Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በባለፈው ላዘኑት ደጋፊዎቻችን ባህር ዳር ከተማን አሸንፈን የገና ስጦታ እናበረክትላቸዋለን”አምሳሉ ጥላሁን (ሳኛ) ፋሲል ከነማ

በመሸሻ ወልዴ /GBOYS/

ፋሲል ከነማ ከሰበታ ከተማ ባደረገው ያላፈው ሳምንት ጨዋታ የብዙዎችን የእግር ኳስ አፍቃሪዎች የኳስ ስሜት የገዛ ሲሆን በእዚህም ጥሩ ፉክክር በተደረገበት ፍልሚያ ሁለቱ ቡድኖች 3ለ3 ሊለያዩ ችለዋል፡፡ ለፋሲል ከነማ ሶስቱን ግቦች ማውሊ፣ ሽመክት ጉግሳ እና ሙጂብ ቃሲም ሲያስቆጥሩ ለሰበታ ከተማ ደግሞ ፍፁም ገ/ማሪያም ሁለቱን እና አስቻለው ግርማ ደግሞ የመጨረሻዋን አቻ ያደረገቻቸውን አንዷን ግብ ሊያስቆጥር ችሏል፡፡
ፋሲል ከነማ ሰበታን በተፋለመበት ጨዋታ የያዘውን የመሪነት ውጤት ለማስጠበቅ ባለመቻሉ ነጥብ ተጋርቶ የወጣ ሲሆን በተገኘው ውጤትም የቡድኑ ተጨዋቾችንም ሆኑ ደጋፊዎች ሲያዝኑ ተመልክተናል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ሰበታ ከነማዎች ፍፁም ሊያምኑ ባልቻሉበት ሁኔታ ነጥብ በመጋራታቸው ሲደሰቱ ተመልክተናል፡፡
የፋሲል ከነማ ክለብ ከሰበታ ከተማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ነጥብ ስለመጋራቱና ስለቡድኑ ቀጣይ የሊግ ፍልሚያ እንደዚሁም ዘንድሮ ሊያመጡት ስላሰቡት ውጤት ካፒቴኑን አምሳሉ ጥላሁንን አናግረን የሚከተለውን ምላሽ ሠጥቶናል፡፡
ሊግ፡- ፋሲል ከነማ ከሰበታ ከተማ ያደረገውን ጨዋታ በተጨማሪ አራት ደቂቃዎች ሁለት ግቦች ተቆጥሮበት አቻ ተለያይቷል፤ ጨዋታው ምን መልክ ነበረው?
አምሳሉ፡- የፋሲል ከነማና የሰበታ ከተማ የእሁዱ ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ የእለቱ አልቢትሮች ግጥሚያውን መቆጣጠር ተስኗቸው እና እንዳቃታቸውም ብንመለከትም የሁለተኛው አጋማሽ ላይ ግን ሁሉንም ነገር ረስተንና የተሻለ ነገርንም ይዘን ገብተን ጥሩ ልንጫወት ችለናል፤ ከዛ ውጪም በእዚሁ ክፍለ ጊዜ እስከመጨረሻው 90 ደቂቃ ድረስም ተጋጣሚያችንን በኳስ ቁጥጥር በመብለጥ 3ለ1 እስከመምራትም ደረጃ ልንደርስ ችለናል፤ በመጨረሻዎቹ አራት የጭማሪ ደቂቃዎች ላይ ግን ፈፅሞ በማይታመን እና ባላሰብነው ሁኔታ በእግር ኳስ ላይ በሚፈጠር ድንገተኛ ክስተት ሁለት ጎሎች ተቆጥሮብን ግጥሚያውን በአቻ ውጤት ልናጠናቀቅ ችለናል፡፡ የፋሲል ከነማ እና የሰበታ ከተማን የእሁዱን ሌላኛው የሜዳ ላይ ትዕይንት ስንመለከት ግጥሚያው ጎንደር ላይ የሚካሄድ ይመስል ነበር፤ ደስ የሚል ድባብም በአዲስ አበባ ስታድየም ላይ ታይቷል፤ እኛም ያለንን አቅም ተጠቅመን ነው ባይሳካልንም ከጨዋታው ሶስት ነጥብ ይዘን ለመውጣትም ወደሜዳ መጥተን የነበረው፡፡
ሊግ፡- የእሁዱ ጨዋታ እንደተጠናቀቀና ልክ ደጋፊዎቻችሁን ስትመለከት በተገኘው ውጤት ምን አይነት ስሜት ነው በውስጥህ ሊፈጠርብህ የቻለው?
አምሳሉ፡- ሰበታ ከተማን በተፋለምንበት ጨዋታ የእኛ ፍላጎት የነበረው ጨዋታውን አሸንፈን ከደጋፊዎቻችን ጋር ደስታችንን ለመግለፅ /ሴለብሬት/ ለማድረግ እና ተቃቅፈንም ለመጨፈር ነበር፤ ያም ሆኖ ግን ይሄን ለማድረግ አልቻልንም፤ በፕሪምየር ሊጉ እንዲህ ያሉ ድንገተኛ እና ፈፅሞ ያልታሰቡ የነጥብ መጣሎች በእኛ ሀገር የፕሪምየር ሊግ ደረጃ ሲከሰት የመጀመሪያው ይመስለኛል፤ ይህ ስሜትን ሊነካ ቢችልም እንደራሴ አመለካከት ግን ሊጉ አሁን ላይ ገና ጅማሬ ላይ ስለሆነ ባመጣነው ውጤት ተበሳጭተን ራሳችንን የምንጎዳበት አንዳችም ነገር አይኖርም፤ ዓለም ላይ እንዲህ ያሉ የነጥብ መጣሎች ብዙ ጊዜ ይከሰታሉና አሁን ላይ እኛ ካለፈው ጨዋታ ስህተቶቻችን በመማር ቡድናችንን ለሻምፒዮናነት ለማብቃት ከፍተኛ ጥረትን እናደርጋለን፡፡
ሊግ፡- ፋሲል ከነማን ከሰበታ ከተማ የእሁዱ ጨዋታ ላይ የሚለየው ነገር ነበር?
አምሳሉ፡- አዎን፤ ይሄ የሆነውም በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ነበር፤ በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለታችንም አንድ አይነትና ተመሳሳይ የሆነ ጨዋታን ነው ይዘን ወደ ሜዳ ገብተን የነበርነው፡፡ ፉክክሩም ጥሩ የኳስ ፍሰት ያለውና አዝናኝም ነበር፡፡ በሜዳ ውስጥ አጠቃላይ እግር ኳሱን ስመለከተው በሊጉ ላይ ከታዩት ጨዋታዎች ይሄ ምርጡም ነበር ብዬ ነው የማስበው፡፡ ከእረፍት በኋላ ግን የእኛ ቡድን ባለው ጥሩ አቋም ሙሉ ለሙሉ እነሱን ተጭኖ እና ዶሚኔት አድርጎ ስለተጫወተ በዛ ከተጋጣሚው ተሽሎ ታይቷል፡፡
ሊግ፡- ፋሲል ከነማ ወደ ባህር ዳር ተጉዞ የደርቢ ፍልሚያውን ያደርጋል፤ ስለዚሁ ጨዋታ ምን ማለት ይቻላል?
አምሳሉ፡- ባህር ዳርን የምንፋለምበት የዛሬው ጨዋታ እኛም ሆንን እነሱ በአንድ ክልል ውስጥ የምንኖር ከመሆናችን አንፃር የወንድማማቾች ጨዋታን ነው የምናደርገው፤ በኳስ ጨዋታም ቋንቋ ስገልፅልህ የደርቢ ፍልሚያንም ነው የምናከናውነው፤ በእዚህ ጨዋታ እነሡ በእኛ እኛም በእነሱ መሸነፍን ፈፅሞ አንፈልግምና ዛሬ በሁለታችን መካከል ጥሩ ጨዋታ ይታያል፡፡
ሊግ፡- በደርቢው ጨዋታ ማን ያሸንፋል?
አምሳሉ፡- ፋሲል ከነማ እሁድ ዕለት ከሰበታ ከተማ ባደረገው ጨዋታ የጣለው ነጥብ ደጋፊዎቻችንን ክፉኛ አሳዝኗል፡፡ ስለዚህም የዛሬውን የደርቢ ጨዋታ በማሸነፍ ለእነሱ የገና ስጦታን ልናበረክትላቸው ተዘጋጅተናልና ይሄን እውን እናደርገዋለን፡፡
ሊግ፡- የገና በአልን ብዙ ጊዜ የምታከብረው የትና በምን መልኩ ነው?
አምሳሉ፡- የገና በአልን ለብዙ ጊዜያቶች ያከበርኩት ከቤተሰቦቼ ጋር ነበር፤ ካለፉት ሶስት አመታቶች ወዲህ ግን በጣም የሚገርምህ በፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎቻችንን ላይ ተጠምጄ ስለቆየው በተለያዩ የክልል ከተሞች ላይ ነው በአሉን ለማክበር የቻልኩት፡፡ ከዚህ በፊት ለምሳሌ አምና መቀሌ ላይ ነበር ያከበርኩት፤ ዘንድሮ ደግሞ ወላይታ ዲቻ ላይ ነው የማከብረውና በዚህ መልኩ ነው በዓሉን ሳሳልፍ የነበርኩት፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን መቐለ 70 እንደርታ እና ወልዋሎ አዲግራት በ10 ነጥብ ይመሩታል፤ እናንተ በ8 ነጥብ ትከተላላችሁ፤ በሊጉ ተሳትፎ የእናንተ ዋናው እቅድ ምንድን ነው?
አምሳሉ፡- ፋሲል ከነማ በሊጉ ተሳትፎው ምንም አይነት ጥርጥር የለውም፤ የእኛ ዋናው ዓላማና እቅድ ዋንጫውን ማንሳት ነው፡፡
ሊግ፡- የሊጉን ዋንጫ ምንአልባት እንዳታነሱ በስጋት መልኩ የምታነሱት ነገር አለ?
አምሳሉ፡- አዎን፤ ይሄም የተጨዋቾች ጉዳት ነው፤ እሱ ሊጎዳን ይችላል፤ አሁን ላይ በሊጉ አራት የሚደርሱ ተጨዋቾቻችን በጉዳት ላይ ነው የሚገኙት፤ እየተተካካንም ነው በመጫወት ላይ የምንገኘው፤ ስለዚህ ይሄ ችግር ቶሎ ሊቀረፍ ይገባል፡፡ ይሄ የተጨዋቾች ጉዳት ባይኖርብን ኖሮ ሊጉን መሪዎቹ ቡድኖች እንደያዙት 10 ነጥብ አይደለም ከዛም በላይ ነጥብ ይዘን ውድድሩን እንመራውም ነበር፡፡
ሊግ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ከጅማሬው እንዴት ተመለከትከው?
አምሳሉ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአሁን ሰአት እየተካሄደ የሚገኘው በብዙዎች ዘንድ ከዚህ በፊት እንደሚብጠለጠለውና እንደሚፈራው አይደለም፤ በየክልሉ እግር ኳሱ የሠላም መገለጫ እንደሆነም እየታየ ይገኛል፤ ከእኛ ቡድን ስንነሳ ወደተለያየ ክልል ለጨዋታ በሄድንበት ሰዓት በጥሩ ሁኔታ ተቀብለውን ሸኝተውናልና ይሄ ስፖርታዊ ጨዋነት በቀጣይነትም ይቀጥላል

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P