤቱ የሚገባን ሆኖም ነው ያገኘነው፡፡
ሊግ፡- የፋሲል ከነማ ክለብ ውጪ የእግር ኳስን የት የት ተጫወትክ፤ የፋሲል ከነማ ቆይታህንስ እንዴት ነው የምትገልፀው?
ሀብታሙ፡- ወደ ፋሲል ከነማ ክለብ ከመግባቴ በፊት የእግር ኳስን የተጫወትኩባቸው ክለቦች በከፍተኛ ሊግ እና በፕሪምየር ሊግ ደረጃ ለመቐለ 70 እንደርታ ክለብ ነው፤ ከዛ በፊት በነበረኝ የኳስ ህይወቴ ደግሞ በክለብ ደረጃ የመጀመሪያ ክለቤ ለነበረው ለዳሽን ቢራ ተጫወትኩና ብዙ ሳልቆይ ቡድኑ በውሰት ለሶስት ወራት ያህል ለደብረብርሃን ከተማ ሰጥቶኝ እዛ ተጫወትኩና የኳስ ህይወቴ በክለብ ደረጃ ይሄን ነው የሚመስለው፡፡
የፋሲል ከነማ ክለብ ውስጥ ስላለኝ ቆይታ ቡድኑን የተቀላቀልኩት ገና ዘንድሮ ቢሆንም እስካሁን ጥሩ ጊዜያትን እያሳለፍኩ ነው፤ ለቡድኑ በቋሚ ተሰላፊነት እየተጫወትኩ ባለሁበት የአሁን ሰዓት ላይም አሰልጣኜ ውበቱ አባተ የሚሰጠኝን የልምምድ አሰጣጥ በአግባቡ ተግባራዊ አድርጌም እየሰራው እና ቡድናችንም ለዋንጫው ፉክክክር እየተጫወተም ስለሆነ ባለኝ ቆይታዬ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን በፕሮጀክት ደረጃ ተጫውተህ አሳልፈሃል?
ሀብታሙ፡- አዎን፤ በፕሮጀክት ደረጃ ገና የታዳጊነት ዕድሜዬ ላይ ሆኜ ነው ተወልጄ ባደግኩበት የጎንደር ከተማ ውስጥ ኳስን የተጫወትኩት፤ ከዛ በፊትም በቡድን በቡድን ደረጃ ተከፋፍለን በቀበሌ እና በአካባቢ ደረጃ እንጫወትም ነበር፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስን በመጫወትህ ቤተሰብ ጋር የነበረው አመለካከት ምን ይመስል ነበር? ኳስ ተጨዋቹስ አንተ ብቻ ነህ… ስንት ወንድም እና እህትስ አለህ…
ሀብታሙ፡- ቤተሰቦቼ ከልጅነት ዕድሜዬ አንስቶ ኳስ መጫወቴ ላይ ምንም አይነት ተፅህኖ አያደርጉብኝም ነበር፤ የቤቱ ኳስ ተጨዋችም እኔ ብቻ ነኝ፤ እነሱ በኳሱ እንድገፋበት እያበረታቱኝም ነው ያደግኩት፡፡ እኛ ቤተሰብ ውስጥ ያሉት ወንድሞቼ ሶስት ሲሆኑ ሶስት እህቶችም አለኝ፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ተጨዋቾች ውስጥ የአንተ ተምሳሌትህ ተጨዋች ማን ነው?
ሀብታሙ፡- ከሀገር ውስጥ የዳሽን ቢራ ተጨዋች እያለው አስራት መገርሳ የእኛ ቡድን ተጨዋች ስለነበርና በችሎታውም ስለማደንቀው ሞዴሌ እሱ ነበር፤ ከባህር ማዶ ተጨዋቾች ደግሞ የማድነቀው ተጨዋች ሞድሪችን ነው፤ እሱን ነው ተምሳሌቴ ያደረግኩት፡፡
ሊግ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሜዳ ላይ በምታሳየው ጥሩ እንቅስቃሴ አድናቆቶችን እያተረፍክ ነው፤ እነዛን አድናቆቶች እንዴት ነው የምትቀበላቸው?
ሀብታሙ፡- የፋሲል ከነማ ተጨዋች ሆኜም ሆነ ከዛ በፊት ለመቐለ 70 እንደርታ ክለብ ስጫወት ሰዎች በሜዳ ላይ የሚሰጡኝን ማበረታታት እንደዚሁም ደግሞ አድናቆቶችን በሚገባ እቀበላለው፤ አከብራለውም፤ ለአድናቆታቸውም ከፍተኛ ምስጋናዬንም አቀርባለው፤ ያም ሆኖ ግን እኔ እነዚህ የሚሰጡኝን አድናቆቶች ሁሌ የማስባቸው ራሴን ቆልዬ እና ኳሱንም በቃ ጨርሻለው በጣም እችላለው ብዬ ሳይሆን ገና ብዙ ነገሮች እንደሚቀሩኝ ነው የምናገረው፤ ስለዚህም እነዚህ የሚሰጡኝ ማበረታቻዎች ለእኔ ብዙ ነገር እንደሚጠበቅብኝ ፍንጭ የሰጡኝ ስለሆነ ከዛ በላይ ሰርቼ አድናቂዎቼን የበለጠ ማስደሰት እፈልጋለው፡፡
ሀትሪክ፡- የእግር ኳስን መጫወት የጀመርከው በአሁኑ ቦታህ በስኪመር ስፍራ ነው?
ሀብታሙ፡- አይደለም፤ አጥቂ ነበርኩ፤ በኋላ ላይ ነው ከ13 ዓመት በታች በፕሮጀክት ደረጃ ስጫወት በአሰልጣኝ ተፅህኖ ውስጥ ወድቄ ስኪመር የሆንኩት፡፡
ሊግ፡- የእግር ኳስ ተጨዋችነትህን ጉዞ የት ማድረስ ትፈልጋለህ?
ሀብታሙ፡- የእግር ኳስ ተጨዋችነት ውስጥ የገባሁት እና በፕሪምየር ሊግ ደረጃም እየተጫወትኩ ያለሁት ገና በወጣትነት እድሜዬ ላይ ስለሆነ የኳስ ህይወቴን ማድረስ የምፈልገው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ነው፤ ባለፈው ጊዜ ለኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን መጣራቴ ምንም እንኳን በጉዳት ባልጫወትም በጣም ነው ደስ ያለኝና በቀጣይ ጊዜ ለሀገሬ ብሔራዊ ቡድን በመመረጥ መጫወትን እፈልጋለው፤ ከዛ ውጪም ወደ ባህር ማዶም በመሻገር ፕሮፌሽናል ተጨዋች መሆንም እፈልጋለውና ለዛ በርትቼ እሰራለው፡፡
ሊግ፡- ፋሲል ከነማ የሊግ ዋንጫውን ያነሳል?
ሀብታሙ፡- እኛማ የሊግ ዋንጫውን ለማንሳት ነው እየተጫወትን የምንገኘው፤ ለእዚህ ደግሞ መጀመሪያ ከፊታችን ያሉብንን ጨዋታዎች ማሸነፍ ይኖርብናል፤ የመሪው ክለብንም መቐለ ነጥብ መጣልም የምንጠብቅ ይሆናል፤ መቐለ ነጥቦችን የሚጥል ከሆነ በእርግጠኝነት ዋንጫውን የምናነሳው እኛ ነን የምንሆነው፡፡
ሊግ፡- የደቡብ ፖሊስ ጋር የነበራችሁን የሜዳችሁ ላይ ጨዋታ ነጥብ መጋራታችሁ ብዙዎቻችሁን አስቆጭቷል፤ ያን እንዴት ትመለከተዋለህ?
ሀብታሙ፡- አዎ፤ እንዴት አያስቆጨን ያን ጨዋታ አሸንፈን ቢሆን ኖሮ ከመሪው ክለብ መቐለ 70 እንደርታ ጋር ያለንን የነጥብ ልዩነት በጣም የምናጠበውም ይሆንልን ነበር፤ ግን ምን ታደርገዋለህ በኳስ የሚከሰት ነገር ሆነና በጨዋታው አቻ ወጣን ከዛ ቁጭት በኋላም ነው መከላከያን በሰፊ ግብ ልንረታው የቻልነው፡፡
ሊግ፡- የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ እና ደጋፊዎቻችሁን ስትገልፃቸው እንዴት ነው?
ሀብታሙ፡- የፋሲል ደጋፊዎች ሁሌም ጥንካሬያችን ናቸው፤ በሚሰጡን ምርጥ ድጋፍም እንደ 12ኛ ተጨዋች ስለምንቆጥራቸው በእዚህ አጋጣሚ ላመሰግናቸው እፈልጋለው፤ የቡድናችንን አሰልጣኝ በተመለከተ ውበቱ አባተ ጥሩ አሰልጣኝ ነው፤ የሰዎችን ችሎታ መቀየር እና ማሻሻል ይችላል፤ ለእኔም ብዙ ነገሮችን በማድረግ እና ጠንክሬም እንድሰራ በመምከር ትልቅ አስተዋፅኦን እያደረገልኝ ይገኛልና ሊመሰገን ይገባል፡፡
ሊግ፡- በመጨረሻ…..
ሀብታሙ፡- የፋሲል ከነማ እና የመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎች ለእኔ ኳሱ ላይ እያመጣሁት ላለው ለውጥ በድጋፋቸው እና በሚሰጡኝም ማበረታታት ጥሩ ነገርን አድርገውልኛልና በቅድሚያ እነሱን ማመስገን እፈልጋለው፤ ከእነሱ በመቀጠል ደግሞ ልጅ ሆኜ በፕሮጀክት ደረጃ ያሰለጠነኝን አሰልጣኝ እና ቤተሰቦቼን ማመስገን እፈልጋለው፤ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮችና ለቤተሰቦቼም መልካም የፋሲካ በዓል እንዲሆንላቸው እመኛለው፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P