Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

“በተወራልን ልክ ራሳችንን አላገኘነውም” “ጊዜው ስላልረፈደ ዋንጫውን የማንሳት ዕድሉ አለን” ሳሙኤል ሳሊሶ /መቻል/

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ11ኛው ሳምንት ጨዋታ በቀድሞ ስሙ መጠራት የጀመረው መቻል ተጋጣሚውን ሐዋሳ ከተማን በሳሙሄል ሳሊሶ እና በረከት ደስታ ሁለት ግቦች 2-0 በማሸነፍ ከተደጋጋሚ ነጥብ መጣል በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል።

በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ታሪክ ትልቅ ስምና ዝናን በማትረፍ በስፖርቱ አፍቃሪ ዘንድ የሚታወቀው መቻል በሊግ ውድድር  ከፍተኛ የአሸናፊነት ግምት ዘንድሮ የተሰጠው ቢሆንም በተደጋጋሚ ጊዜ ነጥብ መጣሉ ደግሞ ጥያቄን ቢያስነሳም የክለቡ ተጨዋቾች ከሆኑት መካከል የኮሪደር ስፍራው አጥቂ ሳሙሄል ሳሊሶ “የሊጉ ውድድር ገና በርካታ ጨዋታዎች የሚቀሩት ነው፤ በእዚህ ዓመት ለእኛ የተሰጠንን ግምት ለማሳካት ከፍተኛ ጥረትን እናደርጋለን፤ ያ ባይሳካ እንኳን በሊጉ ተሳትፎአችን የደረጃ ተፎካካሪ ሆነን የውድድር ዘመኑን እናጠናቅቃለን” በማለት ከሊግ ስፖርቱ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ /G.BOYS/ ጋር በነበረው ቆይታ ምላሹን ሰጥቷል።

ሊግ ስፖርት ከመቻሉ ሳሙኤል ሳሊሶ ጋር በተለያዩ ጥያቄዎች ዙሪያ የነበራት አጠቃላይ ቆይታም እንደሚከተለው ቀርቧል።

ሊግ፦ በቅድሚያ ለቃለ-ምልልሱ ፈቃደኛ ስለሆንክልን ከልብ አድርገን እናመሰግንሃለን?

ሳሙሄል፦ እኔም የጋዜጣችሁ እንግዳ አድርጋችሁ ስላቀረባችሁኝ ከልብ አድርጌ አመሰግናችኋለሁ።

ሊግ፦ በሳምንቱ አጋማሽ ሐዋሳ ከተማን ማሸነፍ ችላችኋል፤ አንተም ጎል ለማስቆጠር ችለሃል፤ ስለ ጨዋታው ምን ትላለህ?

ሳሙኤል፦ ግጥሚያውን ብዙዎች እንደተመለከቱት እኛ የኳስ ብልጫ ነበረን። ብዙ የግብ አጋጣሚዎችንም አግኝተን ሳንጠቀምበት ቀርተናል። ያ ሊያጋጥመን የቻለውም ካለብን ጭንቀትና ውጤቱን ለመቀየርም ከመጓጓት ጭምር ነው። ያም ሆኖ ግን የዕለቱን ጨዋታ ድሉ ለእኛ በሚገባን መልኩ አሸንፈን ስለወጣንበት በጣም ደስ ብሎኛል።

ሊግ፦ በጨዋታው የድል ጎልም ለማስቆጠር ችለሃልና በቀጣይነትም ከአንተ ሌሎች ጎሎች ይጠበቁ?

ሳሙኤል፦ አዎን፤ አሁን ሁለት ጎል አለኝ። እንደ መስመር አጥቂነቴ ከእኔ የሚጠበቅ ነገር ስላለ ሌሎች ተጨማሪ ጎሎች እንደሚኖሩኝ እርግጠኛ ነኝ።

ሊግ፦ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፈጣን ከሚባሉ ተጨዋቾች መካከል አንዱ አንተ ነህ፤ ይህ ፍጥነት እንዴት ሊመጣ ቻለ?

ሳሙኤል፦ /እንደ መሳቅ ካለ በኋላ/ እንደውም ይሄ ፍጥነት አሁን ላይ ቀነሰ እንጂ በተፈጥሮ የመጣ ነው።

ሊግ፦ በውድድር ዘመኑ እስካሁን የ11ሳምንታት የጨዋታ ቆይታን አድርጋችኋል፤ እንደ ቡድን ያላችሁ ጥንካሬና ክፍተት ጎን ምንድን ነው፤ ባሰባችሁት መልኩስ ነው እየተጓዛችሁ ያላችሁት?

ሳሙኤል፦ በውጤት ደረጃ ካየኸው የምንፈልገውን ነገር አግኝተናል ብለን አናምንም፤ ነገር ግን በእንቅስቃሴ ደረጃ ከተመለከትከን ቡድናችን ነጥብ በጣለባቸውም ሆነ ባገኘባቸው ጨዋታዎች ላይ ከዕለት ወደ ዕለት በመሻሻል ላይና ጥሩ ነገሮችንም በየጨዋታው ላይ እያሳየን ነው የምንገኘው።  ይህም የቡድኑን የቀጣይ ጊዜ ጉዞ ጥሩ እንደሚሆንልንም እያስመለከተን ነው የሚገኘው።

ሊግ፦ እስካሁን ባሉት ጨዋታዎች መቻልን በተጠበቀው ልክ ውጤትን  እንዳያገኝ አስችሎታል የምትለው ነገር ምንድን ነው?

ሳሙኤል፦ አንደኛው ነገር ቡድኑ በአዲስ የተገነባ መሆኑ ነው፤ ከ20 የሚበልጡ  ተጨዋቾችም ዘንድሮ የፈረሙ መሆናቸውና ውጤት ለማምጣትም እነዚህን ተጨዋቾች ማቀናጀት የግድ ስለሚለን  ይህ ሁኔታ ጎድቶናል። ሌላው ሁኔታ ደግሞ ክለቦች ከእኛ ጋር ሲጫወቱ በሜዳ ላይ ይዘውት የሚመጡት የጨዋታ አቀራረብ እኛን እያስቸገረን  ነው። አብዛኛው ቡድን ለመከላከል መጥቶ ነው በእኛ ላይ በሆነ አጋጣሚ ጎል አግብተው ነጥብ ሲያስጥሉን የሚታየው፤ አሁን ላይ ግን ወደ መቀናጀቱ እየመጣን ስለሆነና የምንፈልገውንም የጨዋታ ሪትም እያገኘን ስለሆነ በሁሉም ነገር ማለትም በውጤት ደረጃም ሆነ በእንቅስቃሴ ደረጃ  ተሻሽለን እንቀርባለን።

ሊግ፦ ከያዛችሁት የተጨዋቾች ስብስብ በመነሳት የእዚህ ዓመትን  የሊግ ዋንጫ  ዘንድሮ ሊያነሱ ከሚችሉ ቡድኖች መካከል እናንተንም የስፖርቱ  አፍቃሪው በዋናነት ገምቷችኋል፤ እናንተም የራሳችሁን ግምት ልክ እንደ ስፖርቱ አፍቃሪው ነው ያስቀመጣችሁት?

ሳሙኤል፦ አዎን በትክክል፤ ከውድድሩ መክፈቻ በፊት ጀምሮ ነው ሰው እንደሚመለከተው እና እንደሚያስበው ሁሉ እኛም ራሳችንን ስለምንመለከት በእዚሁ ጉዳይ ላይ ማን ምን እንደሆነ ሁሉ ስንነጋገር የነበርነው።  በውድድሩ ላይም እኛ ራሳችንን በጠበቅነው እና ባወራነው ልክ ስላላገኘነው በስነ ልቦና ደረጃ ወረድ ብለን የነበረ ቢሆንም ከእዚህ በኋላ ውጤትን ወደመቀየር ስለምንመጣ በጥሩ ሁኔታ ላይ መገኘታችን የማይቀር ነው።

ሊግ፦ በመጨረሻ  ከሚመዘገብ ስኬታማ ውጤት  ጋር አያይዘህ  አሁን ላይ  ጊዜው ረፍዶብናል ብለህ ታስባለህ?

ሳሙኤል፦ ጊዜው አልረፈደም፤ አሁንም ዋንጫውን የማንሳት ዕድሉ አለን። የ2010ሩን ውድድር ለምሳሌ ተመልከት፤ ጅማ አባጅፋር በመጀመሪያው ዙር ላይ ጥሩ ውጤት አልነበረውም፤ በኋላ ላይ ግን ብዙ ነገሮችን ቀይሮ በመምጣት የውድድሩ ሻምፒዮና ሊሆን ችሏል። ከእዚህ በመነሳት እኛም ይህን የማናሳካበት ምክንያት የለም። ይህ ባይሳካ እንኳን አሁን ከምንገኝበት ደረጃ ተነስተንም የሊጉ የደረጃ ተፎካካሪ ሆነን የውድድር ዘመኑን እናጠናቅቃለን።

ሊግ፦ በእስካሁኑ የሊግ ጨዋታዎቻችሁ ለእናንተ አስቆጪው ግጥሚያ የቱ ነው? የተደሰታችሁበትስ ጨዋታ?

ሳሙኤል፦ በቁጭት ደረጃ የማነሳው  አብዛኛውን ነጥብ እናገኝባችኋለን ብለን አስበን ነጥብ የጣልንባቸውን ግጥሚያዎች ነው። ምክንያቱም ከእስካሁኑ ጨዋታዎቻችን መካከል ከትልልቆቹ ቡድኖች ጋር ተጫውተን ያሸነፍንበትና ነጥብ የተጋራንበት ግጥሚያ በመኖሩ ነው። በጣም ጣፋጭና ተደስቼበታለው ብዬ የምናገረው ፍልሚያ ደግሞ  ውጤት ያገኘንባቸውን ጨዋታዎች ቢሆንም በዋናነት የምጠቅሰው ፍልሚያ ባህርዳር ከተማ ላይ ፋሲል ከነማን ያሸነፍንበት ጨዋታና ሲቀጥል ደግሞ ካለብን ውጥረት አኳያ የምንገኝበትን ሁኔታ ሊቀይርልንም የሚችል በመሆኑ ሐዋሳ ከተማን  በድሬዳዋ ስታዲየም ድል ያደረግንበትን ጨዋታ እጠቅሰዋለሁ።

ሊግ፦ በሊግ ውድድሩ መቻል ከያዛቸው የተጨዋቾች ስብስብ አኳያ  በውጤት ደረጃ  ብዙ ተጠብቆ እስካሁን በተፈለገው መልኩ እየተጓዘ አይደለም፤ ይህን ያወቁት የክለቡ ከፍተኛ አመራሮች በውጤት ማጣታችሁ ምን እያሏችሁ ነው? ጫናዎችስ አለባችሁ?

ሳሙኤል፦ ክለባችን እነዚህን ጥሩ ጥሩ ተጨዋቾች ዘንድሮ ሲያመጣ ውጤትን ፈልጎ እንደሆነ የሚያስታውቅ ነው፤  ያም ሆኖ ግን  የእኛ ቡድን ውጤትን  ባጣበት የአሁን ሰዓት ላይ እንደእዚህ አይነት እንደ እኛ አይነት ምርጥ አመራሮች በህይወትህ ሊያጋጥሙህ አይችልም፤  ልታያቸውም አትችልም። የእኛ አመራሮች ሁሌም ከጎናችን ናቸው፤ በእያንዳንዱም የጨዋታ እንቅስቃሴዎቻችንም የሚከታተሉን ናቸው፤ ያበረታቱናል፤ ጫና ውስጥ እንዳንገባና ቡድኑን የሚያነሳሳ ነገር እንድናከናውንም ያደርጉናል፤  ኳስ ነው አይዟችሁ ከጎናችሁ አለንም ይሉናልና ለእነሱ ከፍተኛ ምስጋና ይገባችኋል።

ሊግ፦ በእስካሁኑ ጨዋታ የሊጉን ጉዞ በምን መልኩ አገኘከው?

ሳሙኤል፦ ፉክክሩ አሪፍ ነው፤ ያም ሆኖ ግን ብዙ ነገሮችን ከሜዳ አኳያ ማየትን እፈልጋለሁ። አብዛኛው የመጫወቻ ሜዳዎች ጥሩ ስላልሆኑ ሁሉንም ቡድን በአቅምም በሌላ ነገርም እኩልም አድርጓቸዋል። የተመዘገቡት ነጥቦች የሚገልፁትም ያንኑ ነው። ከላይ ያሉት ቡድኖች በነጥብ ተቀራራቢ ናቸው። መሀል ላይ ያሉትም ወደላይ መድረስ ይችላሉ። ጥሩ ፉክክር እየተደረገ ቢሆንም ሜዳዎች ላይ ቢታሰብ ግን ጥሩ ነው።

ሊግ፦ የእዚህ ዓመቱ ፉክክር እስከ መጨረሻው እንደ ዓምናው ይጓዝ ይመስልሃል?

ሳሙኤል፦ አዎን፤ ግምቴም ነው።

ሊግ፦ የፕሪምየር ሊጉ ውድድር አሁን ላይ በዓለም ዋንጫው ሽፋን ምክንያት የዲ ኤስ ቲቪ ሽፋንን እያገኘ አይደለም፤ በእዚህ ዙሪያ ልትል የምትፈልገው ነገር ካለ?

ሳሙኤል፦ የጨዋታዎቹ የቀጥታ ስርጭትን አለማግኘት ለተመልካችም ሆነ ለራሳችን የሚቀንስብን ነገር አለ፤ በተለይም ለእኛ ጨዋታዎችን ደግመን እንዳንመለከት እያደረገን ስለሆነ የዲ ኤስ ቲቪ መኖር ጠቀሜታው ከፍ ያለ ነው።

ሊግ፦ አንተን ያጋጠመህ በመሆኑ ለቀድሞ ክለብህ መቻል የመጫወት ዕድሉን አግኝተሃል፤ በእዚህ ዙሪያ ማለት የምትፈልገው ነገር አለ?

ሳሙኤል፦ የመቻል ቡድን ለእኔ ሁሉ ነገሬ ነው፤ በጣምም የምወደው ክለብ ነው። ለዓመታት ተጫውቼበታለሁ። የቡድኑ አመራሮች እኔን በዲስፕሊን ጭምር በሚገባ ያውቁኛል። በተደጋጋሚ ከክለቡ እየወጣው በመመላለስሞ ክለቡን ለማገዝ ችያለሁ። ከታችኛው ሊግ ወደ ላይ ሲያድግም የበኩሌን አስተዋፅኦም አበርክቻለሁ።

ሊግ፦ በመቻል ባለህ የዘንድሮ ቆይታህ ጉዞህን በጠበቅከው ልክ እያስኬድከው ነው?

ሳሙኤል፦ በፍፁም፤ መቻልን አሁን ላይ በሚፈልገኝ ልክ እያገለገልኩት ነው ብዬ አላስብም። ያም ሆኖ ግን ጥሩ ነገር ማድረግ እንደምችል ግን አውቃለሁ  ከፍ  ባለ ደረጃ ላይ ለመቀመጥና ቡድኑንም  በጥሩ ሁኔታ ለመጥቀም ገና ይቀረኛል። ጠንክሬ በመስራት ያን ለማሳካት ጥረትን አደርጋለሁኝ።

ሊግ፦ የመቻል ክለብን አጠር ባለ ቃላት ግለፀው ተብለህ ብትጠየቅ ምላሽህ ምን ይሆናል?

ሳሙኤል፦ እጅግ ትልቅ ቡድን ነው፤ ለስፖርቱ እድገት የቆመም ነው። ሌሎችን ክለቦች ያየው ስለሆነ እዚህ ያለው የስፖርተኞች ክትትልና እንክብካቤው ይለያል። ጨርሶ አይገናኝምም።

ሊግ፦ በማርሽ ባንድም መደገፍ  ጀምራችኋል፤ ይሄን ነገር በምን ሁኔታ ተመለከትከው?

ሳሙኤል፦ ወጣ ያለው ይሄ የድጋፍ ሁኔታ ክለቡ በራሱ የሚያደርገው ነገር ነው። የአደጋገፉ ሁኔታም ለስፖርቱ እድገት ትኩረት እንደሚሰጥ ያሳየም ነውና እነዚህ ደጋፊዎች ኖረው በእዛ ሁኔታ ሲደግፉን ደስተኛ ነው የምንሆነው።

ሊግ፦ መቻልን በሀላፊነት በመምራት ላይ ስለሚገኘው አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ምን አልክ?

ሳሙኤል፦ እሱ ወጣትና የበሰለ ባለሙያ ነው። የተጨዋቾችን ሞራል እንዴት መገንባትና ማሰራት እንደሚችል ያሳየም ነው። አሁንም ትልቅ ነው ለወደፊቱም ትልቅ አሰልጣኝ መሆንም ይችላል።  ከእዛ የአሰልጣኝነቱ ሙያ ውጪም እንደ ሰው በጣም ጥሩ ሰውና ወንድማችንም ጭምር ነውና የምወደውና የማከብረው አይነት አሰልጣኝ ነው።

ሊግ፦ በሊጉ ውድድር  ውጤት በምታመጡበትና በምታጡበት ጨዋታ ውስጣዊ ስሜትህ ምን ነገርን ይነግርሃል?

ሳሙኤል፦ አንዳንዴ ሊያበሳጭህም፤ ሊያስደስትህም የሚችለው ነገር ቡድኑ ነው። ክለባችን ሁሌም ማግኘት ያለበትን ነጥብ ሲያጣ ያ ሁኔታ ያበሳጨኛል። በሆቴል አካባቢ አንነጋገርምም ነበር። እንኮራረፋለንም። ያን የምናደርገውም  ቡድኑ ይህ ውጤት አይገባውም ብለንም ስለምናስብ ነው። ውጤት ሲኖር ደግሞ የኳስን ነገር ታውቀዋለህ በተቃራኒው አንገት ከመድፋት ትደሰትበታለህና እነዚህን ሁኔታዎች ነው በመመልከት ላይ የምገኘው።

ሊግ፦ የኳታሩን ዓለም ዋንጫ ኤየተከታተልክ ነው?

ሳሙኤል፦ በሚገባ!።

ሊግ፦ ውድድሩን እንዴት ተመለከትከው?

ሳሙኤል፦ እስካሁን ያለው ፉክክር አሪፍ ነው። አርጀንቲናን እና ሊዮኔል ሜሲን በመደገፍም ነው እየተከታተልኩ የምገኘው። ለሜሲ ሲባል አርጀንቲና ዋንጫውን እንድታነሳም ምኞቴ ነው።

ሊግ፦ በውድድሩ ላይ በኳሱ ምርጥ ሀገራትን እነማንን ተመለከትክ?

ሳሙኤል፦ ከአርጀንቲና በተጨማሪ ብራዚልና ፈረንሳይ የሚጠቀሱ ናቸው።

ሊግ፦ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለአንተ ሰርፕራይዝ  ያደረገህ ሀገር ማን ነው?

ሳሙኤል፦ ጃፓን ናታ፤ ያስደነቁኝም የሚጫወቱበት ሁኔታ ከፍ ባለ ተነሳሽነት ስለሆነና ለእኛ ሀገር ሊጉ ላይ ለሚጫወቱ ቡድኖችም ማስተማሪያ ጭምር ስለሚሆኑም ነው። ከእዛ ውጪ ስርዓታቸው ይገርማል። ደጋፊዎቻቸውም ይለያሉ።

ሊግ፦ የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ምርጡ ጨዋታ የቱ ነው?

ሳሙኤል፦ የአርጀንቲና ጨዋታዎች ሁሉ ለእኔ ምርጦች ናቸው።

ሊግ፦ በዓለም ዋንጫው አፍሪካዊቷ ሞሮኮም የሩብ ፍፃሜውን ለመቀላቀል ችላለች፤ በእዚህ ዙሪያ አፍሪካዊ እንደ መሆንህ ምን አልክ?

ሳሙኤል፦ ሞሮኮ ብዙ አቅም ያላቸውን ተጨዋቾች የያዘች ሀገር ናት። በከፍተኛ ወኔና ፍላጎት የሚጫወቱ ተጨዋቾችም አላት። በእዚህ የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ውድድርም ሩብ ፍፃሜውን በመቀላቀሏ ደስ ብሎኛል። አሁንም በሩብ ፍፃሜው ጨዋታ ከስፔን ጋር ያደረጉትን እንቅስቃሴ ከደገሙት ፖርቹጋልን ማሸነፍ የማይችሉበት ምንም አይነት ምክንያት የለም።

ሊግ፦ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ እስካሁን ምርጡ ተጨዋች ለአንተ ማን ነው?

ሳሙኤል፦ አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲና ፈረንሳዊው ምባፔ ለእኔ ምርጦች ናቸው።

ሊግ፦ በመጨረሻ…..?

ሳሙኤል፦ በዘንድሮው  የሊግ ውድድር  እስካሁን ባከናወናቸው ጨዋታዎች በሚጠበቅብን ደረጃ ላይ ባንገኝም በእንቅስቃሴ ደረጃ ግን መልካም በሚባል ሁኔታ ላይ ነው የምንገኘው። ይህንን እንቅስቃሴም ወደ ውጤት ቀይረነው ከጥቂት ጨዋታ በኋላ ከፍ ወዳለ ስፍራ ላይ እንቀመጣለን ብዬ አስባለሁ።

 

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P