Free Porn
xbporn

buy twitter followers
uk escorts escort
liverpool escort
buy instagram followers
6x games unblocked fnaf unblocked games 76 unblocked games krunker.io slither unblocked io premium unblocked github.io unblocked games
Google search engine

በአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ዋንጫ መከላከያ፣ ጅማ አባጅፋርና ቅ/ጊዮርጊስ የግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል፤ የባህርዳር ከተማና የቅ/ጊዮርጊስ ጨዋታ ተጠብቋል

 

ካሳለፍነው ቅዳሜ አንስቶ በአበበ ቢቂላ ስታድየም ለ15ኛ ጊዜ እየተካሄደ የሚገኘው የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ዋንጫ ውድድር ተጧጡፎ የቀጠለ ሲሆን ከወዲሁም ከየምድባቸው ወደ ግማሽ ፍፃሜ ያለፉትን ቡድኖች እያሳወቀ ይገኛል፤ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን በገቢ ለማጠናከር ታስቦና ክለቦችም ለቤትኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ተሳትፎአቸው አቋማቸውን በመለካት በኩል እንዲረዳቸው የተዘጋጀው ይኸው ውድድር ጥሩ ፉክክር እየታየበት ሲሆን ተስፋ ሰጪ ችሎታ ያላቸው ወጣት ተጨዋቾችንም እየተመለከትንበት ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሲሳይ አድርሴ ፕሮሜሽን ጋር በፈጠረው የጋራ ጥምረት የአበበ ቢቂላ ስታድየምን ውስጣዊ ገፅታ በማስዋብና የመጫወቻ ሜዳውንም በማስተካከል እያካሄደ ባለው የእስካሁኑ ውድድር ከምድብ አንድ ቅዳሜ ዕለት መከላከያ አዲስ አበባ ከተማን 2-0፣ ጅማ አባጅፋር ኢትዮጵያ ቡናን 2-0፣ ከምድብ ሁለት ሰኞ ባህርዳር ከተማ አዳማ ከተማን 3-0፣ ቅ/ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን 3-0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፉ ረቡዕ ዕለት በነበረው ጨዋታ ደግሞ ከምድብ አንድ ጅማ አባጅፋር አዲስ አበባ ከተማን 1-0፣ መከላከያ ኢትዮጵያ ቡናን በተመሳሳይ ውጤት 1-0 ሲረቱ ሐሙስ በተደረገው ጨዋታ ደግሞ ከምድብ ሁለት ባህርዳር ከተማ ከፋሲል ከነማ 0-0 ሲለያዩ ቅ/ጊዮርጊስ አዳማ ከተማን 1-0 አሸንፏል፡፡

በእዚሁም መሰረት እስካሁን በተደረጉት የየምድቡ ሁለት ሁለት ጨዋታዎች  ሶስት ክለቦች ለግማሽ ፍፃሜው ያለፉ ሲሆን እነዚህም ክለቦች ከምድብ አንድ ጅማ አባጅፋር በ6 ነጥብና በ3 ንፁህ ግብ እንደዚሁም መከላከያም በ6 ነጥብና በ3 ንፁህ ግብ ሊያልፉ ችለዋል፤ የእዚሁ ምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ፕሮግራሙን ለመጨረስ ዛሬ የሚካሄድ ሲሆን በ8 ሰዓት ኢትዮጵያ ቡናን ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ሲያገናኝ በ10 ሰዓት ደግሞ የምድቡ አንደኛ ሆኖ ለመጨረስ መከላከያን ከጅማ አባጅፋር ጋር ያፋልማል፡፡

በአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ሌላው የምድብ ሁለት ጨዋታ ቅ/ጊዮርጊስ በ6 ነጥብና በ4 ንፁህ ጎል የግማሽ ፍፃሜውን ከወዲሁ ሲቀላቀል የእዚሁ ምድብ ቀጣይ ሀላፊ ደግሞ ነገ እሁድ በሚደረገው ጨዋታ ይታወቃል፤ የነገ የጨዋታው ተፋላሚዎችም በ8 ሰዓት ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ ይጫወታሉ፤ አዳማ ከተማ ከወዲሁ መውደቁን ያረጋገጠ ሲሆን የፋሲል ከነማ የማለፍ እድል የሚወሰነው ደግሞ አዳማን አሸንፎ ባህርዳር ከተማ በቅ/ጊዮርጊስ ከተሸነፈለት ብቻ ነው፤ እዚህ ላይ የሚገቡ ግቦችም የቡድኖቹን የማለፍና የመውደቅ እድሎችን የሚወስኑ ይሆናል፡፡ ሌላው በ10 ሰዓት በሚደረገው ጨዋታ ባህርዳር ከተማ ግማሽ ፍፃሜውን ሊቀላቀል የሚችለው ከተጋጣሚው ቅ/ጊዮርጊስ ጋር አቻ ከተለያየና ካሸነፈ ሲሆን ሌላው ተሸንፎም ሊያልፍ የሚችልበት እድል እንዳለውም በሁለቱ የዕለቱ ግጥሚያዎች ከሚቆጠሩት ግቦች በመነሳት የሚወሰንም ይሆናል፡፡

የቅ/ጊዮርጊስና የባህርዳር ከተማ የእሁዱ ጨዋታ በእዚህ ሳምንት ከሚደረጉት ፍልሚያዎች የሚጠበቅበት ሌላም ምክንያት ያለው ሲሆን ምድቡን በቀዳሚነት ለመፈፀምም የሚደረግ መሆኑ ነው፤ ቅ/ጊዮርጊስ 6 ነጥብ ሲኖረው ባህርዳር ከተማ 4 ነጥብ ነው ያለው፡፡

በአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ የእስካሁኑ ፍልሚያዎች በየጨዋታው በኮከብ ተጨዋችነት ለሚመረጡ ተጨዋቾችም የ12 ሺብርና የዋንጫ የአዋርድ ሽልማት እየተሰጠ ሲሆን ይህ ተጨዋቾችን እያበረታታም ይገኛል፤ በእስካሁኑ ጨዋታዎችም በመከላከያና በአዲስ አበባ ከተማ ጨዋታ የመከላከያው ቢኒያም በላይ፣ በጅማ አባጅፋርና በኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ የጅማ አባጅፋሩ ዳዊት ፍቃዱ /አቡቲ/ በባህርዳር ከተማና በአዳማ ከተማ ጨዋታ የባህርዳር ከተማው ዓሊ ሱሌይማን፣ በቅ/ጊዮርጊስና በፋሲል ከነማ ጨዋታ የቅ/ጊዮርጊሱ ሀይደር ሸረፋ፣ በጅማ አባጅፋርና በአዲስ አበባ ከተማ ጨዋታ የጅማ አባጅፋሩ መሐመድ ኑር፣ በመከላከያና በኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ የመከላከያው ቢኒያም በላይ፣ በባህርዳር ከተማና በፋሲል ከተማ ጨዋታ የባህርዳር ከተማው አህመድ ረሺድ /ሺሪላ/ እና በቅ/ጊዮርጊስና በአዳማ ከተማ ጨዋታ የቅ/ጊዮርጊሱ ያብስራ ተስፋዬ ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል፡፡

spot_img
ተመሳሳይ ጽሁፎች

አስተያይት ያስፍሩ

እባክዎን አስተያይትዎን ያስፍሩ
እባክዎን ስምዎን እዚህ ያስገቡ

ትኩስ ዜናዎች

P