በመሸሻ ወልዴ /G.BOYS/
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና የማረሚያ ቤቶቹ ቦክሰኛ አሸናፊ ፉርጋሳ ህይወት ማለፍ የብዙዎቹን የቦክስ ስፖርት አፍቃሪዎች ቤተሰቦቹንና እና ጓደኞቹን ጭምር ያሳዘነ ሲሆን እሱን በተጨዋችነት ዘመኑ በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ያሰለጠነው አሰልጣኝ በላይነህ ሀይለመስቀል ደግሞ “ልክ የመሞቱን መርዶ እንደሰማው በጣም ነው የደነገጥኩት ያዘንኩትም፤ ካለ በኋላ አሸናፊ ማለት ጥሩ ቦክሰኛ እና መልካም የሆነ ሰው ክለቡንም በጣም የሚወድ እና ከልቡም የማያወጣ ነው በማለት ከወቅታዊ ሁኔታው አንፃር እሱን ልንቀብረው አለመቻላችን ሀዘናችንን የበለጠ ከፍ አድርጎብናል” በማለትም እምባ በተቀላቀለበት የሀዘን ስሜት ሀዘኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የቦክስ ቡድንን ከ1991 ጀምሮ መጀመሪያ ላይ በረዳትነት በኋላ ላይ ደግሞ በዋና አሰልጣኝነት በማሰልጠን ያሳለፈው የቀድሞው የህዝብ ማመላለሻ እና የማረሚያ ቤት ቦክሰኛ በተጨዋችነት ዘመኑ ከእነ ይፍሩ ሹመው ከመሳሰሉት ጋር በኮከብ ቦክሰኛነቱ ይታወቅ የነበረ ሲሆን ለሁለት ጊዜያት ያህልም የኢንተርናሽናል ውድድርን በሀገር ውስጥ አድርጓል።
በአሰልጣኝነት ዘመኑ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣት የቦክስ ቡድንን በመያዝም ወደ ቦትስዋና ኬንያ እና ሀዘርባጃንም በመሄድ በተለያዩ የኢንተርናሽናል ውድድሮች ላይ የተሳተፈ ሲሆን በቦክሰኝነታቸው የሚታወቁትን እነ ዩሃንስ ሽፈራው ፀጋስላሴ አረጋዊ /ኮሮኮንች/ ደረጄ መልሴ ሲሳይ አበበ ፍቃዱ በዙ በተጨዋችነት በሰፈሩ ፒያሳ የእሱን አርአያ የተከተለውን እንዳልካቸው ከበደን እና ከትናንት በስቲያ ህይወቱ ያለፈውን የመጀመሪያውን የ91 ኪሎ ግራም ተወዳዳሪ አሸናፊን በማሰልጠንም ለእውቅና ያበቃ ሲሆን
ታዋቂውን ቦክሰኛ አሰልጥኖት ከማለፉ አኳያም ህልፈቱ መቼም ቢሆን ከልቡ እንደማይወጣ እና ለቤተሰቦቹ ለመላው የቦክስ ስፖርት አፍቃሪዎች ለኮልፌ ልጆች እና በባህር ማዶም ለሚኖሩ የቀድሞ የቦክስ ስፖርት ጓደኞቼም ጭምር ከፍተኛ መፅናናትን ፈጣሪ እንዲሰጣቸው እና የአሼን ነፍስ አምላክ እንዲምረውም እመኛለውም” በማለት ሀሳቡን ገልጿል።