Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“2016 የኢትዮጵያ ቡና ጊዜ ነው” በረከት አማረ (ኢት.ቡና)

ወጣቱ ግብ ጠባቂ በረከት አማረ የቡናማዎቹን በር መጠበቅ ከጀመረ አራተኛ አመቱን ይዟል…. ዘንድሮ ግን በወጣቶች ለተሞላው ኢትዮጵያ ቡና ሲኒየርና አምበል ሆኖ ቡድኑን የሜዳ ላይ አሰልጣኝ ሆኖ እየመራ ይገኛል…

ዘንድሮ አዲሱን አሰልጣኝ ኮቫዞቪች ኒኮላ በዋና አሰልጣኝነት የሾሙት ኢትዮጵያ ቡናዎች ጥረታቸው እንደሚሳካም ይናገራል… ከሊጉ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር  ቆይታ ያደረገው በረከት አማረ ስለ ኢትዮጵያ ቡና የዘንድሮ እቅድ፣ ስለዝግጅቱ፣ ስለ አዲሱ ሰርቪያዊ አሰልጣኝ፣ ስለ ኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎችና ሌሎች ጥያቄዎች የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል……

 

ሊግ:- አመሰግናለሁ ለመልካም ፍቃድህ …ወጣቱ በረከት  ለኢትዮጵያ ቡና  ሲኒየርና አምበል መሆኑ ምን ስሜት ይፈጥራል…..?

በረከት:- እኔም አመሰግናለሁ… እንዳልከው ሲኒየርና አምበል መሆን ትልቅ ትርጉም አለው … እንደ ሲኒየር ቡድኑን ለመምራት ይጠቅማል፡፡ ቡድናችን ውስጥ አብዛኞቹ ተጨዋቾች ወጣቶች እንደመሆናቸው እነሱን ለመምራት ይጠቅማል…. ሲኒየር ሆኖ አምበል መሆን ትልቅ ሃላፊነት ነው… ኢትዮጵያ ቡና ትልቅ ክለብ ነው የዚህ ቡድን አምበል መሆን ሃላፊነቱን ትልቅ ያደርገዋል…

እንደሲኒየርም ተጨዋቾቹን ወደ  አንድ ለማምጣት ትልቅ እድል አለው …እንደ አምበልነትም ሃላፊነቱ ቢከብድም እወጣዋለሁ ብዬ አስባለሁ….

ሊግ:–  መልበሻ ክፍሉ ሰላም…ስብስቡ አሪፍ ነው ማለት ይቻላል..?

በረከት:- አዎ …ስብስቡም ሆነ እያደረግን ያለው ዝግጅት አሪፍ ነው፡፡ በጥሩ አንድነትና መናበብ ስራችንን እየሰራን ነው፡፡ መልበሻ ቤቱም ሰላም ነው… አዲሱ አሰልጣኛችን ለሊጉ ተፎካካሪነት የሚያበቃንን ዝግጅትና ልምምድ እየሰጠን በመሆኑ ውጤታማ እንደምንሆን ተስፋ አደርጋለሁ..

ሊግ:– አዲሱ ሰርቪያዊው አሰልጣኝ ኮቫዞቪች ኒኮላ እንዴት አገኛችሁት…?

በረከት:– አሰልጣኛችን ጎበዝ ነው፡፡ ያለንን አውጥተን እንድንሰራ እያደረገ ነው፡፡ በወዳጅነት ጨዋታ በጥሩ ሁኔታ እያዘጋጀን ይገኛል፡፡ እስከ ሊጉ ጅማሮ ድረስ አሪፍ ነገር ይኖረናል ብለን እናስባለን፡፡ አምና ከነበረው በቡድናችን የተወሰነ ነው የተጨመረውና በመዋሃድ ደረጃ ቡድኑ የተዋሃደ ነው፡፡ አብሮ የነበረ መሆኑ ለአሰልጣኙ ነገሮችን ያቀለለለት ይመስለኛል..

ሊግ:– የዝግጅት ጨዋታ አድርጋችኋል እንዴት አገኛችሁት..?

በረከት:– አራት ከሚጠጉ የፕሪሚየር ሊግ ቡድኖችን ጨምሮ እስከ ሻሸመኔ ከተማ የሲቲ ካፑ ጨዋታ ድረስ ወደ 9 የሚጠጉ ጨዋታዎችን አድርገናል… ሁሉንም ጨዋታዎችን አሸንፈናል፡፡ ጥሩ ውጤት እየተመዘገበ ነው። ያው መሸነፍ ሳይኖር እያሸነፉ መዘጋጀት ያስደስታል።

የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦችን ማሸነፋችን በራሱ ለፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ይረዳናል በዚህም ደስ ብሎናል።

ሊግ:– ወደ አራት አመት ቆየህ …ለውጥህ  ምን ይመሰላል..?

በረከት:- ጥሩም መጥፎንም ነገር አሳልፌያለሁ፡፡ ያም ሆኖ በቆይታዬ ደስተኛ ነኝ፡፡ ቆይታዬ በዋንጫ ባለመታጀቡ ቅር ያሰኛል… የተሻለ ነገር ሰርቶም ቢሆን ዋናው ዋንጫ ነው ያም ሆኖ አራት አመት ሙሉ ተለውጬ ልምድ አግኝቼ ለዛሬው እኔነቴ በቅቻለሁ ማለት ይቻላል… ውጣ ውረዱ ባይጠፋም በቀጣይ እንደ ክለብም ሆነ እንደ ግል ለውጥ ይኖረናል ብዬ አምናለሁ፡፡

ሊግ:-  አምና ውጤታማ እንዳትሆኑ ያደረጋችሁ ምን ይሆን..?

በረከት:- አምናም ችግር ነበር ብዬ መናገር አልችልም፡፡ ኳስ ላይ የሚገጥመው ነገር ነው የገጠመን… ስብስቡ ምርጥ ቢሆንም እንደ ሀገር ከዋክብት የተባሉትን ብትይዝም ሜዳ ስትገባ የምትገባው እኩል 11 እና 11 ሆነህ በመሆኑ አንዳንዴ ላይሳካ ይችላል… የአምናው ቡድን አዲስም ስለነበር ወደ 15 ተጨዋቾች አካባቢ አዲስ ስለነበር ለመዋሃድ ተቸግረን ነበር፡፡ እሱ ነው የጎዳን አሁን ግን ከአምናው ስብስብ የተወሰነ ነውና የተጨመረው በመዋሃድ ደረጃ የተሻለ እንሆናለን ብዬ አስባለሁ… ከእግዚአብሄር ጋርም ከአምናው የተሻለ ውጤት ይመዘገባል ብዬ አምናለሁ።

ሊግ:- አምና ውጤት ስላጣችሁበት የተበሳጨህበት ጨዋታ የትኛው ነው..?

በረከት:- አምናማ አብዛኞቹ ጨዋታዎች እየመራን የተሸነፍንባቸው ወይም አቻ የወጣንባቸው ብዙ ናቸው፡፡ እየመራን የተሸነፍንባቸው ጨዋታዎች ያበሳጫሉ፡፡ ማሸነፍም የነበረብን ናቸው በቁጥር ጨዋታውን ባልገልጽም እየመራን የተሸነፍንባቸው ወይም አቻ የወጣንባቸው ነጥብ ማግኘት የነበረብን በመሆኑ ተቆጭተናል።

ሊግ:- በረከት አማረ ኳስ ተጨዋች ባይሆን ምን ሊሆን ይችል ነበር..?

በረከት:– /ሳቅ በሳቅ/ በኳስ ተጨዋችነት ህይወቴ ደስተኛ ነኝ ….የህይወት አጋጣሚ ሆኖ ተጨዋች ባልሆን ግን በርግጠኝነት ሞባይል መነካካት ላይ ጎበዝ ነኝ ብዬ አስብ ነበርና የኤሌክትሮኒክስ ተቋም ኖሮኝ በዚያ ሙያ ላይ እሰማራ እንደነበር እገምታለሁ፡፡

ሊግ:- ኳስ ተጨዋች ወይም የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ባለሙያ.. የአሁኑ የተጨዋችነት ምርጫህ መነሻስ ምክንያት ነው..?

በረከት:-  መነሻዬ ከፕሮጀክት ነው… አዲግራት ላይ በመስቀል በአል ምክንያት የሚደረግ የእግር ኳስ

ውድድር አለና ያኔ ዋንጫ ስናሸንፍ የነበረው ድባብና ደስታ ውስጤ ላይ በፈጠረው ተጽዕኖ በእግር ኳሱ ገፍቼ እንድሄድ አድርጎኛል…. የጀመርኩትም ያኔ ነበርና በእሱ ተጽዕኖ ውስጥ ሆኜ ነው የጀመርኩት ዋናው ምክንያት ያ ይመስለኛል…

ሊግ:-  የሲቲ ካፑንና  የፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ እንጠብቅ..?

በረከት:- ሲቲ ካፑን በድል ጀምረነዋል.. ሻሸመኔን አሸንፈናል፡፡ ከባህር ዳር ጋር ደግሞ አቻ ወጥተናል።

በዚህም እየተማርን ስለምንጓዝ የአመቱ የሊግ ውድድር ሲጀመር ጥሩ ሆነን ስለምንቀርብ ከእግዚአብሄር ጋር እናሸንፋለን ብዬ አምናለሁ… በሊጉ ደረጃ ደግሞ የተሰባሰበው በሙሉ አቅም ያለው ስለሆነ የተሻለ ተፎካካሪ በመሆን ከአምናው የተሻለ ጊዜ ይኖረናል ብዬ አምናለሁ .. 2016 የኢትዮጵያ ቡና ጊዜ ነው….

ሊግ:-  ለበረከት ከውጪና  ከሃገር ውጪ ምርጡ በረኛ ማነው ..?

በረከት:- ለኔ ከውጪ ምርጡ በረኛ የማን.ሲቲው ኤደርሰን ነው…..በእግር መጫወት የሚወስደው ሃላፊነትና የሚያድናቸው ኳሶች  ምርጥ ናቸው…ተምሬበታለሁ…

ከሀገር ውስጥ ብዙ ናቸው፡፡ ለኔ አርአያ የሆኑትን አንዱን ጠርቼ አንዱን መተው አልፈልግም። አምና በነበረው የውድድር አመት የሃድያ ሆሳዕናው ግብ ጠባቂ ፔፔ ሰይዶ እና የኢትዮጵያ መድን ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑራ ምርጥ ነበሩ ጥሩ ጊዜም አሳልፈዋል፡፡

ሊግ:– የማን ደጋፊ ነህ..?

በረከት:– የውጪ ኳስ አያለሁ… የአርሰናል ደጋፊ ነኝ፡፡ አርሴናል ጥሩ አቋም ላይ ይገኛል…ጥሩ ጊዜም እያሳለፈ ነው፡፡ በቀጣይ ምርጥ ጊዜ እንደሚያሳየን ርግጠኛ ነኝ…

ሊግ:– የመጨረሻ ጥያቄ እናድርገውና ለኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች የምትለው ነገር አለ…?

በረከት:- ለደጋፊዎቻችን ማለት የምችለው ነገር ያንስብኛል… ምርጥ ደጋፊ ባለቤት ነን የሚገርም ደጋፊ አለን ብርድ ይሁን ሙቀት.. ይመች አይመች..ደጋፊዎቻችን ከጎናችን ናቸው…በሲቲ ካፑ እየመጡ እየደገፉን ነው በዚህም ደስተኛ ነኝ..ሁሌ ነው የማመስግናቸው… ለነሱ ክብርና ፍቅር አለኝ ሁሌም አመሰግናቸዋለሁ.. በቀጣይም  እንደ ሁሌው  ከጎናችን እንደሚሆኑ ተስፋ አደርጋለሁ  በቡድናችን አባላት ስም ደጋፊዎቻችንን ደጋግመን እናመሰግናለን።

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

ትኩስ ዜናዎች

P